ከአህባሽ ጀርባ፣ ሙስና ተስፋፋ!

Image
ድምፃችን ይሰማ

313 ሚሊዮን ብር እንደገና ለአህባሽ ጠመቃ ስምምነት ተደረገ፡፡ ባለፉት ፅሁፋችን ‹‹አህባሽ በዞረበት ነውጥ አይጠፋም!›› በሚል ርዕስ በሁለት ክፍሎች ስለአህባሽ ሃይማኖታዊ ቅብ ነውጠኛ አንጃ አለማቀፋዊ የረብሻ ተግባራት ከብዙ ጥቂቶቹን ብቻ ማንሳታችን ይታወሳል፡፡ ለዛሬ ደግሞ የዚሁ ቡድን ዋነኛ መገለጫና አካል የሆነውን መንግሥታዊና መጅሊሳዊ ሙስና በዚቹ በድሃ ሀገራችን ላይ ያለውን ሰሞነኛ ሙስና ብቻ በጥቂቱ እናነሳለን፡፡

መጅሊስ እንደ ተቋም ከሙስሊሙ እጅ ወጥቶ በእጅ አዙር የመንግሥት ካድሬዎች መሾፈር የጀመረው ከ1987ቱ የአንዋር መስጂድ ጭፍጨፋ ማግስት ነበር፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ህዝበ-ሙስሊሙ ብዙና የተጠራቀሙ ዘርፈ-ብዙ ችግሮችና በደሎች በመጅሊስ እየተፈፀመበት ለዓመታት ያህል ቆይቶ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ‹‹ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል›› እንዲሉ ለተቋቋመለት ዋነኛ ዓላማ ለህዝበ-ሙስሊሙ ጥቅምና ፍላጎት አለመስራቱ ሳያንሰው መንግሥት የነደፈውን የኢትዮጲያውያንን ሙስሊሞች ‹‹እስልምናችሁን እኔ ልምረጥላችሁ›› የአህባሽ ጠመቃ መርሀ ግብር አሜን ብሎ መቀበሉና ማስፈፀሚያ ሽፋን መሆኑ ከሁሉም በላይ አሳዛኙና ትልቁ ጥፋት ነበር፡፡ ታዲያ በዚህ ጊዜ ነበር እንግዲህ ህዝበ-ሙስሊሙ ‹‹ወይ ሞት፣ ወይ ሽረት!›› በሚል እስልምናን በኢትዮጲያ ምድር ለመታደግ በአንድነት የተለሳው–ትልቅ ህዝብ፣ ትልቅም አደራ!

ለዚሁ የጠመቃ መርሃ ግብር መሳካት ሲባል በመጅሊሱ የተሰገሰጉ የአህባሹ አንጃ አባላት ለጆሮ በሚከብድ መጠነ ሰፊ የሙስና ተግባራት ውስጥ ተዘፍቀው እንደነበር የሚያሳዩ ብዙ የአደባባይ ሚስጥሮች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ያህል የሐጅ ገንዘብ ሙስና፣ የመቃብር ቦታ ሽያጭና የሱቆች ኪራይ ወዘተ በጣም በግልፅ ከሚታወቁት ጥቂቶቹ ብቻ ነበሩ፡፡ ይህም የመጅሊሱ ባለሥልጣናት የሙስና ወንጀል ለመንግሥት የጠመቃ መርሀ ግብሩ ተግባራዊነት ፍፁም ታዛዥነታቸውን እንዲሰጡ ማስፈራሪያ ስትራቴጅ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ከዚህም ባለፈ በየመንግሥታዊ ስብሰባዎች ላይ ቱባ የመጅሊስ ባለሥልጣናት ሁሉ ሳይቀሩ የውሎ አበል ሲሻሙ ማየት በጣም የተለመደና ዓላማቸውን በግልፅ የሚያሳብቅ ነበር፡፡

የህዝበ-ሙስሊሙን ሰላማዊ ተቃውሞ ለማርገብ ሲባል መንግሥት እነዚህን ሙሰኞች በመንግጅሊሳዊው ቅርጫ በሌሎች ጥቅመኞች በባለፈው መስከረም ወር ላይ የተካቸው ቢሆንም ዓላማቸው የግል ጥቅም ማግበስበስ ነውና ከሰሞኑ ዜናዎች ውስጥ የነዚሁ የጥቅመኛ አህባሾች ሥነ-ምግባር ብቻ ሳይሆን ሰብዓዊነት የጎደለው የሙስና ወንጀል ማስተጋባት ይዟል፡፡ ሙስና የአንጃው መገለጫ ነውና የህዝበ-ሙስሊሙን ሀብትና ንብረት ያለምንም ርህራሄ ሲያጋብሱና ህዝብን በልማት ስም ሲያጭበረብሩ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ ጨቅላ ህፃናትን ከአንዋር መስጂድ መድረሳ አባሮ ለግል ጥቅም ሲባል ለመጋዘንነት ማከራየት፣ ለአንዋር የላይኛው መንገድ ልማት ሥም የተከራይ ባለሱቆችን ገንዘብ በማጭበርበር መዝረፍ፣ ወዘተ (በግልፅ የማናውቃቸውን ጨምሮ) የሚደረጉ ወንጀሎች ሰብዓዊነትንም ይፈታተናሉ፡፡ ማለትም ልጅ ለወለደ አባት ልጁን ከምትናፍቀው መድረሳዋ/ው አባሮና ሜዳ ላይ ጥሎ ለግል ጥቅሙ እንደማዋል ይታያልና ነው፡፡ ይህ በንፁህ አዕምሮ ሲታሰብ የሰብዓዊነት ባህሪ ላይኖረው ይችላል ሆኖም ግን የሥርዓቱ ብሎም የአንጃው ባህሪይ ነውና አድርገውታል እያደረጉትም ነው፡፡

መንግሥታዊ ሙስና- ለአህባሽ ጠመቃ!

ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ደግሞ ከዚሁ ከጉደኛው መንግሥት ሌላ አዲስ ነገር ብቅ ብሏል፡፡ ለነውጠኛው የአህባሽ አንጃ አስተምሕሮ ዳግም የጠመቃ መርሀ ግብር 313 ሚሊዮን ብር ለመፍቀድና መርሀ ግብሩን ለማሳለጥ እንደሚውል ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ በንፁህ ውሃ እጥረት (ከተሞችን ጨምሮ) ብዙ ህዝብ በሚሞትባት ሀገር፣ ብዙ እናቶች በወሊድ ህክምና አገልግሎች እጥረት በሚሞተባት ሀገር፣ ህፃናት በአቅራቢያቸው ትምህርት ቤት አጥተው ለመማር በማይችሉባት ሀገር፣ በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ በዝናብ እጥረት ምክንያት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ በሚጠይቁባት ሀገር፣ 313 ሚሊዮን ብር ነውጥ ፈጣሪ አንጃ ለማስፋፋት በመንግሥት ሲታቀድና ሲመደብ በእውነት የጤና ነውን? በዚህ ገንዘብ ስንት የውሀ ጉድጓዶችን፣ ስንት የገጠር መንገዶችን፣ ስንት ክሊኒኮችንና የጤና ኬላዎችን፣ ትምህርት ቤቶችንና ተቃሚ የልማት ሥራዎች በሰራንበት ነበር፡፡ ነገር ግን አልሆነም፣ ለጥሩ ልማት መልካም የሚያስብ አልታደልማ!

ይህ የኢትዮጲያን ህዝብ ሀብትና ንብረት ያለአግባብ፣ ያለህዝብ ፍቃድ፣ ሰላማዊ የነበረውን የሙስሊም-ክርስቲያን ግንኙነት በእጅጉ ለመጉዳት፣ የአህባሽ አንጃ ሀገራዊ ነውጥን ለማንገስ የሚደረግ አህባሻዊ የግዳጅ ጠመቃ መርሀ ግብር ሲባል ለመንግሥታዊ ጥቅምና ፖለቲካዊ ፍጆታ የሚፈሰው ገንዘብ በእርግጥም መንግሥታዊ ሙስና ተፈፅሞበታል፡፡ ይህ የሕዝቦችን መልካም ግንኙነት ለማጥፋት የሚደረግ ያላሰለሰ ጥረት ታሪክ የማይሽረው ህዝባዊ በደል ነው፡፡

አላህ ሆይ! ለበደላችን ድልን አጎናፅፈን! ሀገራችንንና ህዝባችንን ከተንኮለኞች ጠብቅልን! አሚን!

አላሁ አክበር!
ECADF

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: