ኢትዮጵያ ሆቴል ፈርሶ ባለ 60 ፎቅ ሆቴል ሊገነባ ነው

823d7f7cd8e199f1a5c37ae82ff6053d_Lበመሀል አዲስ አበባ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንግዶችን እንዲያስተናግድ ከ50 ዓመታት በፊት የተገነባው የኢትዮጵያ ሆቴል ፈርሶ፣ በምትኩ 60 ፎቅ ያለው ሆቴል እንዲገነባ የአዲስ አበባ አስተዳደር ካቢኔ መወሰኑን ምንጮች ገለጹ፡፡

ካቢኔው ለሆቴል ፕሮጀክቱ 1,700 ካሬ ሜትር ተጨማሪ መሬት ፈቅዷል፡፡ መሬቱ የሚገኘው ኢትዮጵያ ሆቴል ካለበት ጀርባ ያሉ የንግድና መኖርያ ቤቶች ያረፉበት ነው፡፡ እነዚህ ቤቶች ፈርሰው ለፕሮጀክቱ እንዲውሉ ካቢኔው ውሳኔ ማሳለፉ ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ሆቴልን ከፕራይቬታይዜሽንና ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን በ94 ሚሊዮን ብር በመግዛት የራሱ ያደረገው በላይነህ ክንዴ ኢምፖርት ኤክስፖርት ኩባንያ ነው፡፡

ኩባንያው ኢትዮጵያ ሆቴልን እንደ አዲስ ለመገንባት ሁለት ቢሊዮን ብር በጀት መያዙን የሚያመለክት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ለከተማው አስተዳደር ማቅረቡን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተሰበሰበው በከንቲባ ኩማ ደመቅሳ የሚመራው የከተማው ካቢኔ የመጨረሻ ይሁንታውን ለፕሮጀክቱ ተግባራዊነት ሰጥቷል፡፡

ኢትዮጵያ ሆቴልን ጨምሮ ከአምስት በላይ ኩባንያዎችን በባለቤትነት የሚያንቀሳቅሱት አቶ በላይነህ ክንዴ፣ ከአስተዳደሩ ደብዳቤ ያልደረሳቸው በመሆኑ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ በመሀል አዲስ አበባ ከመከላከያ ሚኒስቴር አጠገብ የሚገኘው ኢትዮጵያ ሆቴል የአፍሪካ አንድነት እንግዶችን እንዲያስተናግድ በአፄ ኃይለ ሥላሴ መልካም ፈቃድ የተገነባ ነው፡፡

የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል እንዲያስተላልፍ በተቀመጠለት አቅጣጫ መሠረት ኢትዮጵያ ሆቴልንና የአዳማ ራስ ሆቴልን ለበላይነህ ክንዴ ኩባንያ በሽያጭ አስተላልፏል፡፡ ኩባንያው ሁለቱን ሆቴሎች የገዛው በ134 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ የኩባንያው ባለቤት በሁለቱም ሆቴሎች አዲስ የማስፋፊያ ዕቅዶችን በመንደፍ ለሁለቱም የከተማ አስተዳደሮች አቅርበው ማስወሰናቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ባለአምስት ፎቅ ከፍታ ያለው ኢትዮጵያ ሆቴል በዕድሜ ብዛትና በማኔጅመንት ችግር አገልግሎት አሰጣጡ እየተዳከመ መምጣቱ ይታወቃል፡፡ ሆቴሉ በመሀል ከተማ የሚገኝ በመሆኑና የአዲስ አበባ አስተዳደር ሥራና ኮንስትራክሽን ልማት ቢሮ ባወጣው ደረጃ ያረፈበት ቦታ ለረጃጅም ሕንፃዎች ብቻ የሚፈቀድ ነው፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ ከዚህ ሆቴል አጠገብ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአገሪቱ ረዥሙ የሚባለው ሕንፃ ለመገንባት ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡

በላይነህ ክንዴ በየዓመቱ ሰሊጥን ጨምሮ የተለያዩ የቅባት እህሎችን፣ ቡናና የቁም እንስሳት በመላክ ከ50 እስከ 60 ሚሊዮን ዶላር ያስገባል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የደረቅ ጭነት አገልግሎት የኮንስትራክሽን መሣርያዎች ኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ ኩባንያዎች ባለቤት ነው፡፡ በላይነህ ክንዴ ኩባንያ በቅርቡ ፀሐይ ኢንዱስትሪስ በሚሰኘው ኩባንያው በቃሊቲ ብረታ ብረትና በፀሐይ ኢንሹራንስ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰሱን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

Ethiopian Reporter

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: