“መንግስት” የኤሌክትሪክ ሃይል እጥረት ይከሰታል አለ

ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማትን ለማፋጠን እያደረገች ባለው ጥረትና በሌሎች ኢኮኖሚያዊ ክስተቶች የተነሳ በቀጣዩ ዓመት ቢያንስ እስከ 200 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት እንደሚከሰት ሪፖርተር ከመንግስት ያገኘውን ማስረጃ በማጣቀስ አስታወቀ።

ሒላሪ ክሊንተን በአዲስአበባ ለአፍሪካ መሪዎች “በሻማ” ንግግር ሲያደርጉ

ለጅቡቲ ኤሌክትሪክ በመሸጥ ላይ የሚገኘው መንግስት ይከሰታል ያለውን እጥረት ችግር ከመፍጠሩ በፊት ከወዲሁ ዝግጅት ለማድረግ የመረጠው የጂኦተርማል /የእንፋሎት/ ሃይልን መጠቀም ነው። እየተሰሩ ያሉት አዳዲስ የሃይል ማመንጫዎች በሚቀጥለው ዓመት ስለማይጠናቀቁ ፊቱን ወደ ጂኦተርማል ሃይል ግንባታ ያዞረው መንግስት ብድር እንደሚያፈላልግም ሪፖርተር አመልክቷል።

በመሆኑም እጥረቱን ለመቅረፍ በሌላ ወጪና ጊዜ ቆጣቢ አማራጭ ላይ መተኮር እንዳለበት በመንግሥት የተቀመጠው ውሳኔ ያመለክታል፡፡ በአማራጭነት ከተወሰዱት በፍጥነት ሊደርሱ ከሚችሉ መፍትሔዎች መካከል የጂኦተርማል (እንፋሎት) ኤሌክትሪክ ኃይል ሲሆን፣ በዚህም ሥራ ላይ የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ በመሥራት ችግሩን የመቅረፍ ኃላፊነት እንደተሰጠው የሪፖርትር ዜና ያስረዳል።

የሃይል እጥረትና መቋረጥ እንግዳ ላልሆነበት ህዝብ አስቀድሞ ይህንን መሰሉ መግለጫ መስጠት ትርጉም ዓልባ እንደሆነ የሚጠቁሙት የሕዝብ አስተያየቶች በአምስቱ ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ኢህአዴግ ከኢትዮጵያውያን ይልቅ ጎረቤት አገሮች በኃይል አቅርቦት ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረጉ የዕቅዱ ከጅምሩ መሳካት አመላካች ነው በማለት የኢህአዴግን ‹‹የጽድቅ›› ሥራ ‹‹ያወድሳሉ››፡፡ ሥልጣን በተቆጣጠሩ ወቅት በቀጣይ 10ዓመታት ለኢትዮጵያ ያላቸው ህልም ምን እንደሆነ ተጠይቀው ህዝቡን በቀን ሦስት ጊዜ መመገብ እንደሆነ የተናገሩት ‹‹ባለራዕዩ›› መሪ ግልገል ጊቤ በተመረቀ ሰሞን ሻማ በኤሌክትሪክ መቋረጥ ለሚከሰት ችግር ሳይሆን ለልደት ብቻ እንደሚበራ በመግለጽ ‹‹ውርሳቸውን (ሌጋሲያቸውን)›› ትተው አልፈዋል ።

goolgule

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: