የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲፈታ በድጋሜ ጠየቀ

መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-በዘፈቀደ የሚካሄዱ እስሮችን የሚከታተለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት  አካል የሆነው ፍሪደም ናው የተባለው ተቋም እንደገለጸው ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን አስሮ እስካሁን ማቆየቱ አለማቀፍ ህግን የሚጻረር ነው ።

አምስት ገለልተኛ ፓናሊስቶች የጋዜጠኛ እስክንድርን እስር በመመርመር፣ እስሩ ህገወጥ መሆኑን በመግለጽ፣ ጋዜጠኛው በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቀዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጋዜጠኛው አያያዝ እና የፍርድ ሂደት አለማቀፍ ህጎች የሚሉትን የተከተለ እንዳልነበር ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት ጸረ ሽብርተንነት ህጉን በመጠቀም የግል ጋዜጠኞችን ማፈኑን ማቆም አለበት በማለት የፍሪደም ናው ዋና ዳይሬክተር ማራን ተርነር ተናግረዋል። ህጉ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽን መብት ብቻ ሳይሆን እውነተኛ የጸጥታ ስጋቶችን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረትም የሚያሰናክል ነው በማለት ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ፍሪደም ናው ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ነጻ ህግ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: