የባለራዕይ ማኅበር ወጣቶች ጸሐፊ በደኅንነት ኃይሎች ጉዳት ደረሰብኝ አለች

የባለራዕይ ማኅበር ወጣቶች ጸሐፊ በደኅንነት ኃይሎች ጉዳት ደረሰብኝ አለች (ኢትዮ ምኅዳር)

የባለራዕይ ወጣቶች ማኅበር የጉለሌ ክፍለከተማ ጸሐፊ የሆነችው ወጣት ወይንሸት ስለሺ የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ ከምሽቱ 12፡30 ሰዓት ሲሆን አፍንጮ በር አካባቢ ከሚገኘው የማኅበሩ ጽ/ቤት ለመድረስ 50 ሜትር ሲቀራት በደኅንነት ኃይሎች ተይዛ አንድ ሌሊት ሙሉ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳት እንደደረሰባት ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቀች፡፡ በማኅበሩ ጽ/ቤት ዘወትር ማክሰኞ የሚደረገውን የመማማሪያ ፕሮግራም ለመሳተፍ እየሄደች ሳለ በጽ/ቤታቸው አቅራቢያ መንገድ ዳር ጠብቀው አንገቷ ስር መርፌ ከወጓት በኋላ ራሷን ስትስት መኪና ውስጥ በማስገባት አቃቂ/ቃሊቲ በሚገኝ አንድ ስውር ቪላ ቤት በማስገባት ከብርሃኑ ነጋ ጋር ግንኙነት አላችሁ፤ ከውጭ አገር የሚደግፋችሁ ማነው የሚሉ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበው በሰጠችው ምላሽ ባለመደሰታቸው፣ በጥፊ መመታቷን ገልፃ ለጠየቋት ጥያቄ እውነቱን አውጪ በማለት ግራ እግሯን በመጋረጃ ብረት በመምታት ጉዳት ያደረሱባት ሲሆን በኤሌክትሪክ ንዝረትም ጀርባዋ ላይ የከፋ ጉዳት እንደደረሰባት ገልጻ የህክምና ውጤቷን በመጠባበቅ ላይ መሆኗን ለዝግጅት ክፍላችን አስታውቃለች፡፡ ለሥራ የምትጠቀምባቸውን ሁለት ቴፕ ሪከርደሮች (ዲጂታልና አናሎግ) የቤተሰብ ሁለትሺሕ አንድ መቶ ሀምሳ ሰባት ብር እና የሞባይል ስልኳንም እንደወሰዱባት አስታውቃለች፡፡

—–

በተጨማሪው ጋዜጣው በወጣቷ የተጻፈውን ሙሉ ዝርዝር ይዞ ወጥቷል፡፡

እነሆ በጥቂቱ …

“…ወጣት ወይንሸት እባላለሁ፡፡ የጉለሌ ክ/ከተማ የባለራዕይ ወጣቶች ማኅበር ጸሐፊ ነኝ፡፡ በግሌ የደረሰብኝ ማክሰኞ ታህሳስ 30 ቀን 2005ዓ.ም ማታ ከምሽቱ 12፡30 ሰዓት ላይ ዘወትር በመሃበሩ እንደምናደርገው የውይይት ጊዜ አለን፡፡ በዚህ ውይይት ላይ ለመገኘት ሽሮ ሜዳ አካባቢ የሚገኘው የመኖሪያ ቤቴ ወደ አፍንጮ በር የሚገኘው ማህበራችን ቢሮ ስሄድ የማኅበሩ በር ለመድርስ 50 ሜ ሲቀረኝ ከለሩን ያላየሁት መኪና ሁለት ሰዎች ይዞ አጠገቤ ቆመ መንዱም በጣም ጠባብ ስለነበር ወደዳር ወጥቼ ላሳልፈው ዞር ስል አንገቴ ስር መርፌ ወጉኝና እራሴን አስተውኝ በመኪና ውስጥ ጎትተው እስከሚያስገቡኝ ድረስ ብቻ ነው የማውቀው፡፡

ከዚያ በኋላ ይዘውኝ ሲሄዱ ራሴን አላውቅም ነበር፡፡ ቃሊቲ አካባቢ ጉራንጉሩ ውስጥ ስንደርስ መኪናው ቆመ፡፡ ራሴን ያወቅኩት ከአመራሮቼ ጋር በራሴ ስልክ ሲደዋወሉ ነበር፡፡ እነርሱን በጣም አስደንግጠው ሲረብሹ ከቆዩ በኋላ ነው እኔ የነቃሁት፤ ስነቃ አንደኛው ሰው እሺ ባለራዕይ ነቃሽ አለኝ፡፡ ምን ፈልጋችሁ ነው አልኩት፡፡ በወቅቱ የወጉኝ መርፌ ማጅራቴን እና ጭንቅላቴን ይዞኝ ስለነበር ዓይኔን በደንብ ገልጬ ማየት አልቻልኩም፡፡ ራሴን ከብዶኝ ነበር፡፡ የሆነ የተቀዳ ድምፅ አሰሙኝ፤ የማኅበራችን ፕሬዚደንት ሀብታሙን ድምፅ አሰሙኝ፡፡ ሀብታሙ ስለባለራዕይ ነው የሚያወራው፡፡ ከዚያ የማላውቀው ድምፅ አሰሙኝ፡፡ ይህ ድምፅ የብርሃኑ ነጋ ድምፅ ነው፡፡ ከሱ ጋር ንግግር ያደረጉት ድምፅ ነው ተቀርፆ የመጣ ነው፡፡ ስለዚህ ከግንቦት ሰባት ጋር ኅብረት አላችሁ፡፡ ስለዚህ ይህን መረጃ ይዘናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የማኅበሩ አባላት የእነብርሃኑን፣ የሀብታሙን እና ሌሎች አመራሮችን ድንገት ቆመው የተነሱ የሚመስል ፎቶ አውጥተው እሱም የአባልነት ፎቷቸው መሆኑን ከዚያ ያስመጣነው ነው ስለዚህ ያላችሁን ኅብረት ተናገሪ አለኝ፡፡

 

…” MahiFantish Wube

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: