33ቱ ፓርቲዎች ” በህዝባዊ ንቅናቄ ትግላችንን እንቀጥላለን” አሉ

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከምርጫ ቦርድ ጋር ውዝግብ ውስጥ የከረሙት 33ቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ዛሬ ባወጡት መግለጫ  ለምርጫ ቦርድና ለመንግስት ያቀረብናቸው ጥያቄዎች ሳይመለሱ ” ስለምርጫ ተሳትፎ ማሰብ ‘ ተጨፈኑ ላሞኛችሁን’ መቀበል በመሆኑ በጋራ ይዘን ለተነሳነው ጥያቄ ምርጫ ቦርድም ሆነ ገዢው ፓርቲ ተገደው እንዲሰሙ ለማድረግ ህዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠርና በማስተባበር የተባበረና የተቀናጀ ትግላችንን እንቀጥላለን” ብለዋል።

ፓርቲዎቹ ” ጥያቄያችን ባልተሟሉበት እውነታ እንደ ፓርቲ ስለውድድር፣ እንደዜጋ ስለመራጭነት ምዝገባ መነጋጋር፣ ለገዢው ፓርቲ የምርጫ ሴራ ይሁንታ መስጠት፣ አልፎም የምርጫ መርሆዎች እንዳይከበሩ በመተባባር በህገ መንግስቱ መሰረት ዘላቂ የመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ የሚደረገውን ሰላማዊ ትግልና ጥረት ወደ ሁዋላ መጎተት ነው።” ብለዋል፡፡

“ዋነኛው ባለድርሻ የሆነው ህዝብ ያነሳው ጥያቄ እስኪመለስ መራጩን ህዝብ ከጎናችን እንዲሰለፍ በማድረግ በጥያቄያችን ያነሳናቸው ጉዳዮች መፍትሄ እንዲያገኙ እንታገላለን” የሚለው መግለጫ ፣ ” ወደ ፍርድ ቤት መሄድ፣ ከህዝቡ ጋር በህዝባዊ የውይይት መድረክ የፓርቲዎችን አቋም ማሳወቅ የሚሉት” በአጭር ጊዜ ውስጥ ከሚሰሩት ስራዎች መካከል መሆናቸውን ጠቁማል።

ፓርቲዎቹ በምርጫው ላለመሳተፍ ከወሰኑባቸው ምክንያቶች መካከል ” በህዝቡ ውስጥ ያለው ጠንካራ የለውጥ ፍላጎት፣ እስከዛሬ በተደረጉት ምርጫዎች መሰላቸትና ፓርቲዎቹ ያነሱዋቸው ጥያቄዎች የህዝብ የመወያያ አጀንዳ መሆናቸው” የሚሉት ተጠቅሰዋል።

ጉዳዩን በማስመልከት አቶ አስራት ጣሴ ለኢሳት ራዲዮ እንደገለጡት ህዝቡን አንቀሳቅሶ እስከመጨረሻው መዝለቅ ፈታኝ ነው

ይህንን ሰላማዊና ህጋዊ ትግል ማምጣት ካልተቻለ አመራሩ ራሱን መፈተሽ አለበት በማለት አቶ አስራት አክለዋል:: ምርጫ ቦርድ የምርጫ ምልክት ያልወሰዱ ፓርቲዎች በምርጫው እንደማይሳተፍ ማስታወቁ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ሰፈር ለሰፈር እየዞሩ ህዝቡ ለምርጫ እንዲመዘገብ እያሰገደዱ መሆኑን በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።

ኢሳት በምርጫ የሚመዘገበው ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ መንግስት የቤት ለቤት ቅስቀሳ ሊጀምር መሆኑን መዘገቡ ይታወሳል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: