የመለስ ፋውንዴሽን አዋጅ ፀደቀ

–    ውይይቱ ለጋዜጠኞች ዝግ ነበር 

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ባለፈው ሐሙስ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፣ የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽንን ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ አዋጁን አፀደቀ፡፡

ውይይቱ በዝግ እንዲካሄድ በመደረጉ ጋዜጠኞች እንዳይገቡ ተከልክሏል፡፡

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከወጣትነት ዕድሜያቸው በድንገት ሕይወታቸው እስካፈበት ወቅት ድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝቦችና ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት፣ የልማታዊና ዲሞክራሲያዊ መንግሥት፣ እንዲሁም ዕድገት ያበረከቱትን አስተዋጽኦ መዘከርና ከትውልድ ትውልድ እየተወራረሰ እንዲኖር፣ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ‹‹መለስ ፋውንዴሽን›› መመሥረት አስፈላጊ መሆኑን መንግሥት ስላመነበት ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን የአዋጁ መግቢያ ይተነትናል፡፡

በሕይወት ዘመናቸው ያለ ዕረፍት ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ካበረከቱት በተጨማሪ ለአፍሪካውያን ሰላምና ደኅንነት፣ በዓለም መድረክ የአፍሪካን ጥቅም ለማስከበር ያደረጉትን አስተዋጽኦ፣ እንዲሁም በዓለም የአየር ንብረት ላይ የተጫወቱትን የአረንጓዴ አብዮት ሚና መዘከር ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገር ማድረግ፣ የመለስ ፋውንዴሽን መሠረታዊ ዓላማዎች መሆናቸውን አዋጁ እንደሚያስረዳ የሪፖርተር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

የአቶ መለስ አስከሬን አሁን ከሚገኝበት መካነ መቃብር ተነስቶ ፋውንዴሽኑ በሚያቋቁመው የመናፈሻና የጥናት ማዕከል እንደሚዘዋወርና ለሕዝብ ጉብኝትም ክፍት እንደሚሆን የፀደቀውን አዋጅ በመጥቀስ ምንጮች አብራርተዋል፡፡

ማዕከሉ ቤተ መጻሕፍትና የጥናት ማዕከልን ሲያካትት፣ አቶ መለስ በሕይወት ዘመናቸው ያነበቧቸውና ያጠራቀሟቸው በርካታ መጻሕፍት በዚሁ ማዕከል ውስጥ ለአንባቢያን ክፍት እንደሚሆኑ፣ የተመራመሩባቸው የጥናት ውጤቶችም በዚሁ ሥፍራ ተቀምጠው ትውልድ እንዲማርባቸው ይደረጋል፡፡ ፋውንዴሽኑ ማዕከሉን ከማስተዳደር በተጨማሪ ችግረኛ ሕፃናትን በተለይም የአገሪቱ ሴቶችን የነፃ ትምህርት ዕድል የመስጠት ተልዕኮም እንደሚኖረው ለመረዳት ተችሏል፡፡

በቅርቡ ከፓርላማው አባላት የቀረቡ ጥያቄዎችን ለመመለስ ተገኝተው የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በዚሁ የመለስ ፋውንዴሽን ዙሪያ ገለጻ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ቤተሰቦቻቸው፣ መንግሥት፣ ባለሀብቶችና ጓደኞቻቸው ፋውንዴሽኑን ለማቋቋም በሚያዋጡት ገንዘብ ድርሻ እንደሚኖራቸው ገልጸዋል፡፡ ውይይቱን ጋዜጠኞች እንዳይከታተሉት ዝግ በመደረጉ ግን ዝርዝር የፋውንዴሽኑ ባለድርሻዎችንና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ለማቅረብ አልተቻለም፡፡

በምክር ቤቱ የአሠራርና ሥነ ምግባር ደንብ የምክር ቤቱ ውይይቶች ለጋዜጠኞች ክፍት እንደሚሆኑ፣ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ዝግ ሊሆን እንደሚችል ይገልጻል፡፡ ነገር ግን ይህ ውይይት በምን ምክንያት ዝግ ሊሆን እንደቻለ ለማወቅ አልተቻለም፡፡ ይሁን እንጂ በዝግ የተካሄደውን የምክር ቤቱን ውሎ የመንግሥት የመገናኛ ብዙኅን ከምክር ቤቱ በደረሳቸው መግለጫ መሠረት አቅርበውታል፡፡

Ethiopia Reporter

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: