የሶማሊ ልዩ ሚሊሺያዎች በነዋሪዎች ላይ የፈጸሙትን አሰቃቂ ግድያ ኢሳት ይፋ አደረገ

 

የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በምእራባዊያን አቆጣጠር ማርች 16፣ 2012 በኢትዮጵያዋ የሶማሊ ክልል ፣ በጋሻሞ ወረዳ በክልሉ መንግስት የሚተዳዳሩት ልዩ ሚሊሺያዎች አንድ ወጣት ይገድላሉ። የወጣቱን መሞት ተከትሎ ከወረዳው ህዝብ የተውጣጡ ሰዎች ” አሁንስ በቃ ” በማለት ገዳዩን የሚሊሺያ አባል ተከታትለው  ይገድሉታል። የልዩ ሚሊሺያ ሀይሉ አባላት በተደጋጋሚ

ወደ አካባ በማግስቱ ማርች 17፣ ከ2 ሺ በላይ የሚሆኑ ልዩ የሚሊሺያ አባላት ወደ ወረዳው ተመልሰው በመሄድ ሰዎችን ከቤት እያወጡ ሰዎችን ገደሉ። ቢው በመሄድ ነዋሪዎችን ሲገድሉ፣ ሴቶችን ሲደፍሩና ንብረት ሲዘርፉ መቆየታቸውን የአካባቢው  ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል። “ህዝቡ በቃን” ብሎ እንዲነሳ ያደረገውም የግፉ ጽዋ ሞልቶ በመፍሰሱ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።

 

የአይን እማኞች በፎቶግራፍ አስደግፈው በላኩት መረጃ ከቤታቸው እየተለቀሙ የተገደሉት ሰዎች ብዛት 23 ነው። የልዩ ሀይሉ ድርጊት ያስቆጣው የወረዳው ነዋሪ መሳሪያ አንስቶ ከልዩ ሀይሉ ጋር መታኮስ በመጀመሩ፣ 17 የልዩ ሀይል የሚሊሺያ አባላት ተገድለዋል። የህዝቡ ቁጣ ያስፈራቸው የልዩ ፖሊስ አባላት አካባ
ቢውን ለቀው ወጥተዋል። ይሁን እንጅ ውጥረቱ አሁንም ድረስ እንዳለ የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

በፎቶአንድ ላይ እንደሚታየው ነዋሪው ፊቱ እና እጆቹ አካባቢ በጥይት ተመትቷል፤ ፊቱ እና እጆቹ አካባቢም በሳት ተቃጥሏል። በፎቶግራፍ ሶስት የሚታየው ደግሞ የአካካቢው ሰው በልዩ ሚሊሺ የተገደለውን ለመቅበር ጉድጓድ ሲቆፍር ነው።

በፎቶግራፍ አራት ላይ ደግሞ የልዩ ሚሊሺ አባሉ ከተገደለ በሁዋላ ህዝቡ አስከሬኑን ለመቅበር ጉድጓድ ሲቆፍር ይታያል። በፎቶ ግራፍ አምስት ላይ አንድ ወጣት በጎኑ እንደወደቀ ይህን አለም ተሰናብቷል። በፎቶ ግራፍ  ስድስት ላይ ደግሞ ሁለት ነዋሪዎች ግንባራቸው ላይ ተመትተው  ወድቀዋል።

 

በፎቶግራፍ 7 ላይ የሚታየው ደግሞ አንድ ጎልማሳ በጥይት ከተማ በሁዋላ ነዳጅ ተደፍቶበት ይታያል። በፎቶግራፍ ስምንት ላይ የተቆራረጠ የሰው አካል የሚታይ ሲሆን፣ በርካታ ጃኬቶችም ይታያሉ። በፎቶግራፍ ዘጠኝ ላይ ደግሞ የወረዳው ህዝብ  ሟቾችን ሲቀብር፣ እንዲሁም ጉድጓድ ውስጥ የገቡ አስከሬኖች ይታያሉ።

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚገልጡት ልዩ ሚሊሺያ የሚባሉት ሁሉም ከኦጋዴን ብሄረሰብ የተውጣጡ ሲሆን፣ ጉዳቱ የደረሰባቸው ደግሞ የኢትዮጵያ ሶማሊ የጦርነት ቀጣና ተብሎ በመከለሉ አንድም ጋዜጠኛ ወይም የሰብአዊ መብት ድርጅት ወደ አካባቢው በመሄድ በክልሉ ያለውን ችግር ለማጣራት አልቻለም። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሺን በአካባቢው ገለልተኛ አለማቀፍ አጣሪ ቡድን እንዲላክ ቢወስንም፣ ውሳኔውን በኢትዮጵያ መንግስት እምቢተኝነት የተነሳ እስካሁን ተግባራዊ ለማድረግ አልተቻለም።

የኢሳቅ ጎሳ አባላት ናቸው። ገዢው ፓርቲ በክልሉ ያለውን ችግር ለመቆጣጠር ከአቅሙ በላይ እየሆነ ሲመጣበት ሁለቱ ጎሳዎች እርስ በርስ እንዲጋጩ ማድረጉን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ከ7 አመታት በፊት በሶማሊ ክልል የሚካሄደው ጦርነት በሁለት ሳምንታት ውስጥ ይጠናቀቃል በማለት ለፓርላማ ተናግረው እንደነበር ይታወሳል።

በጋሻሞ የተፈጸመውን እልቂት በተመለከተ የኢትዮጵያን መንግስት አስተያየት ለመጤቅ ሙከራ ብናድርግም ሊሳካልን አልቻለም።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: