ከፍተኛው ፍርድ ቤት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጠ

ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ፣ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን የመከላከያ ምስክሮች ያዳምጣል ተብሎ ቢጠበቅም፣ አቃቢ ህጎች የጊዜ ቀጠሮ በጠየቁት መሰረት ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል።
የጋዜጠኛ ተመስገን ጠበቆች ታዋቂውን የሰብአዊ መብቶች ተማጓች ፕ/ር መስፍን ወልደማርያምን ጨምሮ ሁለት ባለሙያዎችን ለመከላከያ ምስክርነት ከማቅረብ በተጨማሪ ሌሎች የቪዲዮና የኦዲዮ ማስረጃዎችንም አዘጋጅተው ነበር። ይሁን እንጅ አቃቢህጎች ማስረጃዎቹ የደረሱዋቸው ዘግይቶ በመሆኑ በቂ ዝግጅት ለማድርግ ይችሉ ዘንድ ተጨማሪ ጊዜ ጠይቀዋል። የጋዜጠኛ ተመስገን ጠበቆች በእለቱ ቀረቡት ምስክሮች የመስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ቢጠይቁም አቃቢህጎች “የቪዲዮ ማስረጃዎችን በመመልከት ጥያቄዎችን ለማቅርብ እንችል ይሆናል” የሚል መከራከሪያ በማቅረባቸው ፍርድ ቤቱ ለግንቦት22፣ ቀን 2005 ኣም ተላዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ጋዜጠኛ ተመስገን ፍትህ እና ልእልና የተባሉ ጋዜጦችንና አዲስ ታይምስ የተባለ መጽሄት ለማዘጋጀት ቢሞክርም በገዢው ፓርቲ ጫና ምክንያት እንዲዘጉ መደረጋቸውን መዘገባችን ይታወሳል። አንዳንዶች ጋዜጠኛ ተመስገንን ያልተዘመረለት ጀግና ሲሉ ያወድሱታል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: