በጎንደር ከተማ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን ፖሊስ አመነ

በጎንደር ከተማ የካቲት 6 ቀን 2005 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር የከተማዋ ነዋሪዎች ለፍኖተ ነፃነት አሳወቁ፤ ፓሊስም የተኩስ ልውውጥ መሰማቱን አምኗል፡፡ እንደአካባቢው ምንጮቻችን ጥቆማ ከሆነ በዕለቱ የተደረገው የተኩስ ልውውጥ ምክንያት ምን እንደሆነ ባይታወቅም በስፍራው ግን በርካታ የፖሊስ ኃይሎች ሲታኮሱ እንደነበር መታዘባቸውን በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡
በዕለቱ ስለተፈጠረው ተኩስ ልውውጥ የአካባቢው 2ኛ ፖሊስ ጣቢያን መረጃ ብንጠይቅም የተኩስ ልውውጥ መደረጉን አምነው ጉዳዩ ገና እየተጣራ ስለሆነ ዝርዝር ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ የዕለቱ የመረጃ ክፍል ባለሙያ ገልፀውልናል፡፡ ዜናው እስከተዘገበበት ጊዜ ድረስ በተደረገው የተኩስ ልውውጥ በሰው ላይ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ ለማወቅ አልቻልንም፡፡

fnotenetsanet

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: