ሰበር ዜና ፡ የኤርትራ ስደተኞች በአፍሪካ ኅብረት ጽሕፈት ቤት ደጃፍ የተቃውሞ ሠልፍ አደረጉ

ቁጥራቸው ከ400 እስከ 500 የሚሆኑ የኤርትራ ስደተኞች ጥር 23 ቀን 2005 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ጽሕፈት ቤት ደጃፍ የተቃውሞ ሠልፍ አድርገዋል፡፡

በአስመራ መንግሥት የግፍ አገዛዝ ላይ የኅብረቱ አባል አገሮች ተመሳሳይ አቋም በመያዝ ፖለቲካዊ ዕርምጃ ይወስዱ ዘንድ ለመማፀን የተሰበሰቡት የኤርትራ ዜጎች፣ በስደት በአዲስ አበባ ከተማና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚኖሩ ናቸው፡፡

ላለፉት ሃያ ዓመታት የኤርትራ ሕዝብ በዲሞክራሲና በመልካም አስተዳደር እጦት ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ መኖሩን፣ የአቶ ኢሳያስ መንግሥት በተያያዘው አምባገነናዊ ሥርዓት ብዙ ዜጎች ለሞት፣ ለማያባራ ስደትና እንግልት መጋለጣቸውን የሠልፉ አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡

ለደኅንነቱ በመስጋት ‹‹ጆን›› በሚል መጠሪያ ስሙ እንዲታወቅ የፈለገው የሠልፉ ዋና አስተባባሪ ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ የአፍሪካ ኅብረትም ሆነ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ሌሎች ዓለም አቀፋዊ ተቋማት በኤርትራ መንግሥት ላይ ተመሳሳይ አቋም ቢኖራቸውም፣ ከተያያዘው አጥፊ ጉዞ የሚገታው ምንም ዓይነት ዕርምጃ ባለመውሰዳቸው ይህንን ሠልፍ ለማዘጋጀት እንደተገደዱ ይገልጻል፡፡ ‹‹እነሱ ድምፃችንን ሰምተው አፋጣኝ መፍትሔ ባይወስዱም እኛ ባለን አቅም ሁሉ ከመጮህ ወደ ኋላ አንልም፤›› የሚለው ጆን፣ ‹‹በሃያኛው የአፍሪካ ኅብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ተገኝተን ጩኸታችንን ማሰማቱ የተሻለ አጋጣሚ መሆኑን ስለተገነዝብን ነው የወጣነው፤›› በማለት አስተያየቱን ለሪፖርተር ገልጿል፡፡

እስካሁን ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ጋር ምንም ዓይነት ውይይት አለማድረጋቸውንና በዚህም ቅር መሰኘታቸውን የገለጹት ሠልፈኞቹ፣ ተስፋ ባለመቁረጥ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን እንደሚያደርጉ አስረድተዋል፡፡

Ethiopian Reporter

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: