የመተማ ወረዳ አስተዳዳሪና የመተማ ከተማ የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊን ጨምሮ 18 ሰዎች በቦምብ ጋይተዋል

(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው ጃንዋሪ 13 ቀን 2013 ዓ.ም በመተማ የወረዳው አስተዳዳሪ፣ የከተማው የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የከተማው የአቢሲኒያ ባንክ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅን ጨምሮ 18 ሰዎች በመኪና ላይ በተጠመደ ቦምብ ሕይወታቸው ወዲያዉኑ ሲያልፍ ሌሎች 4 ሰዎች መቁሰላቸውን ኢዩኤፍኤፍ ቢያሳውቅም መንግስት ዜናውን  ላፉት 17 ቀናት እንዳልዘገበውና ምንም አይነት መረጃ እንዳላወጣ ምንጮች ገለጹ። ከዚህ ቀደም በደብረማርቆስ፣ በአዲግራት በአዲግራት እና በተለያዩ ከተሞች እርምጃዎችን እየወሰደ የሚገኘው የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይል (Ethiopian Unity and Freedom Force – EUFF) ለዚህ የቦምብ ጥቃት ኃላፊነቱን መውሰዱን የደረሱን መረጃዎች አመልክተዋል።

በዚህ ጥቃት አቶ ተስፋ (የአባታቸውን ስም እያጣራን ነው) – የመተማ ወረዳ አስተዳዳሪ፤ እንዲሁም  አበበ ወርቁ – የመተማ ወረዳ የብ አዴን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የተባሉት በአውቶቡሱ ውስጥ እንደተሳፈሩ የጋዩ ሲሆን የአቢሲኒያ ባንኩ ሥራ እስኪያጅ  ሙሉ ስም በማጣራት ላይ እንገኛለን። በተለምዶ “አባዱላ” እየተባለ በሚጠራው መለስተኛ አውቶቡስ ውስጥ ተጭነው በመተማ ሲሄዱ የተጠመደው ቦምብ እንደፈነዳ ያሳወቁት የዜና ምኝጮቻን ቦምቡ በተለምዶ እንጀራ በጨው በሚባለው የመተማ አካባቢ ፈንድቶ ወዲያውኑ አውቶቡሱ ሲጋይ ከተጫኑት 22 የኢሕአዴግ የኮር አባላትና ደጋፊዎች  ውስጥ አደገኛ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ወደ ህክምና ተልከዋል ሲሉ የኢዩኤፍኤፍ ምንጮች ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይል ከዚህ ቀደም በደብረማርቆስ እርስቤትን አጥቅቶ  17 የ እስርቤቱን  ጠባቂዎች መሞታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በአዲግራት እስቤት ቤትም ቦምብ በመጣል እስረኞች ለመሞታቸው ይኸው ኃይል ራሱን ተጠያቂ ማድረጉ ይታወሳል። ከዚህ ቀደም ይኸው ድርጅት “ከኢሕአዴግ  ሥርዓት ጋር አትተባበሩ የሚል ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ላልሰሙ ደጋፊዎች ክምር ድንጋይ የሚባለው አካባቢ የነዳጅ ዘይት ማጠራቀሚያ ማጋየቱና፤ እንዲሁምጨጨሆ ላይ ላይ ደግሞ አውቶቡስ ማቃጠሉ መዘገቡ አይዘነጋም። የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይል (Ethiopian Unity and Freedom Force – EUFF) በመተማ ይህን እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ለሕዝቡ ከመንግስት ጋር እንዳይተባበር፤ ይልቁንም ለነፃነቱ እንዲነሳ፤ ሲቀሰቅስ እንደነበር የሚገልጹት እነዚሁ ዘጋቢዎች ይህን አልሰማ ባሉት ላይ ነው እርምጃውን ሊወስድ የቻለው ብለዋል።

ከኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ኃይል ይህን መረጃ ካገኘን በኋላ ከመንግስት በኩል የሚሰጠንን ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

zehabesha

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: