ለ3ኛ ጊዜ ህትመቱ የተቋረጠበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ” ከእንግዲህ ከጫካ መለስ ባሉ መታገያ መንገዶች በመጠቀም መብታችን እናስከብራለን” አለ

መጋቢት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይህን የተናገረው ልእልና ጋዜጣ በመንግስት ጫና እንዳድታተም ከታገደች በሁዋላ ነው። ጋዜጠኛ ተመስገን ” የንግድ ሚኒስቴር በልእልና ጋዜጣ የቀድሞ ባለቤትና በአዲሱ ባለቤት መካከል ህገወጥ የሆነ የስም ዝውውር ተደርጓል በማለት የንግድ ፈቃዱ  ” እንዲሰረዝ መደረጉን ተነግሯል።

ፍትህ ጋዜጣ በህገወጥ መንገድ እንዳይታተም ከተደረገ በሁዋላ፣ ጋዜጠኛው አዲስ ታይምስ መጽሄትን ከሌላ አሳታሚ ላይ በመግዛት ለተወሰኑ ሳምንታት ሲያሳትም ቆይቷል። መጽሄቷ በተመሳሳይ መንገድ እንድትዘጋ ከተደረገ በሁዋላ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን እንደገና ልእልና ጋዜጣን ከሌላ አሳታሚ ላይ በመግዛት ስራውን ለመስራት ሞክሮ ነበር። ይሁን እንጅ ከ100 ሺ ብር በላይ በሆነ ወጪ የገዛው ጋዜጣ  ከመንግስት በተላለፈው ጫና እንዳይታተም በድጋሜ ታግዶበታል

ተመስገን በራሱ ስም ፈቃድ አውጥቶ መስራት ከተከለከለ፣ ከእንግዲህ ወዲያ ስለሚኖረው አማራጭ ሲጠየቅ፣ “ያለኝ አማራጭ ከሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር ፣ ከጫካ ትግል በመለስ ያሉትን የሰላማዋ ትግል አማራጮች በመጠቀም ፣ አስገዳጅ ሁኔታ በመፍጠር መብታችንን እናስከብራለን” ብሎአል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ሰሞኑን በገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ከፍተኛ ወከባ ሲደርስበት እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።  ተመስገን፣ ከ106 ያላነሱ ክሶችም እንዳሉበት ይታወቃል።

 

Advertisements

3 thoughts on “ለ3ኛ ጊዜ ህትመቱ የተቋረጠበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ” ከእንግዲህ ከጫካ መለስ ባሉ መታገያ መንገዶች በመጠቀም መብታችን እናስከብራለን” አለ

 1. Adugna ayana April 6, 2013 at 9:38 pm Reply

  Teme ayzogn.lehagerhe eyekefelk yalew waga/meswaetnet bedil yitenakekal.GETA eyesus keante gar yihun.

  Like

 2. Ewnetu April 7, 2013 at 3:27 pm Reply

  የሰላማዋ ትግል አማራጮች በመጠቀም ፣ አስገዳጅ ሁኔታ በመፍጠር መብታችንን እናስከብራለን!

  Like

 3. Personal Checks Wood April 8, 2013 at 7:36 am Reply

  “Real attractiveness comes from having a certain dignity.
  For all of these reasons, I think apology is the right move.
  Calling one of her trusty servants, she bribed him with a rich reward to take Snow
  White into the forest, far away from the Castle. Exceptions :
  Stocks of the same industry will be retained for comparison
  purposes. Worldwide, 30,742 deals closed worth $2.
  4 trillion, compared with 32,536 deals worth $1.9 trillion in 2010.

  Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: