የጨቋኝና አምባገነን ስርዓት ማሻሪያው የተባበረ ትግል ነው

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ( ሸንጎ ) በአገራችን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሕወሓት/ኢሕአዴግ አምባገነን መንግሥት የሚያካሂደውን የኃይል አገዛዝ በመቃወም በአገር ውስጥ በይፋ የሚንቀሳቀሱ 23 የተቃዋሚ ፓርቲዎች በጋራ ለመታገል የሚያሰችላቸው መግባባት ላይ መድረሳቸውን በመግለጽ ባወጡት መግለጫ እጅግ የተደሰተ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል።

ሸንጎው ከጥንስሱ ጀምሮ አንግቦ የተነሳው በሀገራችን ውስጥ ሰፍኖ የሚገኘውን አምባገነን ስርዓት በጋራ ትግል አሰወግዶ በምትኩ የዜጎች ሁለንተናዊ መብቶች የሚከበሩባት፣ የሕግ የበላይነት የሰፈነባት፣ እውነተኛ በሕዝብ ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እውን የሚሆንባትንና አንድነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው።

በድምሩ የአስራ አንድ ፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት እንዲሁም የታዋቂ ግለሰቦች ትብብር የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)፣ 23ቱ ድርጅቶች በጋራ ለመታገል በሚያሰችላቸው ተጨባጭ መግባባት ላይ መድረሳቸው እጅግ አበረታች እና ለትግሉም ተሰፋ ሰጪ ነው ይላል። ይህ አበረታች እርምጃም ይበልጥ እንዲጎለብትና በህዝባችን ላይ የተጫነውን የዘረኛነት፣ የከፋፋይነትና የአፈና ስርዓት ለማስወገድ እንዲበቃ በሚደረገው ትግል ሁሉ ከጎናቸው እንደምንቆም እናረጋግጣለን።

በየትኛውም ቦታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ይህንን አበረታታች ጅምር ወደተሻለ ደረጃ እንዲደርስ አሰፈላጊውን ትብብር ሁሉ እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናሰተላልፋለን።

በተደጋጋሚ እንደገለጽነው ትግሉ እረጅምና እልህ አስጨራሽ እንደሚሆን ሸንጎው አይዘነጋም። ሆኖም ግን በጋራ ቆመን ከታገልን የነፃነታችን ቀን እውን የሚሆንበት ጊዜ እጅግ እንደሚፋጠን ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ የለንም።

የፍራቻ ድባብን አስወግደን በተባበረና በተቀናጀ ትግል፤አንድነቷ የተጠበቀ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እንገነባለን!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: