ሠማያዊ ፓርቲ የገቢ መሰባሰቢያ የራት ምሽት ዝግጅት እንዳያደርግ ተደረገ

በሀገሪቱ ሕገ መንግሥትና በፓርቲዎች መቋቋሚያ አዋጅ መሠረት በሕጋዊ መንገድ ተደራጅቼ የምገኝ ፓርቲ  ሆኖ ሳለ የገቢ ማስባሰቢያ  ራት ግብዣ አዘጋጁቼ ተከላከልን ሲሉ የፓርቲው ፕሬዝዳንት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት አስታወቁ፡፡ ኢ/ር ይልቃል መጋቢት 2 ቀን 2005 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ለጋዜጠኞች እንዳስታወቁት ‹‹ ከፍተኛ የገንዘብ ወጪ አውጥተን የካቲት 30 ቀን 2005 ዓ.ም በዋቤ ሸበሌ ሆቴል ያዘጋጀነው የራት ዝግጅት እንዳናከናውን ተከልክለናል›› ሲሉ አስታወቀዋል፡፡

የፓርቲው ፕሬዝዳንት እንደተናገሩት ‹‹ ዝግጅቱን አጠናቀን ለማከናወን እንግዶች ወደ አዳራሹ በማስገባት ላይ ሳለን የሆቴሉ አስተዳዳሪ ልዑል በእደማርያም ከአቅሜ በላይ በሆነ ችግር ራት ዝግጅታችሁን ማድረግ አትችሉም፡፡ እንደ አንድ ነጋዴ ከዚህ በላይ የምላቸው ነገር የለም፤ እንግዶቻችሁን አሰናብቱ ብለውን መበትን ችለናል፡፡ ይህ የሚየሳየው በሀሪቱ ውስጥ ያለው የአፈና ሥርዓት ያለበትም ደረጃ ነው፡፡ መንግሥት ካለበት የአቅም መነስ የሚወሰደው እርምጃ ነው፡፡ የምርጫ ቦርድ ሕግ ከአባሎቻችንና ከደጋፊዎችን ገንዘብ እንድናሰባስብ ሕጉ ይፈቅድልናል፡፡ ገዢው ፓርቲ ግን ከሕግ ውጭ አፈና እየፈፀመብን ነው፡፡›› ሲሉ አማረዋል፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ ከዋቢሸበሌ ሆቴል አስተዳደር ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት መልስ የሚሰጠን ኃላፊ ባለመኖሩ አልተሳካም፡፡

269070_104712222960067_2836725_n

fnotenetsanet

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: