የሽግግር ምክር ቤቱ 2ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አደረገ

የካቲት ፩፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ከፌብርዋሪ 22 እስከ 24 ቀን 2013 በአሌክሳንድሪያ ቨርጂኒያ በሚገኘው ጽህፈት ቤቱ 2 ኛ ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዶ በጉባኤው በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ  ውይይት በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉን ገለጠ

ምክር ቤቱ ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ ” ጉባኤው የስራ አስኪያጅ፥ የኦዲተርና የአካባቢ ምክርቤቶች ሪፖርቶችን አዳምጦና ተወያይቶ ማጽደቁን” ጠቅሷል።

ጉባኤው የምክር ቤቱ የመተዳደሪያ ደንብ ላይ ተወያይቶ ማሻሻያዎች ማድረጉን፣ የሽግግር ምክርቤቱ ከሌሎች የፖለቲካና ሲቪክ ማህበራት ጋር እያደረገ ስላለው ትብብር ጉባኤው የቀረበለትን ሪፖርት አድምጦ  የተጀመረውን አበረታች ጥረት የምክር ቤቱ አመራር እንዲቀጥልበት በሙሉ ድምፅ ተስማምቷል።

የሽግግር ምክርቤት ምንድነው የሚለው ጥያቄ በአንዳንድ ወገኖች ዘንድ ብዥታን መፍጠሩን የገለጸው ምክር ቤቱ ፤ “የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክርቤት የወያኔኢህአዴግን ጸረ-ኢትዮጵያ አገዛዝና የዘረኝነት ስርዓት አስወግዶ የኢትዮጵያ ህዝብ በነጻና ፍትሃዊ ምርጫ በመረጠው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመተካት የሚታገል ህዝባዊ የፖለቲካ ተቋም ” መሆኑን ገልጿል።

የሽግግር ምክር ቤቱ መሰረታዊ ዓላማ “የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት፥ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ለማስከበር ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ቅድመ ሁኔታዎችን ማመቻቸት” መሆኑን ፣  የትግል ስልቱም ሰላማዊ ህዝባዊ እምቢተኝነት መሆኑን ጉባኤው ወስኗል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሽግግር ምክር ቤቱ የሽግግር መንግስት አለመሆኑን ያብራራው መግለጫው፣  የሽግግር መንግስት የትና እንዴት እንደሚቋቋም ህዝባዊ  ምክክር ተደርጎበት የሚወሰን መሆኑንም ጠቅሷል።

መግለጫው በመጨረሻም ” በሀገራችን ያለውን ጸረ-ኢትዮጵያ፥ ጸረ-ህዝብና ጸረ-ዴሞክራሲ የሆነውን መንግስት አስወግዶ ወደ ህዝባዊ ስርዓት ስለመሸጋገር የሚመክር ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ ጉባኤ በፊታችን ሀምሌ  2013 ወር ላይ በዋሽንግተን ዲሲ ለማዘጋጀት መውሳኔ መተላለፉን” ገልጿል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: