አምባሳደር ስዩም መስፍን ቻይና በአካባቢ ውድመት ላይ የሚቀርብባትን ክስ መከላከል አያስፈልጋትም አሉ

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአሁኑ የቻይና አምባሳደር ስዩም መስፍን ከሲሲቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ቻይና በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ማእድናትን በምታወጣበት ጊዜ የአካባቢ ውድመት ታደርሳለች እየተባለ በአፍሪካውያንና በምእራባዊያን ዜጎች የሚደርስባትን ወቀሳ መከላከል አያስፈልጋትም ብለዋል።

አምባሳደሩ ይህን መልስ የሰጡት የሲሲቲ ጋዜጠኛ ” ብዙውን ጊዜ አገራችን በሌሎች አገሮች ማእድናትን ስታወጣ የአካባቢውን ህዝቦች ታፈናቅላለች፣ በአካባቢውም ላይ ውድመት ታደርሳለች እየተባለች ትወቀሳለች፣ ይህ ችግር በኢትዮጵያም ውስጥ አለ?’ የሚል ጥያቄ ካቀረበላቸው በሁዋላ ነው።

አምባሳደር ስዩም መስፍን ሲመልሱ ” ቻይና የአፍሪካን ማእድን ለማልማት እዚህና እዛ ለሚቀርብባት ወቀሳ ራሱዋን መመከላከል አያስፈልጋትም፣  የእኛ ነባር ወዳጆች እኮ ይህንኑ ለዘመናት ሲያካሂዱ ነበር” ብለዋል።

“የምእራባዊያን ኩባንያዎች ማእድናትን በአፍሪካ ውስጥ አውጥተው በተወሰነ ደረጃ ቀይረው ወደ ወደ አውሮፓ ሲልኩ ቀረጥ ይከፍላሉ፣ ማእድናትን እንዳለ ሲልኩ ግን ቀረጥ አይከፍሉም ይህ በአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ እንዱስትሪ ላይ እድገት እንዳይኖር አድርጓል” የሚሉት አምባሳደር ስዩም  ቻይና ይህንን እስካልኮረጀች ድረስ በአካባቢ ውድመት ዙሪያ ለሚደርስባት ክስ ትኩረት መስጠት እንደማይገባት መክረዋል።

ጋዜጠኛው ” ቻይናዎች ጥሩ ምክር ከእውነተኛ ወዳጅ ይገኛል ይላሉ” በማለት በአምባሳደር ስዩም መስፍን መልስ መርካቱን ገልጿል።

ቻይና በአፍሪካ ውስጥ ማእድናትን ፍለጋ በምታካሂደው እንቅስቃሴ በአካባቢ ላይ ጉዳት ታዳረስላች ለህዝብ መፈናቀልና ችግር ትኩረት አትሰጥም በማለት ወቀሳ እንደሚቀርብባት ይታወቃል።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: