አገሬን የምትል በየት አለህ ?

563591_520834774628836_1159458005_n

ዳዊት ሰለሞን

ጥቃት የመጨረሻው ጥግ ሲደርስ የጥቃቱ ሰለባዎቸ የሚያነሱት ጥያቄ “አገራችን የት ነው” የምትል ስለ መሆኗ የአዲስ ነገር፣የአውራምባ ታይምስና የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሄት አዘጋጆችን ማስታወስ ብቻ ይበቃል፡፡ አገር እያላቸው መንግሰት አለሁላችሁ እያላቸው በአገራቸው እንዳሉና መንግስት እንዳላቸው እንዲሰማቸው ያላደረጓቸው ነገሮች ጥንካሬያቸውን እያጎለበቱ ወደ ጥቃት ጫፍ ሲያደርሷቸው ስደትን መረጡ፡፡ አሁን የሚገኙበት አገር አገራቸው፤ ህዝቡም ህዝባቸው መንግስቱም መንግስታቸው እንዳልሆነ ቢያውቁም ከአገር እንዲወጡ ያደረጋቸው ጥቃት ስላልተከተላቸው ቢያንስ የአካል ደህንነት ይሰማቸዋልና የስደት አገራቸውን እንደ አገር መቁጠራቸው ግፋ ሲልም እንደ ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ዜግነት መቀየራቸው የሚጠበቅ ይሆናል ፡፡ በኢትዮጵያችን “አገሬ የት ነው” የሚል ጥያቄ ለማንሳት የሚያበቁ ጥቃቶች በየዕለቱ የሚፈጸሙ መሆናቸውን ዜግነቱ ድንግርግር ላለው የአገሬ ልጅ መንገር ትርፉ ማሰልቸት ነው፡፡
ከሰሞኑ ግለሰባዊና ድርጅታዊ የነበረው ጥቃት መልኩን ቀይሮ ማህበረሰባዊ ገጽታ መላበሱን እየተመለከትን ነው፡፡ በቤኒሻንጉል ለአመታት ቤት ንብረት
አፍርተው ሰላማዊ ኑሮ
የነበሩ ዜጎች “ክልላችሁ ባለመሆኑ አካባቢውን ልቀቁ” ተብለው ለስደት ተዳርገዋል፡፡ የእነዚህ ዜጎችን መፈናቀል በሰማንበት ወቅት በሳዑዲ አረቢያ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን “ወደ አገራችሁ ተመለሱ” ተብለው ስለመፈናቀላቸው እያደመጥን ነበር፡፡ መቼም የሳዑዲው ይሁን ከገዛ አገር መፈናቀልን በምን ልንገልጸው እንችላለን፡፡ እርግጥ ነው በአንድ ክልል ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ለግጭት የመዳረጋቸው ዜና አዲስ አይደለም፡፡ ከመሬትና የተፈጥሮን ጸጋ ከመጠቀም አንጻር ግጭቶች መፈናቀሎች ይፈጠራሉ፡፡ ከግጦሽ መሬት ጋር በተያያዘ በተነሱ ግጭቶች የብዙዎች ህይወት ተቀጥፏል፡፡ እንዲህ አይነት ግጭቶች በተከሰቱ ቁጥር የፌደራል መንግስቱ ጣልቃ በመግባት ችግሩን ከስሩ ለመቅረፍ ከመሞከር ይልቅ ወታደሮቹን እያዘመተ ግጭቱ ካጠፋው የሰው ህይወት በላይ እንዲጠፋ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
ገዢው ግምባር ኢህአዴግ ይህችን አገር በብረት መግዛት ከጀመረበት ግዜ አንስቶ በተለያዮ ቦታዎች መፈናቀሎች ተከስተዋል፡ ፡ እነዚህ መፈናቀሎች አደረሱ ከምንላቸው የመብት ረገጣዎች፣ የሞራል ድቀቶች ባልተናነሰ ህይወት ተገብሮባቸዋል፡፡ በበደኖና በአርባጉጉ የደረሱ ሰቆቃዎች የጥቃቱን አድራሾች ማንነት ያልለዩ ከመሆናቸውም በላይ የድርጊቱ ፈጻሚዎች በፍትህ አደባባይ ቀርበው የእጃቸውን አለማግኘታቸው የጉራፈርዳው ትራጄዲ እንዲፈጸም ምክንያት ሆኗል፡፡ ጉራፈርዳ ወረዳ የነበሩ ዜጎችን እንዲፈናቀሉ ያደረጉ ሆዳሞች የተፈናቃዮቹን መሬት የግላቸው ማድረግ የመቻላቸው ዜናም በየክልሉ የሚገኙ ሆዳሞችን ማነቃቃቱ የሚጠበቅ ነው፡፡
በዚህ መነሻነትም ይመስለኛል በቤኒሻንጉል የአማሮች መሰደድ የተከሰተው፡፡ የኢትዮጵያ የወቅቱ ህገ መንግስት ዜጎች በፈለጉበት አካባቢ የመኖር፣የመስራትና ሀብት የማፍራት መብት እንዳላቸው የሚደነግግ ቢሆንም ነባራዊው እውነታ ግን ከዚህ ጋር በእጅጉ የሚጣረስ ነው፡፡
የዜጎች መብት በጥቂት ነውረኞች ሲደፈጠጥ ለምን የሚል ስርዓት ባለመዘርጋቱም በደህናው ጊዜ አገሬ ነው በሚል ኢትዮጵያዊ ስሜት ተነሳስተው ከቀያቸው ርቀው ኑሮ የመሰረቱ ዜጎች ድንጋጤ ውስጥ እንዲገቡና የሰቀቀን ህይወት እንዲመሩ እየተደረጉ ነው፡፡ኢህአዴግ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስም እንዲህ አይነት ዘግናኝ ዜናዎችም መደመጣቸው አይቀሬ ነው፡ ፡ ነገሩ ስር እየሰደደና በሁሉም ክልልሎች የሚገኙ ሆዳሞች ምሳቸውን ለማግኘት የእባብ መርዛቸውን ከመርጨታቸው በፊት አገሪቱን በቀደመው የኢትዮጵያዊነት ጠበል የሚያጠምቅ መሲህ መፈጠር ይኖርበታል፡ ፡ እርግጥ ነው ይህ መሲህ ከድንግሊቱ የሚወለድ ባለመሆኑ ‹‹ድንግሏን››መጠበቅ አይኖርብንም፡፡ወይም መቼ ይሆን መሲህው የሚወለደው በማለት ለጠቢባን ስንቅ መሰነቅ አይጠበቅብንም፡፡ምክንያቱም አዳኙ
የክልል ወይም የፌደራሉ መንግስት ለም መሬትን ለውጪ አገራት ኢንቨስተሮች ያለ ገደብ በመስጠት ዜጋውን የበይ ተመልካች ማድረጋቸውም እየሰማነው ለምንገኘው ማፈናቀል የመሰረት ደንጊያ ሆኗል፡፡ዜጋውን ተጠቃሚ ያደረገ ፖሊሲ የሌለው ድኩም መንግስት ደግሞ የመጀመሪያ ትኩረቱ ወደ አገር እንዲገቡ ያደረጋቸው የውጪ ኢንቨስተሮች እንጂ ዜጋው ባለመሆኑ ጉዳዩ የክልሉን መንግስት የሚመለከት በመሆኑ ጣልቃ አልገባም ማለቱ የሚጠበቅ ነው፡፡ከጥቂት ጊዜ በፊት በ ኡጋዴን በቻይና ሰራተኞች ላይ የደረሰውን ጥቃት አቀነባበሩ ያላቸውን ሀይሎች መንግስት በቁጥጥር ስር ለማዋል ምን ያህል ፈጣን እንቅስቃሴ ማድረጉን የሚያስታውሱ ሰዎች ቻይናዊነትንና ኢትዮጵያዊነትን ጠረጴዛው ላይ በማቅረብ ለዚህ መንግስት የትኛው እንደሚቀርብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ የክልል መንግስታት ተወላጆች ከሚሏቸው ዜጎች የሚነሳባቸውን የመልካም አስተዳደር፣የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች እንዲህ አይነት ሆድ አደር ካድሬዎችን በማሰማራት ማድበስበስ እንደሚችሉ ገምተው ከሆነ ተሳስተዋል፡፡እርግጥ ነው ዜጎችን በማፈናቀል ጥቂት መሬት ተገኝቶ ይሆናል፡፡የዚህ ጦስ ግን ዘመን ተሻጋሪ ነው፡፡ ሆዳሞች ኢትዮጵያዊንትን
www.fnotenetsanet.com
መስርተው
የሚመጣው እኛ ለዚህች አገር ከሚኖረን ርዕይ ነው፡፡አገሬ ይህችው ኢትዮጵያ እንጂ ሌላ አይደለችም የምንል ከሆነ ምድራችን በጥቂት ሆድ አደር በቀቀኖች የሁቱና ቱትሲ አይነት እልቂት ሳይከሰትባት፣እርስ በእርሱ የማይተማመንና ብሄራዊ ስሜት የሌለው ማህበረሰብ ሳይፈጠርባት የበኩላችንን ለማድረግ እንነሳ፡፡ የቤኒሻንጉል ህዝብ አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ ወንድሞቹን ከክልሉ እንዲሰደዱ አደረገ ማለት ለእኔ ህዝቡን መስደብ ነው፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት 22 ዓመታት እንዲጋት የተደረገው የዘውጌ ፖለቲካ አንድነቱን ሳይንድበት እስካሁን ኢትዮጵያዊነት በሚሰኝ አንድ ጥላ በመሰብሰብ አገሪቱን ማባሪያ ወደሌለው ዕልቂት ሊከታት ይችል የነበረን ሃላፊነት የጎደለው ፖለቲካ ታግሏል፡፡ ነገር ግን ይህ መስመር ዋጋ አላስከፈለንም ማለት አይቻልም፡፡ውድ የኢትዮጵያ ልጆች መተኪያ የሌለውን ህይወታቸውን ገብረውበታል፡፡ለአመታት የደከሙበትን ንብረት ሆዳሞች ተቀራምተውታል፡፡
አሸንፈው እነመለስ በ1997 ምርጫ ወቅት እንደፎከሩብን ኢንተርሀሙዬ እንደማይወለድ አምናለሁ፡፡የአማራው መፈናቀል የጉራጌው፣የትግሬው፣የኦሮሞውና የሌላውም መፈናቀል እንጂ ኦሮሞው፣ቤኒሻንጉሉ ወይም ሀድያው አፈናቃይ አይደለም፡ ፡የኢትዮጵያ ህዝብ ወይም አማራው የበደኖው፣የቤኒሻንጉሉና የጉራፈርዳው አፈናቃዮችን ማንነት አብጠርጥሮ የሚገነዘብ በመሆኑ ጊዜው ሲደርስ ማንን በፍርድ አደባባይ እንደሚያቆም ያውቃል፡፡አማራው በኦሮሞው ፣ጉራጌው በትግሬው እንዲነሳ የሚፈልጉና አጀንዳ በማስለወጥ የስልጣን ጊዜያቸውን ማርዘም የሚመኙ ሆዳሞች ከርሳቸውን ሳይሞሉ የክፉ ህላማቸው ሳይሰምር እጅ ከፍንጅ መያዛቸው አይቀሬ መሆኑ በተስፋ እንድታሰር ያደርገኛል፡፡ይህ የክፋት ቀን እንዲያጥር ግን አገሬን ባዮች ከማጀት መብሰልሰል ወደ አደባባይ መውጣት ግድ ይላቸዋል፡፡ እናም የቤኒሻንጉሉ ግፍ የሚያስተጋባው የጥሪ ደወል‹‹አገሬን የምትል በየት ነህ ››የሚል ነው፡፡ይህን የሚሰማም እነሆ በዚህ ነኝ ይበል፡፡

fnotenetsanet

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: