በጎንደር እስከ ሐሙስ የምርጫ ካርድ በኢህአዴግ ካድሬዎች ሲታደል እንደነበር ተገለፀ

Gonder-city

በብሔረዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመራጮች ካርድ መውሰጃ ቀን የተጠናቀቀው የካቲት 1 ቀን 2005ዓ.ም. ቢሆንም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በተለይም በጎንደር ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ እና አደባባይ ኢየሱስ ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች እስከ ሐሙስ ሚያዚያ 3 ቀን 2005ዓ.ም. ድረስ የመራጮች ካርድ እየሰጠ መሆኑን የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ምንጮች ገለፁ፡፡

እንደ ምንጮቻችን ገለፃ በከተማዋ የተለያዩ ቀበሌዎች የተሰማሩት የኢህአዴግ ካድሬዎች ቤት ለቤት በመዞርና በመንገድ ያገኙትንም ሰው በማስቆም የምርጫ ካርድ ማውጣት አለማውጣቱን በመጠየቅ ካርድ አላወጣንም ያሉ ሰዎችን በመመዝገብ ካርድ እያደሉ ይገኛሉ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ አርብ ሚያዚያ 4 ቀን 2005ዓ.ም. ለምርጫ ታዛቢዎች በሚል በጎንደርና በመቀሌ ከተሞች ያሉ የቀበሌ ሰራተኞች እየዞሩ ገንዘብ ለመሰብሰብ መሰማራታቸውን የከተሞቹ ነዋሪዎችም “ተወዳዳሪ በሌለበት የምርጫ ታዛቢ ለምን ያስፈልጋል?” በሚል ፊት እየነሷቸው እንዳባረሯቸው ተጠቁሟል፡፡ እስካሁን ባደረግነው የማጣራት ሙከራ በጎንደር ከኢህአዴግ ውጭ ምንም ዓይነት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ እንደሌለና ብቻውን ለውድድር እንደቀረበ ከስፍራው ምንጮቻንን አረጋግጠዋል፡፡

ይህንንም በሚመለከት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ምላሽ እንዲሰጠን ጸደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም አልተሳካም፡፡

fnotenetsanet

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: