እኛና እነሱ – የሁለት ሀገር ሰዎች ነን

ከሥርጉተ ሥላሴ 10.03.2013

እም! ብዬ እያማጥኩ ጀመርኩት።

eprdf leanders in ethiopia

(ፎቶ – ከኢትዮጵያ ከረንት አፊርስ ዲስከሽን ፎረም የተወሰደ)

እኛ ማነን? እኛ የተቀመምንበት ኢትዮጵያዊነት የሚያንገበግበን። ችግሯ – ችግራችን፤ ዕንባዋ – ዕንባችን፤ መከፈቷ – መከፈታችን፤ ጉስቁልናዋ – ጉስቁልናችን፤ አንገት መድፋቷ ሃዘናችን የሆነው በዬትኛውም ዓለም የምንገኝ ልጆቿ ነን። በወያኔ መዳፍ ውስጥ አሳሩን በማዬት የሚገኘው ከስሜን እስከ ደቡብ ጫፍ፤ – ከዱቡብ ጫፍ እስከ ምዕራብ ጫፍ፤ ከምዕራብ ጫፍ እስከ ምስራቅ ጫፍ የሚገኝ ህዝብ ለሀገሩ ልዩ መለዮችን የሆነው ሥጋና ደም ነን።

እነሱስ? „የደላው ገንፎ ያላምጣል“ እንዲሉ ከማህደረ – ኢትዮጵያዊነት ትንሽ ልቅላቂ ያልፈጠረላቸው፤ አለቶች … በዕንባ ላይ ይሾማሉ፤ ይሸለማሉ …. ልጆቻቸውን አንደላቅው ያሰተምራሉ፤ ሲሰኛቸው ውጬ ልከው ዶላር አፍሰው ያዝመነምናሉ።

ባይታዋሩ ወገናችን ደግሞ ዕጣ ፈንታው … ሥራ ፍለጋ በሺህዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን፤ በውሃ ጥም፤ በመንገድ ጉዞ አቅም በማነስ፤ በውሃ ሙላት፤ በጾታ ጥቃት፤ በቀጣሪ ዳባ እንደተበተነ ያልቃል፤ እንዲሁም ካሰቡት ሳይደርሱ የአሞራ እራት ይሆናል። በስደቱ በእሳት የሚቀቀሉት፤ ከፎቅ ተከስከስሰው የሚሞቱት፤ በጭንቀት በሽታ አብደው አድራሻቸው ጠፍቶ የሚቀሩትንማ ስሌትም አይገታውም። እንደ ጣሊያን በመሳሰሉት ሀገሮችም መንገድ ላይ ተዳዳሪ ወገኖቻችን በሚመለከት — ቤቱ ይቁጠረው።

ሞተን እያዩ ወደ ሞት ፊት ለፊት የሚገሰግሱ፤ በልተን እንሙት ብለው ከሞት ጋር የሚፋጠጡት ሴተኛ አዳሪ እህቶቻችን ቁጥርም ከሌሎች የችግሩ ሰለባ ከሆኑት ወገኖቻችን ቁጥር

Ethiopian girl holding baby gott

(ፎቶ – ከኢትዮጵያ ከረንት አፊርስ ሆም ፔጅ – ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል ከሰጠው መግለጫ ትርጉም – የተወሰደ)

ቢበልጥ እንጂ ከቶውንም አያንስም። ጧሪ ጠዋሪ አጥተው ቤት እንደ ተዘጋባቸው የሚያልፉት አዛውንታት በእርግማን ለወግ ሳናበቃቸው አፈር ራታቸው፤ ድንጋይ  ትራሳቸው ሆኗል። ሊለምኑ ያፈሩ አካሎቻችን ቁጥር የትዬለሌ ነው። ከመሬት የሚፈናቀሉ ወገኖቻችን ልጆቻቸውን ለመሸጥ ነፍሳቸው እንዲሰነብት ተሰልፈዋል …. ለመራራ ስንብት፤

የጥንተ – ጥዋቱ የአባት አደሩ ወግና ባህል ቀርቶ ዛሬ በገበሬው መንደር ሳይቀር ቡና እንኳን ብቻ – ለብቻእንደ አውሮፓ የሚጠጣበት ዘመን ተድርሷል። ለቡናውም የቡና ቁርስ አሯል። እንግዲህ እኛ የዚህ እርቃኑን – መለመላውን ያለ፤ ለዕለት ጉርስና ከፈን ያልበቃ፤ መጠለያ የሌለው ወገንተኛ ነን፤ ቀኑ እራሱ የተጋጠ የተመለመለ ነው የማረተበት!

እነሱ ደግሞ ለአንድ የምክትል ጠ/ሚኒስተር ቦታ ሶስት – ከዋናው ጋር በድምሩ አራት ሰው ይሾማሉ … አዎን! እኛ የወያኔ ሱፍ ለባሾች ወገንተኛ አይደለነም። የእነኝህ እንጂ ….

እነሱ — ያላጋጥሉ! ….

ይማግጣሉ! ….

በህዝብ የዕንባ ጥሪት ይቀብጣሉ!

በማናለብኝነት ቀፎ ሰረገላ ይዝመነማናሉ!

በፈጣሪ አምላክም ይሳላቃሉ። በሚፈርስ ገላ ላይ ሆነው ይደልቃሉ። „በሬ ሆይ! ሳሩን አዬህ እንጂ …. „ እንዲሉ። ይህም ያልፋል። የማያልፍ ነገር ያልተፈጠረብቻ ነው። በተፈጥሮ

EPRDF leaders in Ethiopia

(ፎቶ – ከከረንት ሆም ፔጅ „መሳቂያው ፓርላማ – ከአቤ ቶኪቻው መጣጥፍ የተወሰደ)

ሂደት ይጨበረባራሉ … መፈረሳቸውን ስተው — ይደንሳሉ — ሙጃ!

… እኛና እነሱ የማንገናኝ፤ ልንቀራረብም ከቶውንም የማንችል ነን። …. በዬትኛውም ዘመን በዬትኛውም ጊዜ የማንገናኝ … የሁለት ሀገር ሰዎች ነን። ምን ግዜም አዎን ምንግዜም እኛ እና እነሱ በዚህ ሚዛኑን ባልጠበቀ ተፈጥሮ፤ ሚዛኑን ባልወሰነ ውስጥነት ስለማንገናኝ እስከ ህልፈት ድረስ፤ በታሪክም የማንገናኝ ሰዎች ነን። ብንሞትም አጥንታችን ከክህደት አጥንት ጋር ከቶውንም እርቀ ሰላም የለውም።  – ኃራም!

ታዲያ የተከበርክ ወገናችን ሆይ! ይህ የረመጥ ዘመን፤ ይህ ዘመነ ፅልመት እንዲያከትም ምን ትመክራልህ?! ምን ታስባለህ?! … እንደ ትናንቱም ዛሬ ወጥተህ ወያኔን ጠቅጥቀኝ፤ ተርትረኝ፤ እረሰኝ፤ በራህብ ጨርሰኝ … በስጋት ክተፈኝ ብለህ ድምጽህን ትሰጣለህን? ወይንስ በቃኝን በድርጊት አስጊጠህ – አሻም ብለህ – ትቆርጣለህ?

ድንቁ ወገናችን … ሆይ! የቱ ነው ምርጫህ እና ውሳኔህ? … እንሆ ነገ ያለ በእጅህ – በአንተ መዳፍ ወስጥ  ነውና ወስንለት! በውሳኔህንም እንክርዳዱን ከስንዴ ለይበት። ስንት ጊዜ ምርጫ አዬህ ….?! ምን ተለውጦ አገኘኽው?! ከቶ ከራህብህ፤ ከመገፋትህ፤ ከመረገጥህ፤ ከመታሰረህ፤ ከመሰደድህ፤ ከሞመትህ ድነኃልን?!

የሚጎሰምልህ የስጋት ነጋሪት፤ የሚታወጅልህ የመንፈስ እስረኝነት፤ የሚነገረህ ዕብለት ስለመሆኑስ ታስተውለዋለህን? ማግኘቱ፤ በሥልጣን ማደጉ፤ በኑሮ መድላቱ – ልማቱ ከቶ ለአንተ poor ethiopia mothers and daughterለራህብህ፤ እጥፍ ብሎ እህል እውሃ ለሚለምነህ አንጀትህ ፤ የዕለት ከፈን ለሚማጸንህ አካልህ፤ መጠጊያ አጥቶ የነፍሳ – የውጪ – ግቢ ህቅታ ድምጽ ለሚያስተጋበው  ጥግ አልባው ሰውነትህ  ምኑ ነው? በተደሞ እሰሰው፤ በአርምሞ መርምረው … አንተ ለእነሱ ለጥጋበኞች ምናቸውም አይደለህም። ልንገር እነሱ ከአንተ ይልቅ — ትቢያን ያከብራሉ ….

ይሄውልህ — እንደለመደው ወያኔ — አዲሱን ጨዋታ ይዞ ኮሶን በማር ለውሶ፤ ዓይኑን በጥሬጨው አሽቶ ለአዲስ ምርጫ ምረጠኝ እያለህ ነው። ቅድመ መሰናዶው እያዬህው ነው። … ውሳኔህ፤ ድምጽህ  ——— ለልደትህ ወይንስ ለቅብረትህ ….?! ለዳግም ሞትህ ወይንስ ለትንሳዬህ? ብይንህን ስጥ። የሚዛንህ አድሎ ለደም ዕንባህ ይሁን። ይህ ልግጫ እስከ መቼ በልና አፋጣቸው! … በተናጠል አይደለም – በህብረት!  … አንተ ዕልፍ – እነሱ እፉኝ ናቸው። ባህሪያቸውም እንደ እፉንኝት ነው። ሲጠነሰሱ አዳርን ገደሉ። ሲወለዱ ደግሞ እናታቸውን … በላ!  እንደ እስልምና እምነት ወገንህ አንተም …. የልብህን ለማደረስ ተሰናዳ! ቁረጥ! — ቁርጥ ያጠግባልና …..

መሽቶ ሲነጋ –

ነግቶ ሲመሽ  — ላይነጋ

ቀናቶች ሲከታተሉ  — እያወጉ

ወራቶች ሲደራረቡ — እዬተዋጉ

ዓመታት እኛን ትተው ሲነጉዱ

ምዕተ ዓመታታ እኛን – እረስተው – በድልቂያ – ተዥጎርጉረው ተዥጎደጎዱ።

ሰማዩም በአርምሞ ሲመክር …

ምድርም ጥቅጣቃው በዛብኝ ብላ — በሰቀቀን — ስትጣራ ….

የኢትዮጵያ መከራ ይከማራል፤ ይደረደራል በበቀል – ሰቤጠራ።

! … የሃርነት ትግራይ ትል ፍልቶ – አፈልቶባት ….

በመታበይ ሲደነፋባት ….

መራራት …. ጎመዘዛት እማ እናታለም ….

የትናንትናዋ ቀለማም – ለምልም –

ጠራች — እሙ —  ለነፃነትህ  ብላ/ – ትመም! – ትመም!

ሃብተ – ንብረቷ

ጥሪተ  – ቅርሷ፣

ባህለ – ልማዷ

እምን!  አርግዞ – ይሄው – ፤ ትውፊቷ በዕብሪት በሙጃ ሰርክ ይመነጠራል

ያራል – ይከስላል፤ – ከወገን ጋር ይደለቃል – በመታበይ ይደቆሳል።

ሞልቶ ተትረፎ

የአሳር ጎርፍ አጎርፎ

አደራ ይጣራል

ድረሱልኝ ይላል።

እሷማ —- አሮባታል

ተደፍቶባት —-

ቀኑ —- መክኖባት

ሰቀቅን ተከዝኖባት

እህህ! ከትሞባት፤

ሞት – ነግሶባት

እስራት – ቀስሶባት

እም! እያጠደፈ – ተጭኗት

ትጣራለች እናት ቀኑ ጨልሞባት

ኑ! ትላላች አማ ሁሌም – መሽቶባት።

ወገኔ ሆይ! ልደትህን ለማቅረብ ቁልፉ ያለ በእጅህ ላይ ነውና በቃኝን ተክለህ አጽድቀው!

(በምፈልገው መልክ ገጠር ድረስ በመሄድ ፎቶዎቹን አጠናክራ ያመጣችልኝ  ሲዊዛዊ እህቴን … ከልብ አመሰግናታለሁ)

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

ECADF

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: