የወያኔ ኢህአዴግ ባለስልጣናትን ተጠያቂ የሚያደርግ ምንም አይነት ስርአት አለመኖሩ ተረጋገጠ

Unknownየብአዴን ነባር ታጋይ ነው የሚባለው ህላዊ ዮሴፍ፣ ከፍተኛውን አመራር የምንጠይቅበት ስርአት የለም በማለት ሰሞኑን ብ አዴን ሲያካሂድ በነበረው ስብሳባ ላይ መናገሩን ዘጋቢያችን ከባህር ዳር በላከልን ሪፖርት ገለጠ። እንደዘጋቢያችን ሪፖርት በዚሁ በ ብ አዴኑ ስብሰባ ሙስና እና ፖለቲካ ብአዴንን እየፈተኑት እንደሆነ በግልጥ የታየ ሲሆን ህላዊ ዮሴፍ በንግግሩ ከፍተኛ አመራር አካላትን ተጠያቂ የሚያደርግ ስ ስር አት የለንም በማለት በዚሁ መድረክ መናገሩ ተሰብሳቢዎችን ሳይቀር እንዳስገረመ ገልጹአል። ህላዊ ዮሴፍ፣ የአማራ ልማት ማህበር ሊ/መንበር በነበረበት ጊዜ፣ የድርጅቱን የሂሳብ ሰነዶች አቃጥሎ ያለተጠያቂነት ወደ አዲስ አበባ እንዲዛወር መደረጉ አንዳንድ የብአዴን አባላትን ሲያብሰከስክ የቆየ መሆኑ ቢታወቅም ፣ በኢህአዴግ 9ኛው ጉባኤ ላይ ባሳየው ጠንካራ አቋምና ባቀረበው ንግግር ህሊናቸው የሚወቅሳቸውና ለሆድ ያደሩት የብአዴን አባላትን ማስደሰቱም ታውቁአል።

የባህርዳር ከተማ ህዝብ እና የብአዴን አባላት ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ እየፈጸመ ያለው ግፍና በደል ለከት ማጣት የውስጥ ለውስጥ ተቃውሞ ማስነሳቱ የሚታወቅ ቢሆንም በረከት ስምኦንና አዲሱ ለገሰ፣ ይህን እንቅስቃሴ ለማፈንና ለማዳከም የማይቆፍሩት ጉድጉአድ እንደሌለ ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው አንድ የቀድሞ የብአዴን አባል መናገራቸውን ገልጹአል።

በረከትና አዲሱ ለገሰ ቁልፍና በአይነ ቁራኛም መከታተል የሚፈልጉአቸውን ግለሰቦች፣ ማለትም የክልሉን የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ የነበረውን ከበደ ጫኔን እና የክልሉ የፍትህ ቢሮ ሀላፊ የነበረውን ጌታቸው አምባየን ወደ ፌደራል መንግስቱ እንዲዛወሩ ያደረጉ ሲሆን ከበደ ጫኔን ከጸጥታ ዘርፍ ሃላፊነት ወደ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒሰትርነት፣ ጌታቸውን ደግሞ ከፍትህ ቢሮ ሀላፊነት በምክትል ከንቲባነት ማእረግ የመሬት ባንክ ሃለፊ አድርገው ሾመዋል። እነኝሁ ሁለቱ ባለስልጣናት ወደ አዲስ አበባ እንደተዛወሩ በባህርዳር ከተማ ነዋሪ የሆነ ታዋቂው ባለሀብት ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ቤት ገዝቶ ቁልፉን ያስረከባቸው መሆኑን ተያይዞ የደረሰን ዘገባ አመልክቱአል።

የነ በረከት ስምኦንን ስር የሰደደ የስለላና የጭካኔ ርምጃ በጥልቀት የሚያውቁት እኚሁ የቀድሞ ብ አዴን አባል ለዘጋቢያችን እንደገለጡት አንድ ሰው ስለ እነ በረከት ክፉ ቢያወራ በደቂቃዎች ውስጥ ራሱን እስር ቤት ውስጥ ያገኘዋል፣ ያሉ ሲሆን እሄው ስር የሰደደ ሆድ አደርነትና ፍራቻ በብአዴን ወጣት አባላትም መባባሱንና እንዲያውም ወጣት አመራሮች ምንም ነገር ሳይናገሩ ጉባኤው መጠናቀቁን፣ ወጣት አመራሮች እንደ ተራው አባል ሁሉ “እናውቃለን፣ ብንናገር እናልቃለን ” የሚሉ አይነት አቁአም ይዘዋል ብለዋል።

Ginbot 7

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: