የአቶ ጁነዲን ያለመከሰሰ መብት ያለመነሳት ጉዳይ ማነጋገሩን ቀጥሏል

ጥር ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከሁለት ሳምንት በፊት ያለመከሰሰ መብታቸውን ለማንሳት በአጀንዳ መልክ ለፓርላማ ቀርቦ የነበረውና ባልታወቀ
ምክንያት ፓርላማው እንዳይወያይበት በተደረገው የቀድሞ የኦህዴድ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር
አቶ ጁነዲን ሳዶ ጉዳይ _ሕግ አስፈጻሚው አካል አሁንም ዝምታን መምረጡ አነጋጋሪነቱ ቀጥሎአል፡፡
ፓርላማው ከሁለት ሳምንት በፊት ባቀረበው አጀንዳ የአንድ የም/ቤት አባል ያለመከሰሰ መብት ስለማንሳት በሚል
ለውይይት አጀንዳ መያዙን ካስታወቀ በኃላ በድንገት ስብሰባው ከተጀመረ በሁዋላ ለሌላ ጊዜ መተላለፉ በአፈጉባዔው
በኩል ተገልጾአል፡፡

የፓርላማው ምንጮች እንደገለጹት አጀንዳው በፓርላማው ከኦሮሚያ ደራ ወረዳ ተመራጭ የሆኑትን አቶ ጁነዲን ሳዶን
የሚመለከት ነበር፡፡

ሆኖም ባልታወቀ ምክንያት አጀንዳው እንዲያድር ከተደረገ በሃላ ላለፉት አስራአምስት ቀናት
በላይ ዝምታ መመረጡ የብዙዎችን ትኩረት መሳቡ ታውቋል፡፡

አቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤታቸው ወ/ሮ ሐቢባ መሐመድ አዲስአበባ ከሚገኘው ሳዑዲ ኤምባሲ ገንዘብና የተለያዩ
መጽሐፍትን ተረክበው ሲወጡ እጅ ከፍንጅ ከተያዙበት ከሐምሌ 9 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ከመንግስታዊ
ኃላፊነታቸውን በተጨማሪ በመስከረም ወር መጨረሻ የዓመቱ መደበኛ ሥራውን የጀመረው ፓርላማ ተገኝተው አያውቁም፡፡

ከባለቤታቸው ጥፋት ጋር ተያይዞ ከኦህዴድ አመራርነት ተገምግመው እንዲነሱ የተደረጉት አቶ ጁነዲን በጠ/ሚ
ኃይለማርያም አዲሱ ካቢኔም ተወግደው በአቶ ሙክታር ከድር መተካታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ባለቤታቸው በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ክሳቸውን እየተከታተሉ ቢሆንም ከሳዑዲ ኤምባሲ ጋር ከነበራቸው ግንኙነት ጋር
በተያያዘ የምዋች እናታቸውን ኑዛዜ ለማስፈጸም የገንዘብ ዕርዳታ የጠየቁት ራሳቸው መሆናቸውን በመግለጽ ባለቤታቸው
በጉዳዩ እጃቸው እንደሌለበት በይፋ ቢናገሩም እስካሁን የተጠየቁበት ሁኔታ አለመኖሩ የህግ ሥርዓቱን ፍትሐዊነት
ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል፡፡

ፓርላማው ያለመከሰሰ መብታቸውን ለማንሳት ያደረገው ሙከራም የከሸፈበት ምክንያትም ለብዙዎች እንቆቅልሽ እንደሆነ ነው፡፡
በተያያዘም ነሐሴ 14 ቀን 2004 ዓ.ም ባለቤታቸውን አቶ መለስ ዜናዊን በድንገተኛ በሞት ያጡት ወ/ሮ አዜብ
መስፍን ከሐዘናቸው ካገገሙም በሃላ በፓርላማ ውስጥ ተገኝተው እንደማያውቁ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

ፓርላማው በ3ኛ ዓመት የስራ ዘመኑን በመስረም ወር መጨረሻ ጀምሮ እስካሁን መደበኛ ስብሰባዎችን እያስተጎጎለም
ቢሆን 15 መደበኛ ስብሰባዎችን ያካሄደ ቢሆንም የፓርላማው አባል የሆኑት ወ/ሮ አዜብ በአንዱም ስብሰባ ላይ
አልታዩም፡፡

እንደ  ምንጮቻችን ገለፃ አቶ መለስ ዜናዊ በሕወት በነበሩበት ጊዜ በቁም የተነሱትን ፎቶግራፍ ሁሉም አባላት
ሊያዩት በሚችሉበት ሁኔታ ፊት ለፊት የተሰቀለ ሲሆን ይህ ፎቶ በትልቁ ፊት ለፊት መሰቀሉ በብዙዎቹ የፖርላማ  አባለት ዘንድ አሁንም ፖርላማውን እየመሩ ያሉት እርሳቸው እንደሆኑ የሚያሳስብ መንፈስ ፈጥሮባቸዋል::

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: