የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንት በዋስ ተፈቱ

“ዜብራ” ላይ ሰው ገጭተው ሸሽተዋል በመባል ለ10 ቀናት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የቆዩት የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ፀሐይ ሽፈራው በዋስ ተፈቱ፡፡ ወደ ውጭ አገር እንዳይጓዙ ታግደዋል፡፡ በትናንቱ የቂርቆስ ምድብ ችሎት፤ ፖሊስ የአንድ ምስክር ማስረጃ ውስብስብ ሁኔታ ፈጥሮብኛል ብሏል፡፡ አቶ ፀሐይ የተጠረጠሩበት ጉዳይ የዋስ መብት የማያሰጥ ቢሆንም በዋስ ከተለቀቁ ግን ከአገር እንዳይወጡ ለሚግሬሽን ትእዛዝ ይሰጥልኝ ብሏል – ፖሊስ፡፡ የሥራቸው ፀባይ ከአገር የሚያስወጣ በመሆኑ ከአገር እንዳይወጡ እግድ እንዳይሰጥ የተከራከሩት የአቶ ፀሐይ ጠበቆች በበኩላቸው፤ ሌላ አማራጭ እንዲሰጥ ወይም ለፖሊስ አሳውቀው እንዲወጡ እንዲፈቀድ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ ዳኛው የግራ ቀኙን ከሰሙ በኋላ ተጠርጣሪው በ50 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁና ከአገር እንዳይወጡ ለሚግሬሽን እንዲጻፍ አዘዋል፡፡
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: