በኤርትራ የወታደሮች አመፅ ቆመ

ያመፁ የኤርትራ ወታደሮች የማስታወቂያ ሚኒስቴሩን ለአንድ ቀን ከተቆጣጠሩ በኋላ ለቅቀው መውጣታቸው ተዘግቧል፡፡
ወደ አንድ መቶ እንደሚሆኑ የተነገረው ወታደሮች ወደ ደቡብ የጦር ሠፈራቸው የተመለሱት ከፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

ዛሬ አብዛኛውን ቀን ዝግ ሆኖ የዋለው የሃገሪቱ ቴሌቪዥን ጠፍቶ የዋለበትን ምክንያት ሣይናገር ምሽት ላይ መደበኛ ፕሮግራሙን ቀጥሏል፡፡
የቴሌቪዥን ጣቢያው ድንገት ከመቋረጡ በፊት አንባቢው ሕገመንግሥቱ እንዲከበር እና የፖለቲካ እሥረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ መግለጫ ያነብብ እንደነበረ ታውቋል፡፡

ስድስት ሚሊየን ሕዝብ ባላት ኤርትራ ከአምስት ሺህ እስከ አሥር ሺህ የፖለቲካ እሥረኞች ወህኒ ቤት ውስጥ እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ቢሮ ገልጿል፡፡

እሥረኞቹ ዛሬ (ሰኞ) ረፋዱ ላይ በብረት ለበስ መኪና መምጣታቸውንና ቅሬታዎቻችን ናቸው የሚሏቸውን ጉዳዮች ዝርዝር ይዘው እንደነበረ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ብዙ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሠራተኞች አመልክተዋል፡፡

የወታደሮቹ ጥያቄ ምን እንደነበረ እና አመፁ በምን እንደተፈታ ለጊዜው የተገኘ  ዝርዝር መረጃ የለም፡፡

አሥመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ አሥመራ ከተማ ውስጥ ከሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ አውጥቷል፡፡

የኤምባሲው መግለጫ የሚናገረው በአንዳንድ የዋና ከተማይቱ አካባቢዎች ወታደሮች በብዛት እየታዩ መምጣታቸውን ዲፕሎማቶች መናገራቸውን ነው፡፡

በሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ከተገነጠለችበት ጊዜ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ መንበሩን እንደተቆናጠጡ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ኤርትራ ለውጭው ዓለም በአመዛኙ ዝግ የሆነችና በጠንካራ እፍኞች ተጨብጣ የሆነች ሃገር እንደሆነች ይነገራል፡፡

ዛሬ ስለተፈጠረው አጋጣሚ የመንግሥቱን አስተያየት ለመጠየቅ ስልክ በተደጋጋሚ ቢደወልም ባለሥልጣናቱ ስልኮቹን ሳያነሱ ቀርተዋል፡፡

ኤርትራ ሶማሊያ ውስጥ የሚንቀሣቀሱ አማፂያንን ታስታጥቀለች፤ ትረዳለች በሚል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዛሬ ሦስት ዓመት አካባቢ – እአአ በ2009 ዓ.ም ማዕቀብ እንደጣለባት ይታወሣል፡፡

voaamharic

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: