በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ ለፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡት ስምንት የህሊና እስረኞች ለስድስተኛ ጊዜ ጉዳያቸው መታየት ባለመቻሉ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡ከአራት ወራት በፊት ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤቱ በተላለፈባቸው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት በማግኘቱ አቃቤ ህጉን ያስቀርባል በማለት ያከራከረ ቢሆንም የመጨረሻና ገዢ የሚሰኘውን ውሳኔ ለማስተላለፍ በቀጠሮ ጉዳዮን ማጓተቱ አግራሞት ጭሯል፡፡
ዛሬ ማለዳ የመጨረሻውን ውሳኔ ለማድመጥ ከቃሊቲና ቂሊንጦ ማረሚያ ቤቶች ብረት ባነገቱ ፖሊሶች አጀብ እጆቻቸው በካቴና ተጠፍንገው የቀረቡት እነ አንዷለም ዳኞቹ መዝገቡን መርምረው ውሳኔ ለመስጠት ጊዜ ያጠራቸው መሆኑን በማሳወቅ ለሚያዚያ 24/2005 ተለዋጭ ቀጠሮ ለመስጠት መገደዳቸውን ሲያስታውቁ እንግዳ ፊት ባለማሳየት ነገሩን ቀደም ብለው የሰሙ ያህል ወደ መቀመጫቸው ተመልሰዋል፡፡
fnotenetsanet
Advertisements
Leave a Reply