መንግስት የህሊና እስረኞች ላይ የሚያደርሰውን የግፍ አይያዝ ሊያቆም ይገባል!

በህሊና እስረኞች ቁጥር ከፍ በማለቱ፣ሀገሪቱ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ወህኒ ቤቶችን አጣበዋል፡፡ በፖለቲካ አመለካከታቸው፣የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው፣ የሃይማኖት ነፃነት ጥያቄ በማቅረባቸውን በሌሎችም ምክንያቶች ወንጀል ሳይፈፅሙ የሚታሰሩት የህሊና እስረኞች በግፍ መታሰራቸው ሳያንስ፣ በወህኒቤት ውስጥ ሆነው የተለያዩ የግፍ ድርጊቶች ይፈፀምባቸዋል፡፡

የኢህአዴግ መንግስት በውጫዊና በውስጣዊ ምክንያቶች በተናወጠ ቁጥር በእስረኞች ላይ በተለይም በህሊና እስረኞች ላይ የግፍ በትር የመምዘዝ እኩይ ልምድ አለው፡፡ ለማሳያነት ያክልም በምርጫ 97 ማግስት እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሞት ይፋ ሲደረግ ስቃችኋል፣ ደስብሏችኋል በሚል የተደበደቡ፣ ከሚኖሩበት ስፍራ የተዛወሩ፣ዛቻና ማስፈራሪያ ደረሰባቸው ዜጎች መጥቀስ ይቻላል፡፡

በኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች ውስጥ የሚፈፀሙ ሆኖም በሚዲያ ለመዘርዘር የመይመቹ በርካታ ሰብአዊነት የጎደላቸው የግፍ ድርጊቶች እንዳሉ የሚያመላክቱ መረጃዎች በየጊዜው ለጋዜጣችን ይደርሳሉ፡፡ የእነዚህን መረጃዎች እውነትነት ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ መንግስትን የእስረኞች አያያዝ የያሳዩ አለም አቀፍ ሪፖርቶችን መመልከት በቂ ነው፡፡
በህግ ጥበቃስር የሚገኙ እስረኞች በህገመንግስት የተረጋገጡ መብቶች አሏቸው፡፡ ከዚህ ውስጥ የሚጠቀሰው እስረኞች በወዳጅ ዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸውና በሃማኖት አባቶቻቸው መጎብኝት መብት ነው፡፡ ሆኖም አብዛኞቹ የህሊና እስረኞች ከቅርብ ቤተሰቦቻተው ውጪ በሌሎች እንዳይጠየቁ ክልከላ ደርሶባቸዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በወህኒ ቤቱ ውስጥ ህገ ወጥ ክትትልና ሌሎች በደሎችም ይደርስባቸዋል፡፡
በድፍረት መናገር እንደሚቻለው የኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች መንግስት ተቀናቃኞቼ ናቸው የሚላቸውን ዜጎች የሚበቀልበት ስፍራ እንጂ ማረሚያ ቤቶች አይደሉም፡፡

ለመብቱ መከበር የታገለ ዜጋ ያለጥፋቱ የሚታሰርበትና በእስር ላይ ሆኖ ጥቃትን ሚቀበልበት ስፍራ እንደምን ማረሚያ ቤት ልንለው እንችላለን?

የህሊና እስረኞቹ በግፍ መታሰራቸው ሳይበቃ በመንግስት በሚላኩ “ሽማግሌ ነን” ባዮች ባልሰሩት ወንጀል ይቅርታ እንዲጠይቁ የተለያየ ጫና ይደረግባቸዋል፡፡ ሆኖም በደል ሲደርስባቸው “ሽማግሌ ነን” ባዮቹ ጆሮ ዳባልበስ ማለታቸው አስተዛዛቢ ነው፡፡

ለህሊና እስረኞች በተቃዋሚ ፓርቲዎችም ተገቢውን ትኩረት አግኝተዋል ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ ይመስለናል፡፡ በርግጥ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህሊና እስረኞችን ለማሰብ በየወሩ የሻማ ማብራት መርሀግብር ያዘጋጃል፤ ይህ በሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሊተገበር የሚገባው መልካም ተሞክሮ ነው፡፡ ሆኖም ተቃዋሚዎች ከዚህ ባለፈ መንግስት የኢህአዴግ ባለስልጣናት በአምባገነንነት እብሪት በህሊና እስረኞች ላይ የሚፈፅሟቸውን ኢሰብአዊ በደሎች እንዲያቆሙ የሚያስችል ጠንካራ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በማድረግ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል መቁረጥ ይገባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብም በአመለካካታቸው ብቻ የታሰሩ ዜጎችን ጉዳይ በቅርብ መገታተል ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር በመሆን መንግስት የሚያደርሰውንም ግፍ ለመቃወም መነሳት ይጠበቅበታል፡፡

ከሁሉ በላይ ለመንግስት ሊገባው የሚገባው ቁም ነገር ግን ታጋዮችን በማሰር ብሎምም በመግደል የሚቆም የነፃነት ትግል እንደሌለ ነው፡፡ አዎ! ኢህአዴግ ሆይ ብዙዎች የታሰሩለት፣ ብዙዎች የተሰቃዩለትና የሞቱለት ነፃነት ፈጠነም ዘገየ እንደሚመጣ ቅንጣት አንጠራጠርም፡፡

fnotenetsanet

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: