የመቀሌ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገለጡ

የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- በመቀሌ ከተማ የላጪ ሰፈር ነዋሪዎች በውሀ እና በመብራት እጦት ለ ዓመታት እየተንገላታን እንገኛለን ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል

የላጪ ሰፈር ነዋሪዎች ለኢሳት ዘጋቢ  እንደገለፁት ማዘጋጃ ቤቱ በሰጣቸው ቦታ ቤት ሠርተው ከገቡ ሁለት ዓመታት የተቆጠሩ ቢሆንም፤እስካሁን ድረስ ውሀ እና መብራት ሊገባላቸው አልቻለም።

ችግራቸውን በተደጋጋሚ ለሚለከተው የመንግስት አስተዳደር ቢያቀርቡም ምንም ዓይነት መፍትሔ ሊያገኙ እንዳልቻሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

በመቀሌ ከፍተኛ ንፁህ መጠጥ ውሀ ችግር እንዳለ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።

ብዙዎቹ የከተማዋ ነዋሪዎች በንፁህ የመጠጥ ውሀ እጦት በሚሰቃዩበት ጊዜ የ ኢፈርት ሀላፊዎች እቤታቸው ድረስ የውሀ ማጣሪያ እንደገባላቸው መዘገባችን ይታወሳል።

እንዲሁም ከፍተኛ የህወሀት ሹማምንት ከከተማው ወጣ ብሎ በሚገኝ ነፋሻማ ቦታ ላይ በብዙ ሚሊዮን ብር ወጪ የተሠሩ ቬላዎችን ያቀፈ አፓርታይድ የተሰኘ እንደገነቡ በተደጋጋሚ መዘገቡ አይዘነጋም።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: