የወያኔው ኢህአዴግ እየተተራመሰ ነው፣ ድርጂት ተብየው እንደ ድርጅት አንድ ሆኖ መውጣት እንደተሳነው ተዘገበ

በተለይም የዘረኛው አገዛዝ አምባገነን መለስ ዜናዊ ከሞተ ወዲህ በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የተከሰተው የውስጥ ሽኩቻ ከእለት እለት እየጨመረ መሄዱ በተከታታይ ሲዘገብ የቆየ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ይሄው ትርምስ ከሰሞኑ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ በመድረሱ የወያኔው ኢህአዴግ እንደ ድርጅት አንድ ሆኖ መውጣት እየተሳነው እንደሆነ ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ዘገባ አመለከተ።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት እንደዘገበው በህወሀት ውስጥ ሁለት ቡድኖች ድርጅቱን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ መጀመራቸው ከተዘገbe ከወራት በሁዋላ ችግሩ ከመቃለል ይልቅ እየጨመረ መምጣቱን አንድ የቀድሞ የህወሀት ነባር ታጋይ ለኢሳት ዘጋቢ ገልጸዋል ብሏል።

እንደ ኢሳት ዘገባ ነባር ታጋዩ፤ በስብሀት ነጋ በኩል ባሉ ሰዎች ወደ ድርጅቱ እንዲመለስ ጥሪ ቀርቦለት እንደነበር መጥቀሱንና ፤ እርሱ ግን አሻፈረኝ ማለቱን፣ እንዲሁም በድርጅቱ ውስጥ የሚታየው ክፍተት ለአደባባይ ባይበቃም፣ ህዝቡ የሚያየውና እየተነጋገረበት ያለ ጉዳይ መሆኑን ገልጹዋል ብሏል።

በተያያዘ መልኩም በኦህዴድ በኩል ከመለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ የታየው ክፍተት እየሰፋ እንጅ እየጠበበ ሲሄድ አለመታየቱ ተገልጿል። በተለይም በከፍተኛ ህመም የሚሰቃየው ፕሬዚዳንቱን አለማየሁ አቶምሳን ለመተካት ቢፈለግም፣ በእርሱና በአፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ ደጋፊዎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ሌላ ፕሬዚዳንት ለመሾም ሳይቻል በመቅረቱ አለማየሁ በስልጣን ላይ እንዲቆይ መደረጉ ተገልጿል።

የወያኔው አገዛዝ አቀንቃኝ የሆነው ሪፖርተር ጋዜጣ በትናንትናው እለት እትሙ ባወጣው ዘገባ ደግሞ ኦህዴድ የካቲት 20 ቀን 2005 ዓ.ም. ጠቅላላ ጉባዔውን ለማድረግ የተሰበሰበ ቢሆንም ፤ያልተጠበቁ አጀንዳዎች በመቅረባቸው፤ ለኢሕአዴግ በሚቀርበው የሁለት ዓመታት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ብቻ በመወያየት ጉባዔውን ለሚቀጥለው ሳምንት አስተላልፎአል ብሏል። ጋዜጣው አክሎም የኦህዴድ አባላት፤ ድርጅታቸው የተለያዩ ችግሮች ስላሉበት ጉዳዩ በአጀንዳ ተይዞ ውይይት እንዲደረግበት ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ፣ የሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴ ሰብሳቢዎች በድጋሚ ሌላ ስብሰባ እንደሚደረግና በዚያ ስብሰባ ላይ “አሉ” የተባሉ ችግሮችን በማንሳት መወያየትና መፍታት እንደሚቻል ቢናገሩም፣ ስምምነት ላይ አልተደረሰም ብሎአል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: