ጠ /ሚያችን ሃይለማርያም ራሳቸው እሰረኛ “እስረኛ የለም” ይላሉ

ጠ /ሚያችን ሃይለማርያም ራሳቸው እሰረኛ “እስረኛ የለም” ይላሉ

Hailemriam the puppetመቸም አገራችን ካለችበት ምስቅልቅል  የምትወጣ መስሎን  በትግሬ  ነጻ  አውጭ ግንባር  የሚመራው ኢህአዲግ  በጠመንጃ  ሃይል ስልጣን ከያዘበት ማግስት ጀምሮ “የዘመነ መሳፍንት” ጊዜ አስተሳሰቡን ትቶ አለም የደረሰበት ዲሞክራሲያዊና መልካም አስተዳደር  ደረጃ ላይ ባንደርስ እንኩዋ ጠጋ ብለን ለዘመናት ታፍኖና በችጋር ተቆራምዶ የኖረው ሕዝባችን የሚሰማውን አየተነፈሰ የለፋበት ሳይቀነስብት እየተቁኣደሰ ለመኖር የሚችልበት ስርእት እንዲዘረጋ ያልወተወትነው አልነበረም፡፡

ሰሚ ጠፋና አልሆነለንም፡፡ አምባገነኑ ወያኔ/ኢሀአዲግ እያድር ጥሬ እንጂ ሊበስል አልቻልም፡፡ ለውትወታችን  የስጠው ምላሽ ሲሻው በጡቻ፡ አላያም በጠመንጃ እንዲያም ሲል አይን ባወጣ ፍርደ-ገምድል ፍርድ ሕዝባችንን ማሰቃየት ብቻ ነው፡፡ ሕዝባችንንም ካለአንዳች እረፍት ሲያሰቃይ እነሆ ሁለት አሰርተ-አምታት አገባዶ ሶስተኛውን ተያይዞታል፡፡

መለስ በጌታ ፍርድ ከስልጣናቸው ሲወገዱ ግራ-ገቡን ሃይለማርያም ደሳልኝን ሳይወዱ ተክተው ሲሄዱ ነገሩ ሳይገባን ከእነበረከት ስምኦን ይልቅ ደስ ያለን እኛ ነበርን። የሁዋላ ሁዋላ “የምጣዱ እያለ የእንቅቡ በመንጣጣቱ”ፍዝዝ ብለን እያየን  መደነቅ ብቻ ሳይሆን የባሰ ግራ ተጋብትንም ነበር፡፡ ለካ  ነገሩ ወዲሀ ነው፡፡  እኛ ደስ ብሎን የነበር ሃይለማርያም ለዘመናት ተጨቁኖ ይኖር ከነበረው የደቡብ ክፍለ-አገራችን ከሆኑ ወገኖቻችን አብራክ ወጥተው ከፍተኛ የስልጣን እርክን  የደረሱ ስለመስለን ነበር፡፡ “ጉድ ወደ ሁዋላ ነው” እንዲሉ ሁዋላ ስንረዳው የእነ በረከት ደስታ ከኛ የተለየ ነው፡፡ እነርሱ የተደሰቱት ሙሽራው ሲወጣ ከተሻማው ዳቦ ባገኙት ጉራጅ ኖሮዋል። የተደበቀው በበለጠ የተከሰተልን ደግሞ ሃይለማርያም እራሳቸው በየመድርኩ እየወጡ የአምባገነኖቹ የእንግዴ ልጅ መሆናችውን  በጽናት ሲያረጋግጡ ነበር፡፡

ታዘው ይሆን ወይንም ወደው ባናውቅም   አንዴ ወጥተው የመለስ ተቀጥያ እንጂ ለኢትዮጵያ የራሳቸው ወጥ  የሆነ  የመልካም  አስተዳደር ራእይ እንደሌላቸው በገሀድ ነገሩን፡፡ አስተዳደራ ቸው የሚመራው በጀማ እንጂ እርሳቸው ከአፈ-ቀላጤነት በስተቀር ምንም ሚና እንደሌላቸው ሲያስታውቁን ደግሞ እንደዚሀ እራሱን ያዋረደ መሪ አይተን ስለማናወቅ  በጣም ደነገጥን፡፡  የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተብለው የመጨረሻው የስልጣን ጣሪያ ላይ ሲቀመጡ ሚኒስትሮቻቸውን የማያስሾሙ የጦር መኮንንኖቻቸውን  የማያስመድቡ ከሆነ የእኝህ ሰው ጠቅላይ ሚኒስትርነት እምኑ ላይ ነው እያልን ተጨነቅን፡፡ ለመሆኑ አንድ ስህተት ቢፈጠር በህሊናችን ያሉበትን ሁኔታ እያወቅን በሃላፊነት ልንጠይቃቸው ነወይ?እያልን ዋለልን፡፡ በአጠቃላይ   በከፍተኛ የመንግስት አስተዳደር ደረጃ ለሚከስቱ ጉዳዮች ሁሉ በሃላፊነት የምንጠይቀው አሳጡን፡፡

የዚህ አይነቱ ክስተት ሲፈጠር በታሪካችን የመጀመሪያ ልዜ እይደለም፡፡ በቀዳማዊ ሃይለስላሴ  ካቢኔ ጠቅላይ ሚ/ር የነበሩት አክሊሉ  ሃብተወልድ የንጉሱ ልጅ የነበሩት ልእልት ተናኘ ወርቅ    የበላያቸው ድብቅ ጠቅላይ ሚ/ር እንደነበሩ የንጉስ ነገስቱ መንግስት በወሎ ሕዝባችን ላይ ባደረሰው ጥፋት የተነሳ  ሲጠየቁ በእየዬ ማጋለጣቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡  ያ እየዬ ጩኽታቸው ግን አምሽቶ የመጣ ስለነበር ከሞት አላዳናቸውም፡፡ ተረሽኑ፡፡ ችግራቸውን በወቅቱ ለሕዝብ አሳውቀው ዞር ብለው በነበር ምናልባት ከክሱ በዳኑ ነበር። አላደረጉትም። በዚህም የተነሳ እኛን የመሰል የነጻነት ታጋይና ያገር ባለውለታ ሳንቀብራቸው ቀረን፡፡ ታሪካችንም ተበላሽ፡፡ ጠቅላይ ሚ/ር እክሊሉ ችግራቸውን በወቅቱ ያልተጋፈጡት አንድም ከማን አለብኝነት እምበለ በለዚያም በስንት ርኩቻ ያገኙትን ሰልጣን ላለማጣት ይሆናል፡፡  ክቡር ልጅ ሚካኤል እምሩ ግን ይህን አላደረጉትም፡፡ ለአጭር ጊዜም ቢሆን በደርግ ካቢኔ ጠቅላይ ሚ/ር ሆነው ስርተዋል፡፡ ነገር ግን የደርግ አካሄድ አስቸጋሪና የማይታረም መሆኑን ሲረዱ በዘዴም ሆነ በልምምጥ ራሳቸውን አገለሉ፡፡ ስለሆነም ከሕረተስቡ ተቀላቅለው በክብር ኖሩ፡፡

እኛ ሃይለማርያምን ልናከብራቸው እንፈልጋለን። የጠቅላይ ሚ/ር አክሊሉ እድል እንዲገጥማቸው አንሻም። ልንቀብራቸው እንፈልጋለን። እርሳቸው ግን መንገዱን መምረጥ አለባቸው፡፡ የአክሊሉን ወይንም የሚካኤልን። የመለስን እመርጣለሁ ካሉ ግን ጠባቸው ከሕዝብም፡ ከእግዚአብሄርም ከራሳቸውም ጋር መሆኑን ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ ስለ ፓለቲካ እሰረኛም ስናነሳ ቁጥሩን ከራሳቸው አንድ ብለው ቢጀምሩ መልካም ነው። ሃይለማርያም “እራሳቸው የፖለቲካ እስረኛ ሆነው “የፖለቲካ እስረኛ የለም ይላሉ፡፡ ይህ የተለመደ የመለስ አባባል ነው፡፡ እንዴት ራሳቸውን ማወቅ ይሳናቸዋል? ይልቁንስ እውነታውን ከመካድ እራሳቸውን ከእስር ቢያስፈቱ ይሻላቸዋል።

ጸሃፊው ዘነበ ታምራት በኢሜይል አድራሻቸው ztamira@yahoo.com ላይ ይገኛሉ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: