(ሰበር ዜና) የዛሬው የሲኖዶስ ስብሰባ ውሎ፤ አባይ ጸሐዬ ውጭ ያለው ሲኖዶስ በአሸባሪነት ይከሰሳል አሉ

“መንግስት የሚላችሁን የማትቀበሉ ከሆነ የቤተክርስቲያን መሬቶችን እንወርሳለን”

“ከአሁን በኋላ ከሁሉም ሲኖዶስ አባላት ጋር ሳይሆን እኛ በመረጥናቸው 5 ጳጳሳት በኩል ነው የምንነጋገረው”

“ውጭ ያለውን ሲኖዶስ በቅርብ ቀን በአሸባሪነት እንከሳለን”

“ስደተኛው ሲኖዶስ ሃገር ቤት የሚመጣው መንግስት ለመገልበጥ ነው” አባይ ጸሐዬ

አባይ ጸሐዬ በአሸባሪነት ይከሰሳሉ ካሏቸው አባቶች መካከል አቡነ መልከጼዲቅ

አባይ ጸሐዬ በአሸባሪነት ይከሰሳሉ ካሏቸው አባቶች መካከል አቡነ መልከጼዲቅ

(ዘ-ሐበሻ) በሃገር ቤት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ትናንት የጀመረውን አስቸኳይ ጉባኤ በዛሬው ውሎው በ እርቀ ሰላሙ ዙሪያ ሲወያይበት የነበረውን ጉዳይ ዛሬ አጠናቀቀ። ነገ ሐሙስ በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይቶ መግለጫ እንደሚያወጣ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከስፍራው ዘግበዋል።በዛሬው የስብሰባ ውሎ ከመንግስት አቶ አባይ ጸሐዬ እና የፌደራል ጉዳዮች ሚ/ር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም የተገኙ መሆኑን ያስታወቁት የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች፤ አቶ አባይ ጸሐዬ “እርቀሰላምና የቤተክርስቲያን አንድነት ይቅደም” የሚሉ አባቶችን ሲያስፈራሩ ውለዋል። አቶ አባይ ጸሐዬ እንዳሉት እነዚህ አባቶች በአቋማቸው የሚጸኑ ከሆነ መንግስት የቤተክርስቲያን መሬቶችን ይወርሳል። መንግስት በርከት ያሉት ጳጳሳት መሬት ስላላቸው በዚህ መሬትን መጠቀሚያ አድርጎ አባቶቹ አቋማቸውን እንዲቀይሩ አስፈራርቷል። ብዙ ሕዝበ ክርስቲያን ሲጠብቀቅ የነበረው የቤ/ክ አንድነት ተስፋው እየተሟጠጠ ነው::

“በውጭ ያለው ሲኖዶስን ከሙስሊሞቹ ጋር አብረን በቅርብ ቀን በሽብርተኝነት እንከሳቸዋለን” በማለት አቶ አባይ ጸሐዬ በግልጽ መናገራቸውን ያጋለጡት የዘ-ሐበሻ ምንጮች በተለይ ከስደተኛው ሲኖዶስ ብጹዕ አቡነ መልኬጼድቅን በሽብርተኝነት ለመክሰስ ሙሉ ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል።

“አቋማችሁን የማትቀይሩ ከሆነ የቤተክርስቲያንን መሬት ወርሰን ባዶ እጃችሁን እናስቀራለን” በማለት የደነፉት አቶ አባይ ጸሐዬ ከአሁን በኋላ በ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ላይ ትኩረት እንዲደረግ አስጠንቅቀዋል ያሉት ምንጮቻችን ‘ውጭ ያለው ሲኖዶስ ሃገር ቤት የሚመጣው መንግስት ለመገልበጥ ነው” ሲሉ መናገራቸውን እነዚሁ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘግበዋል።

ከአሁን በኋላ ኢትዮጵያ ያለውን ሲኖዶስ መንግስት በወከላቸው አምስት ጳጳሳት በኩል ነው የምንገናኘው በማለት አቶ አባይ ጸሐዬ የነዚህን ጳጳሳት ስም መናገራቸውንና በነርሱ በኩል የመንግስትና የሲኖዶሱ ግንኙነት እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

እነዚህም 5 ጳጳሳት፡

1ኛ. አቡነ መቃርዮስ

2ኛ. አቡነ ሳዊሮስ

3ኛ. አቡነ ሳሙኤል (ዋናው ሰብሳቢ)

4ኛ. አቡነ ቀለሚንጦስ

5ኛ. አቡነ ጎርጎርዮስ  እንደሚሆኑ ተናግረው ከነዚህ አምስት ጳጳሳት በተጨማሪም አቡነ ገብርኤል አብረው እንደሚሰሩ ተገልጿል። አቡነ ሳሙኤል ደግሞ እነዚህን 5 ጳጳሳት በመምራት የመንግስትን ጉዳዮች ያስፈጽማሉ።

ነገ በሚሰጠው መግለጫ ላይ ሃገር ቤት ያለው ሲኖዶስ “ለፓትርያርክ መርቆርዮስና ለስደተኛው ሲኖዶስ ጥሪ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል” ያሉት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ጥሪው የሚሆነውም ፓትርያርክ እንዲሆኑ ሳይሆን ሃገር ቤት ገብተው በፈለጉበት ቦታ እንዲቀመጡ የሚል ይሆናል ሲሉ ምንጮቻችን ዘግበዋል። ሃገር ቤት ያለው ሲኖዶስ ይህን ጥሪ የሚያደርገው ም ዕምናኑን ለማደናገር ታስቦ እንጂ ወትሮውንም ውጭ ያለው ሲኖዶስ ይህን እንደማይቀበል ስለሚያውቅ ነው ያሉት እነዚሁ ምንጮች ድርጊቱ “እንዳያማህ ጥራው፤ እንዳይበላ ግፋው…” ዓይነት ነው ብለዋል።

እንደዘሐበሻ ምንጮች ከሆነ በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል የሚኖረው አንድነት ተስፋ የሌለው ይመስላል። በተለይ መንግስት በግልጽ ውጭ ያለውን ሲኖዶስ መንግስት ለመገልበጥ ነው የሚመጣው፤ በአሸባሪነት እንከሳለን፤ ሃገር ቤት ያሉትን የሰላምና የአንድነት ናፋቂ አባቶችን “መሬታችሁን እንወስዳለን” የሚል ማስፈራሪያ መስጠቱ በሕገመንግስቱ የተደነገገውን የ እምነት ነፃነት የሚጻረር ነው ሲሉ እነዚሁ የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል።

ይህን ጉዳይ ተከታትላ ዘ-ሐበሻ አሁንም በሰበር ዜና መዘገቧን ትቀጥላለች።

ይህ በ እንዲህ እንዳለ በስደት የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በሎስ አንጀልስ ድንግል ማርያም ቤ/ክ ተጀምሯል። ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ከካናዳ ተጉዘው የተገኙ ሲሆን በዛሬው ዕለት ሲነጋገሩ የዋሉትም የሰላምና የአንድነት መፍትሄው እየከሸፈ በመሆኑ በስደት ያለውን ሕዝበ ክርስቲያን ለማጽናናትና፣ ወንጌልን በመስበክ እንዴት በስደት ያለውን ም እመናን አንድ ማድረግ በሚችልበት ሁኔታ ተነጋግሯል። ይህ ጉባኤ ነገም የሚቀጥል ሲሆን ከምንጮቻችን የምናገኘውን መረጃ ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ከማድረስ ወደኋላ አንልም።

15, January 2013

zehabesha

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: