በፓትርያርኩ ምርጫ መንግስት ሙሉ በሙሉ እጁን አስግብቶ ነበር ተባለ

የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ 6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ ጋር በተያያዘ መንግስት እጁን ሙሉ በሙሉ አስገብቶ እንደነበርና ምርጫው ነጻ፣አሳታፊና ገለልተኛነት በሆነ መልኩ እንዳልተካሄደ ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡
የቀድሞ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ ለሶስት ዓመታት ያህል በውጪ አገር ካለው ስደተኛው ሲኖዶስ ጋር ሰላም ለመፍጠር ቀጥሎ የነበረው ጥረት እንዲከሽፍና የፓትርያርክ ምርጫው በተፋጠነ ሁኔታ እንዲካሄድ እንዲሁም መንግስት የሚፈልጋቸው ፓትርያርክ እንዲመረጡ በቀጥታና በተዘዋዋሪ በቤተክርስትያናቱ መሪዎች
ላይ የመንግስት አካላት ግልጽ ተጽዕኖ ሲያሳርፉ ቆይተዋል፡፡
በመንግስት በየትኛውም መዋቅር ውስጥ የለሁበትም የሚሉትና ድንገት እየተነሱ ያሻቸውን የሚናገሩት አቦይ ስብሃትን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ቤክርስትያኒቱን አባቶች በማንጓጠጥና በማዋረድ ሥራ ሆን ብለው በተከታታይ ያከናወኑ ሲሆን የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና የመንግስት የደህንነት ኃይሎች አባቶችን እግር በእግር በመከታተል፣የስልክ ግንኙነታቸውን በመጥለፍ፣በማስፈራራት ሒደቱ በሚፈልጉት መልክ እንዲሆን ሰፊ ሚና ተጫውተዋል፡፡
ከ53ቱ አገረ ስብከቶች ለመራጭነት የታጩ ሰዎችን ለአቡነ ማቲያስ ድምጽ እንዲሰጡ እስከማግባባት የዘለቀ ሥራ በይፋ ማከናወናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችንን አመልክተዋል፡፡
የመንግስት ኃሎች ከሕገመንግስቱ ድንጋጌ በተቃራኒ በሃይማኖት የውስጥ ጉዳይ ሊገቡ የፈለጉት ገዥው ፓርቲ ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር ካለው ከፍተኛ ፍላጎት ጋር የተገናኘ ሳይሆን አይቀርም።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ ከትላንት ጠዋት ጀምሮ 806 መራጮች ድምጽ የሰጡ ሲሆን ከሰዓት በኋላ በተደረገው ድምጽ ቆጠራ ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ በ500 ድምጽ የመጀመሪያውን ድምጽ በማግኘት 6ኛው ፓትርያርክ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኢህአዴግ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት አጥብቀው በመቃወም የሚታወቁት አባ አምሀ እየሱስ የፓትርያርኩ ምርጫ ” የመንግስት ምርጫ እንጅ የምእመናን ምርጫ አይደለም” ብለዋል

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: