የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያደርገውን ምርመራ አራዘመ

መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአለም ባንክ በሂውማን ራይትስ ወች የቀረበለትን ጥያቄ መነሻ በማድረግ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚከተለው ፖሊሲ የተነሳ ሰብአዊ መብቶች መጣሳቸውን ለማረጋገጥ የጠራው ስብሰባ መራዘሙን ሂውማን ራይትስ ወች ዘግቧል።

ድርጅቱ በድረገጹ ላይ ባሰፈረው ዘገባ ” የአለም ባንክ ፕሮጀክት ከሰፈራ ፕሮግራም ጋር የተያያዘ ነው። ሂውማን ራይትስ ወች የአለም ባንክ ከሰፈራ ጋር በተያያዘ የሚከተለውን ፖሊሲ እንዲመረምር ጥያቄ ማቅረቡን አስታውሷል። በሂውማን ራይትስ ወች ሪፖርት መሰረት በአለም ባንክ በሚደገፍ ፕሮጅክት 1 ሚሊዮን 500 ሺ ኢትዮጵያውያን ያለፍላጎታቸው ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ተደርጓል።

 

የአለም ባንክ መሰረታዊ ለሚባሉት አገልግሎቶች ለኢትዮጵያ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል። የሂውማን ራይትስ ባለስልጣን የሆኑት ጄሲካ ኢቫንስ የአለም ባንክ ፕሬዚዳንትና ቦርዱ በኢትዮጵያ ውስጥ ምርምራ እንዲካሄድ ማድረግ አለባቸው ብለዋል።

ሂማን ራይትስ ወች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ተከታትሎ በማጋለጥ ከፍተኛ እውቅና ያተረፈ ድርጅት ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ሂውማን ራይትስን የኒዮ ሊበራል ፍልስፍና አቀንቃኝ በማለት ድርጅቱ የሚያወጣቸውን ሪፖርቶች በተደጋጋሚ ውድቅ ሲያደርጋቸው ቆይቷል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: