የአቡነ ጳውሎስ መኖሪያ ቤት ውስጥ የተገኘው ሃብት አነጋጋሪ ሆኗል

 

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ታትሞ የተሰራጨው ቁምነገር መጽሔት እንደዘገበው ከሟቹ የአቡነ ጳውሎስ መኖሪያ ቤት ውስጥ የተገኘው ገንዘብ አንጋጋሪ ነው ይላል። እንደ መጽሔቱ ዘገባ ከሆነ “ፓትርያርኩ በየዓመቱ በዓለ ሲመታቸውን ሲያከብሩ ከየአብያተ ክርስቲያናቱ የሚበረከትላቸው ከጣት ቁጥር በላይ የሆኑ የወርቅ መስቀሎችና ከልዩ ልዩ ሀገር እህት አብያተ ክርስቲያናት የተበረከቱላቸው ውድ ውድ ስጦታዎችስ የት እንደደረሱ ባይታወቅም፤ የሞቱ እለት ታሽጎ የነበረው ቤት ሲከፈት የተገኘው አንድ የወርቅ መስቀል፣ 1 ሺህ የኢትዮጵያ ብር፣ 50 ዶላርና ጥቁቂት ብሮች የተመዘገቡበት የባንክ ደብተር ብቻ መሆኑ በከተማው መነጋጋሪያ” ሆኗል። ቁምነገር መጽሔት “ይልቅ ወሬ ልንገርህ” በሚለው አምዱ ያቀረበውን ሽሙጣዊ ዘገባ ያንብቡት።

የቀድሞው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሐይማኖት… የቀድሞው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚዳንት…የቀድሞው የዓለም ሀይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት… እነሆ ካረፉ ስድስት ወር ሆነ አይደል? እናስ? ታዲያ ምን አዲስ ነገር አለ? አልክ?
ምን መሰለህ? የፓትርያርኩ መኖሪያ ቤት ታውቀው የለ? የቱን? ቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን አጠገብ የሚገኘው ነዋ፡፡
እናልህ ያ መኖሪያ ቤታቸው የታሸገው ፓትርያርኩ ያረፉ ዕለት ነበር፡፡ እናስ? እናማ ቤቱ ከታሸገበት ጊዜ ጀምሮ በጥብቅ ጥበቃ ስር ነበር፡፡ ለምን መሰለህ? ያው የሚወራውን አንተም ሳትሰማ አልቀረህም፡፡
ፓትርያርኩ ባለፉት 20 ዓመታት ቤተክርስቲያኒቱን ሲያስተዳድሩ ከየዓድባራቱና ከየገዳማቱ ፈሰስ የሚደረጉ ገንዘቦች ነበሩ ይባላል….. ከየአብያተ ክርስቲያናቱ የሚገባው (በተለይም ከነግሸን ማርያም፣ አክሱም ፂዮን ማርያም እና ቁልቢ) የሚገባው ወርቅና ሌላም ሌላም የከበረ ሀብት በቀጥታ የሚላከው ወደ እሳቸው ነበር ይባላል፡፡ ያው ይባላል ነው፤ እንጂ መቼም የተረጋገጠ ነገር የለም፡፡ ታዲያ ለምንድነው ፓትርያርኩ እንደሞቱ ቤቱ ታሽጎ በፌዴራል ፖሊስ ጥበቃ ስር የወደቀው? ጥርጣሬ ይፈጥራል፡፡ እናልህ አዲሱ ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ባለፈው ሳምንት በዓለ ሲመታቸውን እንዳከበሩ የት ይግቡ? ቤቱ መከፈት አለበት በመባሉ ለዚሁ ተብሎ የተቋቋመው ኮሚቴ ባለበት ቤቱ ተከፍቶ ‹‹አሉ›› የተባሉትን ንብረቶች ተቆጥረው ምዝገባ ይካሄዳል በመባሉ ቤተሰቦቻቸው ሳይቀሩ ተገኝተው ነበር ተብሏል፡፡ እናልህ ቤቱ ሲከፈት ምን ቢገኝ ጥሩ ነው?
አንድ ወርቅ መስቀል…አንድ ሺህ የኢትዮጵያ ብር……50 ዶላር….ጥቂት ብሮች የተመዘገቡበት የባንክ ደብተር……በቃ….ሌላስ አልክ? ሌላው የብፁዕነታቸው አልባሳትና ቆብ ብቻ ነው የተገኘው፡፡ ሌላው የሳቸው ንብረት ያልሆነ የቤተክርስቲያኒቱ ስዕሎች መስቀሎች መቋሚያዎች አልጋና ወንበር ብቻ……
ፓትርያርኩ በየዓመቱ በዓለ ሲመታቸውን ሲያከብሩ ከየአብያተ ክርስቲያናቱ የሚበረከትላቸው ከጣት ቁጥር በላይ የሆኑ የወርቅ መስቀሎችና….ከልዩ ልዩ ሀገር እህት አብያተ ክርስቲያናት የተበረከቱላቸው ውድ ውድ ስጦታዎችስ…..አልክ? ይሄ የሁሉም ሰው ጥያቄ ነበር….
ከዚህ ሁሉ በኋላ ግን ብፁዕ አቡነ ማትያስ የጠየቁት አንድ ጥያቄ ነበር፡፡ ምን መሰለህ? ‹‹ፓትርያርክ መያዝ ያለበት የወርቅ መስቀል በመሆኑ የተገኘውን የወርቅ መስቀል ስጡኝ›› ብለው ፎቶ ላይ ገጭ አሉ፤…..በል ቻዎ
ዘ-ሐበሻ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: