የአቶ መለስ ዜናዊን ስም፣ ምስልና ሥራዎቻቸውን መጠቀምን የሚከለክልና የሚፈቅድ የመመርያ ረቂቅ ቀረበ

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር እንደዘገበው የአቶ መለስ ዜናዊን  ማንኛውም ከመንግሥትና ከፓርቲ ሥራዎች ጋር ያልተያያዙ ምስሎች ወይም ፎቶግራፎች ባለቤትነት የቤተሰቦቻቸው ብቻ ነው።

ረቂቅ መመርያው፣ ማንኛውም ሰው ገንዘብ ለማሰባሰብ፣ ለሽያጭ፣ ለባዛር፣ ለጨረታ ወይም ለማንኛውም ዓይነት ጥቅም ማስገኛነት ሊሰቅል፣ ሊለጥፍ፣ ሊቀርጽ ወይም ሊያስቀምጥ እንደማይችል ይከለክላል፡፡

የአቶ መለስን ፍቅርና ክብር ለመግለጽ የሚፈልጉ ምስላቸውን በመኖሪያ ቤታቸው ግድግዳ ላይ ሊሰቅሉ፣ በአልበም ውስጥ፣ በቦርሳቸው፣ በኪሳቸው፣ በተሽከርካሪያቸው ወይም በሌላ የግል መጠቀሚያቸው ሊይዙ እንደሚችሉ ደግሞ መመርያው ይፈቅዳል እንደ ጋዜጣው ዘገባ።

ከፋውንዴሽኑ ቦርድና ከቤተሰቡ በቅድሚያ ፈቃድ በመጠየቅ ስማቸውን ለአርዓያነት፣ ለማስተማሪያነትና ለመታሰቢያነት ማንኛውም ሰው መጠቀም እንደሚችሉ የመመርያው ረቂቅ የሚያስረዳ ሲሆን፣ በተለየ ሁኔታ ለሕዝባዊ ዓላማም ከሆነ ፈቃድ ጠይቆ ገንዘብ ማሰባሰብም እንደሚቻል በረቂቁ ተጠቁሟል፡፡

በአቶ መለስ ስም የታተሙም ሆነ ያልታተሙ ሥራዎች ለቤተሰባቸው እንደሚሆኑ የሚገልጸው ረቂቅ መመርያው፣ በመንግሥት ወይም በፓርቲ ኃላፊነታቸው የሠሯቸው ማናቸውም ሥራዎች ባለመብት መንግሥት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብና አባል ድርጅቶች መሆናቸውን ገልጿል፡፡

አንዳንድ ወገኖች አቶ መለስ ዜናዊ እንደጣኦት መመለክ ጀመሩ በማለት በማህበራዊ ድረገጾች አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: