በሁለት ወር ውስጥ ከ15 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ የመን ገብተዋል(IOM)

 የመን ውስጥ ምላሱን የተቆረጠውን ሀፊዝ ጨምሮ 25 ኢትዮጵያዊያን ሆስፒታል ገብተዋል

 ዮርዳኖስን መኪና ላይ አስረው መሬት ለመሬት ጎተቷት፣ (ሚሚ) ተደፈረች…ቃለ ምልልስ አለኝ

(ግሩም ተ/ሀይማኖት)

የመን ውስጥ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰው በደል ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መጥቷዋል፡፡ በጅቡቲ አድርገው ቀይ ባህርን ተሻግረው ወደ የመን የሚገቡትን ኢትዮጵያዊያንን በማገት 1000 እና 1500 የሳዑዲ አረቢያ ሪያል እና ከዛም በላይ ከወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲያስልኩ የሚያደርጉ አፋኞች መኖራችን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ

መግለጼ ይታወሳል፡፡ እነዚህ አፋኞች ያገቱት ሰውን ለማስለቀቅ
ገንዘብ የሚልክለት ከሌለ ከተራ ድብደባ እስከ መግደል የደረሰ ቅጣት
ይፈጽማሉ፡፡ አይን ማጥፋት፣ ብልት መቁረጥ፣ በእሳት ማቃጠል፣
በህወይት እያሉ መቅበር፣ መድፈር…የመሳሰሉትን ይከውናሉ፡፡ እነዚህን አፋኞች ካገቷቸው ውስጥ 25 ኢትዮጵያዊያን ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ገቡ ሲል የመረጃ ምንጬ ገልጾልኛል፡፡

ትላንትናሰኞ(በ8/4/13) የየመንሀገርውስጥሚኒስቴርየሀረጥአውራጃደህንነቶችን፣ድንበርጠባቂዎችን፣ሁለትብርጌድ የተውጣጣ ወታደር አድርገው አፋኞቹ ያሉበትን አካባቢ በመክበብ 158 ኢትዮጵያዊያንን ነጻ አውጥቷል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 25 የሚሆኑት

ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው በመሆናቸው ሆስፒታል መግባታቸውን ተልዕኮውን የመሩት ኮረኔል አሊ ኡመር ይስለም ገልጸዋል፡፡ እንደ ኮረኔሉ አባባል በአካባቢው ያሉ ባለስልጣናት በአብዛኛው እነዚህን አፋኞች የሚረዱ፣ የተሳሰሩ እና የሚተባበሯቸው በመሆኑ የነበረውን የማስለቀቅ ትግል ከባድ እንዳደረገው ገልጸዋል፡፡ በመሳሪያ ትጥቅም በኩል ቢሆን ከመንግስት ሀይል የላቁና የተደራጁ መሆናቸውን አስምረውበታል፡፡ በመጨረሻም ከእነዚህ አፋኞች ጋር የአለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት( IOM) ሰራተኞችም አባሪ ሆነው ተገኝተዋል ሲሉ የሚያሳዝን እና ተይቶ የማይታወቅ አሰቃቂ ድርጊት ኢትዮጵያዊያኑ ላይ መፈጸሙን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የመረጃ ምንጬ እንዳመለከተኝ ከተጎጂዎች መካከል ያናገራቸው ሰዎች ስላሉ እነሆ፡-

ሚሚ ትባላለች፡፡ የ19 አመት ሴት ነች፡፡ አካባቢዋ ላይ ያሉ ልጆች ሲጓዙ ስላየች እንደተጓዘች ነው ለጠያቂዋ የነገረችው፡፡ የተለያዩ ፈተናዎች ቢገጥሟትም ባህሩን አልፋ ከየመን ጠረፍ እንደረገጠች በአጋቾች እጅ ወደቀች፡፡ አንደኛው አጋች ነይ የእኔን ክፍል አጽጂ ብሎ ወደ አንድ ክፍል አስገባት፡፡ ለብዙም ደፈሯትም፡፡ ይህን በተመለከተ ስለጉዳዩ መግለጫ የሰጡት ባለስልጣን ‹‹..ሰቅጣጭ በሆነ ሁኔታ ነው መደፈሩ የተከወነባት..›› ብለዋል፡፡

ሀፊዝ ይባላል፡፡ የሚከፍለውም ሆነ የሚያስልክበት ቦታ ስለሌለው የደረሰበትን ድብደባ መቀበል ግድ ብሎት ቆይቷል፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ምላሱን ቆርጠውት ሀረጥ ሆስፒታል በህክምና ላይ ነው ያለው፡፡ አንደኛዋ ሴት ደግሞ ዮርዳኖስ ትባላለች፡፡ ድብደባውን በጸጋ ብትቀበልም ገመድ አንገቷ ላይ አጥልቀው እየሰቀሉ ደብድበዋታል፡፡ አንቀዋት ትንፋሽ ሲያጥራት አውርደው መኪና ላይ በማሰር ጊቢው ውስጥ መሬት ለመሬት በመጎተት ሰውነቷ እስኪላላጥ ጎድተዋታል፡፡

በተያያዘ ዘገባ በሁለት ወር ውስጥ ከ15 ሺህ በላይ ኢትዮጵዊያዊያን ባህር ተሻግረው የመን መግባታቸውን አለም አቀፉ የስደተኞች ጽ/ቤት (IOM) አስታወቀ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንጂ ሲቀንስ ያልታየው የኢትዮጵያዊያን የስደተኞች ባህር ማቋረጥ አሳሳቢ ከሚባለው በላይ ሆኗል፡፡

በ2010 ዓ.ም ብቻ 53000 ኢትዮጵያዊያን የኤደን ባህረ ሰላጤን እና ቀይ ባህርን ተሻግረው የመን መግባታቸውን ከሁለት ሺህ በላይ ባህሩ ላይ መቅረታቸውን IOM ገልጾ ነበር፡፡ ጉድ ጉድ ሀገር ውስጥ ማን ቀረ ተብሎ ታለፈ፡፡ መንግስት ዝምታ ምሽግ ውስጥ ተቀብሮ ማዳመጡ በርቱ ውጡ ያለ መሰለ፡፡ ከዛም ቁጥሩ ማሽቆልቆል ሳይሆን ማሻቀብ አሳይቶ በ2011 ባህር ተሻግሮ የየመንን ድንበር የጣሰው

ኢትዮጵያዊ ቁጥር 103000 ደረሰ፡፡ ቱ…ቱ…አደገልን የሚያስብል አለያም በእልልለታ የታጀበ አታሞ የሚያስደልቅ አይደለም፡፡ የሀዘን ከል የሚያስለብስ ነበር፡፡ ምክንያቱም በባህሩ ላይ የሚጓዘው ቁጥሩ ማየል በተቀናጀ መልኩ ለዘረፋ የሚነሱ ግሩፖችን አስከተለ፡፡ በዚህ

የተደፈረችው ሚሚ እና በመኪና የተጎተተችው ዮርዳኖስ

ሰዓት መንግስት ችግሩ አሳሳቢ መሆኑን ተነፈሰ እና ምንም አይነት መላ ሳይዘይድለት በውስጣዊ እንጉርጉሮ ‹‹የራሳችሁ ጉዳይ….›› ብሎ ያቀነቀነ መሰለ፡፡ በ2012 ደግሞ ‹‹..እባካችሁ ኑ…›› ተብሎ ቅስቀሳ የተደረገ ይመስል አሻቅቦ 107000 ኢትዮጵያዊያ የመን መግታቸውን IOM አስታወቀ፡፡ በዛው ልክ ባህር ላይ የሚሞቱትም ቁጥር መጨመሩ ያሳሰበው አይ.ኦ.ኤም ሀረጥ ባለው ካምፕ ውስጥም ከ14 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን በመኖራቸው የሳዑዲያን፣ የየመንን እና የኢትዮጵያዊያንን ባለስልጣኖች ለውይይት ጋበዘ፡፡ ከኢትዮጵያ መንግስት የተገኘው ድጋፍም ሆነ ምላሽ አሳፋሪ እና ለዜጎቹ ያለውን ክብር ግምት ውስጥ የከተተ ነበር፡፡ ‹‹ወደ ሀገር ስትመልሷቸው እንቀበላለን፡፡ ከዛ ውጭ ምንም ማድረግ አንችልም፡፡›› ነበር ያሉት፡፡

አስቡት ላለመቀበልም አስበው ነበር ማለት ነው? በዕርግጥም ሀገር ውስጥም ያሉትን ህጋዊ አይደላችሁም እየተባሉ ሲፈናቀሉ እያየን ክጭ ከስደት የሚመለሱትንስ በዝምታ ይቀበላል ብሎ ሰብ ሳይከብድ ይቀራል፡፡ ባለፈው ጊዜ ከሳዑዲያ ተመለሱ የተባሉ 60 አካባቢ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር ልሱን ብለው ነበር፡፡ ኤምባሲውም ሆነ ኮሚኒቲው የሰጡት መልስ አሳፋሪ ነበር፡፡ እየአንዳንዳችሁ 250-300 ዶላር ክፍሉ ካለበሊያ አናውቃችሁም አሉ፡፡ ፖሊስ አምጥተው አሳፍሰው ከከተማ ክልል ውጭ ተጣሉ፡፡ ዜጋውን እንደቆሻሻ አሳፍሶ ያስጣለ ብቸኛው ኤምባሲ ሳይሆን ይቀራል፡፡ ከተጣሉበት ተመልሰው ‹‹ኢትዮጵያዊ ነን እና መመለስ እንፈልጋለን መልሱን ወደ ሀገራችን..›› ብለው ኮሚኒቲው በር ላይ ተቀመጡ፡፡ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸው የመጡ ኢትዮጵያዊያን እንዳይራቡ እህል ውሃ ያላቸውን ሰው ሁሉ መክሰስና ማሳሰርም የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ስራ ሆነ፡፡ በመጨረሻም ስደተኞቹን አሳፍሶ ሚግሬሽን እስር ቤት አስገባ፡፡

ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com April 10, 2013

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: