በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚቆም የነጻነት ትግል እንደማይኖር በተግባር ለማሳየት ዝግጁዎች ነን። ርዕስ አንቀፅ

AG7-logo-300x300የህወሃት አገዛዝ ለዛሬ የካቲት 23 ቀን 2010 ጠርቶት የነበረው አስቸኳይ የፓርላማ ስብሰባ የካቲት 9 ቀን 2010 የሚንስትሮች ምክር ቤት የተባለው ስብስብ ያወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በ346 ድምጽ ድጋፍ በ88 ተቃውሞና በ7 ድምጸ ታዕቅቦ ማጽደቁን አስታውቆአል። ከዚህ የዛሬው የፓርላማ ውሳኔ ሁለት ነገሮችን ማስተዋል ተችሎአል።

1. ያለፈውን ምርጫ መቶ በመቶ በማሸነፍ 547ቱንም የአገሪቱን ፓርላማ መቀመጫ ሙሉ በሙሉ እንደተቆጣጠረ በኩራት ሲደሰኩርና አለምን ሲያስደምም የቆየው የህወሃት/ኢህአደግ አገዛዝ በዛሬው የፓርላማ ውሎ የድጋፍና የተቃውሞ ድምጽ የሰጡ አባላቱ ብዛት 441 ብቻ እንደሆኑ ሲያስታውቅ የተቀሩት 106 አባላቱ Continue reading

Advertisements

የዶክተር መረራ ከእስር መፈታት

ከአንድ ዓመት እስራት በኋላ ዛሬ  የተለቀቁት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ፣ ኦፌኮ፣ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ እንዲፈቱ ጠየቁ። ዶከተር መረራ እቤታቸዉ ሲደርሱ ዘመዶቻቸዉ እና በርካታ ደጋፊዎቻቸዉ ደማቅ አቀባበል አድርገዉላቸዋል።

Merera-Gudina-Politics-court-hearing-source-VOA-Amharic-1

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ፣ኦፌኮ፣ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ከአንድ ዓመት በላይ እስር ላይ ከቆዩ በኋላ ዛሬ እቤታቸዉ Continue reading

አገራችንን ከተደቀነባት አደጋ መታደግ የሚቻለው የሥርዓት ለውጥ በማምጣት ብቻ ነው። የአርበኞች ግንቦት 7 ርዕስ አንቀጽ

AG7-logo-300x300የአገራችንን ሉአላዊነት እና የህዝባችንን አንድነት ድርና ማግ ሆኖ አቆራኝቶ ለዘመናት ያቆዩትን እሴቶች ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ህወሃት እንደ ድርጅት መሪዎቹም አንደ ቡድን ልዩ ጥቅም እናገኛለን በሚል የፖለቲካ ስሌት ላለፉት 27 አመታት ረጅም ርቀት ተጉዘዋል። በዚህም የተነሳ አብዛኞቹ አመራሮች እና ለአመራሩ ቀረቤታ ያላቸው ካድሬዎች እስከነ ዘመዶቻቸው የአገሪቱን ፖለቲካ ሥልጣን ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚውንም በበላይነት ለመቆጣጠር ዕድል አግኝተዋል። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያቤት ውስጥ የአፍሪካ ጉዳይ ረዳት ሚንስትር እና በተለያዩ አገሮች የአገራቸው አምባሳደር ሆኖ ለረጅም ጊዜ ሲያገለግሉ የኖሩት ሚስተር ሄርማን ኮሄን ሰሞኑን ለሚዲያ በሰጡት ምስክርነት ይህንን Continue reading

የወያኔ አገዛዝ ካጠመደልን የእርስ በእርስ እልቂት ህዝባችንንና አገራችንን እንታደግ። የአርበኞች ግንቦት7 ርዕስ አንቀፅ

የህወሃት አገዛዝ ለሥልጣን ዕድሜው መራዘም ሲል በአገራችን ያሰፈነው የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የጋራ ታሪክ ባለቤት የሆነውን ህዝባችንን በባህልና በቋንቋ ሸንሽኖ አንደኛው ከሌላኛው ጋር ምንም የሚያቆራኘው ታሪካዊም ሆነ ወገናዊ ትሥሥር በመካከሉ እንደሌለ በመስበክ እያንዳንዱ በጥላቻና በጥርጣሬ እንዲተያይ የማድረግ ስልታዊ እርምጃ ነው።

ተደጋግሞ እንደተገለጸው ህወሃት የተጠቀመበት ይህ የአንድ አገር ዜጎችን በቋንቋና በባህል ከፋፍሎ የመግዛት ፖሊሲ አውሮፓዊያን አፍሪካን በቅኝ ግዛትነት በተቀራመቱበት ዘመን ከተጠቀሙበት ስልት የተቀዳ መሆኑ ግልጽ ነው። በዚያን ዘመን ቅኝ ግዛት ሥር የወደቁ የአፍሪካ አገሮች የቀድሞ ቅኝ ገዥዎቻቸው ተጠቃለው ከወጡላቸውና በራሳቸው ዜጎች መመራት ከጀመሩ ወዲህ እንኳ ትተውባቸው ከሄዱት የርስ በርስ ክፍፍል መውጣት አቅቶአቸው ላለፉት 50 እና 60 አመታት በመገዳደልና አንዱ ሌላውን እንደጠላት በመቁጠር ሲናቆሩ ከባርነት ቀንበር ነጻ ወጥቻለሁ ላለው ህዝባቸው ኑሮ መሻሻል Continue reading

ሕልም አለኝ ከአርበኛ ታጋይ ዕዝራ ዘለቀ ከኤርትራ

ሕወሃት/ኢሕአዴግ መሰረቱ ተናግቶ እየተንገዳገደ ነው። መውደቁ እንዴትና መቼ የሚለው ጥያቄ ሊያነጋግር ይችላል። ግን 12373403_184095175272945_8742457289203482535_nመዉደቁ አይቀሬ ነው። ከብዙ ምልክቶቹ አንደኛውና ዋነኛው በአሁን ሰዓት በቄሮዎቹ የገጠመው የከረረና የመረረ ተቃውሞ ነው።

ሆኖም ግን ይህንን በእጅጉ አንገብጋቢ የሆነውንና ተገቢ ምላሽ Continue reading

ሁላችንም ለለውጥ እንነሳ

አገራች ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ደረጃ ጊዜ ለውጥ ልትወስድባቸው የሚገባት ጉዳዮች

አሉ።ትውልዱ የለውጥ ስሜትን ሊያመጣ የሚገባበት ዘመን ላይ ነን።ለውጥTheodros Ghezahegn

ሲባል ከምን ከምን ልንል እንችላለን።አንደኛው ከጎሰኝነት እስራት፣ ከጥላቻ ፖለቲካ፣

 

ከድህነት፣  ከአምባገነኖች ጭቆና፣ ከአደገኛ ባህሎች ሁሉ ነው  አገራችን ኢትዮጵያ

ከገባችበት ዙሪያ መለስ ችግሮች ለመውጣትና የተሻለ ዓለም ለማየት ፖለቲካዊ ለውጥ

ብቻውን አይበቃትም። ሕወሓት ኢሕአዴግ ወደሥልጣን ከመጣ በኋላ የገባንበት ስስታም ፖለቲካ ደግሞ አንዱ ኢትዮጵያውያን የለውጥ ክተት ልናውጅበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ አገራችን ከእኔ እኔ እኔ ከሚል ራስ ወዳድና ጠባብ አስተሳሰብ ወጥታ ወደ እኛ አስተሳሰብ መግባት Continue reading

የብር የውጭ ምንዛሬ ተመን ከነገ ጀምሮ የ15 በመቶ ማስተካከያ ይደረግበታል

FB_IMG_1507632929716አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የወጪ ንግድን ለማሳደግ ሲባል ከነገ ጀምሮ የብር የውጭ ምንዛሬ ተመን በ15 በመቶ ማስተካከያ እንደሚደረግበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገለፀ። Continue reading

%d bloggers like this: