የጎንደር ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ጥር ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም


ኢሳት ዜና:-ወደ አንድ ሺ የሚጠጉ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ዛሬ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ በትናንትናው እለት በደህንነት ሀይሎች ታፍነው የተወሰዱት 2ቱ ጓደኞቻቸው የት እንዳሉ ዩኒቨርስቲው እንዲያሳውቃቸው ጠይቀዋል።

የዩኒቨርስቲው አስተዳዳሪዎች ከተማሪዎች ለቀረበው ጥያቄ ” ተማሪዎቹ በደህንነት ሀይሎች ተፈልገው የተወሰዱ በመሆኑ እኛ ምንም ማድረግ አንችልንም፣ ለወደፊቱም የፍርድ ቤት ማዘዣ ይዘው ከመጡ አሳልፈን እንሰጣለን” በማለት መልስ መስጠታቸው ታውቋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተሳተፉ ተማሪዎች እንደገለጡት በሙስሊም ተማሪዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ እየጨመረ በመምጣቱ ትምህርታቸውን ተረጋግተው ለመማር አልቻሉም።

በደህንነት ሀይሎች የተወሰዱት ሰይድ እና ኡመር የተባሉት ተማሪዎች በዚህ አመት ይመረቃሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር። በሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት እየጨመረ መምጣቱን መዘገባችን ይታወሳል።

በተመሳሳይ ዜና በሐረር ኢማን መስጂድ ዘበኛ የነበሩት ስማቸው ለጊዜው ያልታወቀው ግለሰብ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ታውቋል። ግለሰቡ ከመገደላቸው በፊት በአካባቢው መብራት ጠፍቶ የነበረ ሲሆን፣ ሁኔታው ከተረጋጋ በሁዋላ መብራት ተመልሶ መምጣቱ ታውቋል።

መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን የሰጠው መልስ የለም።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: