ትግራይ አባይ ወልዱን ወደ ቁንጮነት ከመጡ ወዲህ ምን ትመስላለች?

ከአስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል

መቀሌ

0

ኣባይ ወልዱ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በህዝብ ላይ ጨካኝ እና ዘግናኝ እርምጃ እየወሰዱ የልማት ሰራዊት በማደራጀት የ 5 ኣመት እድገት እና ትራንስፎርሜሽን ግቡ እንዲመታ እናደርጋለን፤ የሚሊኒየም ግብ ካስቀመጥነው ጊዜ ገደብ ኣስቀድመን እንፈፅማለን ብለውናል:: ኣባይ ወልዱ ኣለቃ ፀጋይ በርሀን አስወገደው ስልጣኑን ከተቆጣጠሩ በኋላ በክልሉ እጅግ ብዙ ፀረ ዲሞክራሲ የሆኑ ድርጊቶችን ፈፅመዋል። እንደ ኣብነት ለመጥቀስ በሚያዚያ26/27/2005 ዓ/ም በትግራይ ደቡባዊ ዞን ወረዳ ሞኮኒ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ 7000 ኣባዎራዎች ከ ኣፂ ሃይለስላሴ እስከ ዘመነ ኣገዛዝ ኢህአደግ ሲኖርበት የነበሩ ከ 3 ትውልድ በላይ ጊዜ የኖሩበት ተተኪ

images

አቶ አባይ ወልዱ

እጅጉን የሚገርመውና የሚዘገንነው የራያና የዋጅራት ወረዳዎች በ36 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ ከ 120 ሺ ህዝብ ነዋሪ በላይ ለሁለት ኣመት ዝናብ ባለመዝነቡ በድርቅና በርሃብ በውሃ እጦት እየተሰቃዩ ተጨማሪ ካሳ ቤታቸው በማፈረስ ለባሰ ርሃብና ብርድ ፀሃይ በሽታ መጋለጣቸው ህሊና ላለው ሰው እጅጉን ዘግናኝ እርምጃ ነው፡፡

የራያ ህዝብ ህውሃት ራያን እንድ ደጀን ኣድርጎ 17 ኣመት ሙሉ ሲታገል ልጆቹ ሃብቱ ለህውሓት ያስረከበ ከመሆኑም በላይ ህፃን ኣዛውንት ሳይቀር ከህውሓት ሰራዊት ወደ ጦርነት ገብቶ ተሰውታል፡፡ ታጋይ በመሆኑ በኣንድ ቀን 15000 ቤቶች በደርግ ሰራዊት የተቃጠሉበት በሺ የሚቆጠሩ እንስሳ ዘቤት ተገድለውበታል፤ ተዘርፈዋል። በሺ የሚቆጠሩ ጉድጋድ የሞሉ ጤፍ እና ማሽላ በደርግ ተቃጥለዋል። የራያ ህዝብ ኣርሶ የሚያመርተው እህል በባህላዊ መንገድ በጥንቃቄ በተሰሩ ትላልቅ ጉድጓዶች ስለሚያስቀምጥ ለዚህ ሃቅ የሚያውቁ በኣሁን ጊዜ በሂወት ያሉ እነ ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ፣ ጀነራል ታደሰ ወረደ፣ ጀነራል ሰዓረ ሞከነን ሌሎቹም ኣሉ፡፡ ጀነራል ሓየሎም/ፈንቅል/ ኣሁን ቢኖር ኖሮ ይህ የራያ ህዝብ ስቃይ ሲያየው ምን ስሜት ይፈጥርባቸው ይኖር ነበር? የራያ ህዝብ ሃየሎምን እንዴት ይወዱት እንደነበር የሚያውቁ ሊመሰክሩ ይችላሉ። ሓየሎም በራያ ህዝብ ሁለት ስም ነበረው ኣንደኛው ሓየሎም ሲሆን 2ኛው ፈንቅል ይሉት ነበር በኣሁኑ ጊዜ በራያ /መኮኒ/ ከ1972ዓ.ም እስከ ዛሬ የተወለዱት ወጣቶቸ እና ህፃናት ሓየሎም ወይም ፈንቅል የሚባል ስም ያወጡላቸው በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ናቸው እስከ 2000 ዓ.ም ሓየሎም የሚባሉ ወጣቶች 2300 ደርሰው ነበር እነፈንቅልም ብዙ ናቸው ይህ የሚያሳየው የራያ ህዝብ ለፍትህ ለነፃነት ብሎ ከህውሓት ጎን ተሰልፎ ምን ያህል መስዋእትናት እንደከፈለ የሚያመላክት ነው። ኣባይ ወልዱ ግን ራያ በነበሩበት የራያ ወፍራም ጎጎ በልተው ነበር የኖሩት። ግን ደግሞ ጨከኑበት፤ በጠራራ ፀሃይ ቤታቸውን ኣፈረሱባቸው። የራያ ህዝብ መስዋእት ኣባይ ወልዱ ምስክር ናቸው። በኣላማጣም በተመሳሳይ ለብዙ ኣመት የኖሩበት ወልደው ከብደው ሃብት ኣፍርተው ዘመናዊ እፅዋትና ኣትክልት ተክለው ኣሳድገው ሲኖሩ ሃብታቸው ቤታቸው የኣባይ ወልዱ የ ኣፍራሽ ልማት ሰራዊት በግሪደር እና በሎደር ሲያፈርሱባቸው ኣናፈርስም ብለው በመቃወም የመቀሌ ኣ.ኣ መንገድ በመዝጋት ሰላማዊ ሰልፍ ቢያደርጉም ኣቶ አባይ ወልዱ ኮማንዶ ፖሊስ ኣስለቃሽ ጋዝ በመቶኮስ በመደብደብ ወደ እስር ቤት በማጎር ፈቱት። እስካሁንም በማይጨው ወህኒ ቤት ታስረው ይገኛሉ። ለምሳሌ ሻምበል ዳርጊ ነዋሪነቱ ኣላማጣ ይጠቀሳሉ፡፡ የኣለማጣ ህዝብም ልክ እንደ መኮኒ ህዝብ ለፀሃይ ለብርድ ለዝናብ ተጋልጦ ንብረት ቤት ኣልባ ሆኖ ቀርተዋል፡፡ እስካሁንም ምንም መፍትሄ ኣላገኝም የጨለማ ኑሮ እየኖረ ነው፡፡ ቀደም ብሎም ይህ ድርጊት በመቀሌ በገፊህ ገረብ በ ኣዲ ሃ/ኣዲ ዳዕሮ/ በሮማናት ላጪ ደብሪር ኩሃና ኣካባቢዋ የሚኖሩ በ 10.000 የሚቆጠሩ ኣባዎራዎች ከ6-10 ኣመት በህጋዊ መንገድ ገዝተው ቤት ሰርተው የኖሩበት በኣባይ ወልዱ ይፍረስ ተብሎ ሲታዘዝ ህዝቡ ተቃውሞ ሲያሰማ በዛን ጊዜም የፌዴራል ፖሊስ ድብደባ ጥይት በመተኮስ ኣስለቃሽ ጋዝ በማፈን ብዙ ህፃናቶች እንደተሳቃዩ በወቅቱ ተነግራል፡፡ ኃላ የተሰራ ቤት በዶዘርና በኣባይ ወልዱ የኣፍራሽ ሀይሎ ስራዎች በቢሊዮን ብር የሚገመት ቤት ፈርሰዋል በመቀሌ ኣፓርታይድ መንደር ግን ባለስልጣናትና ጥቂት ባለሃበቶች ህገወጥ በሆነ መንገድ ተሰርቶ ምንም እርምጃ ኣልተወሰደበትም በሽሬ እንዳ ስላሴም የመኮኒ እጣ ፈንታ ደርሶባቸው የዚህ ህዝብም ተቃውሞ ኣሰምቶ የባለስልጣኖች ኣቤቱታ ኣቅርቡ ውሃ ዘግኖ ቀረ፡፡

ቦታ ሳይሰጡ፣ ግምት ሳይከፈላቸው ሆን ብለው ግምት እንዳይከፈሉ ህገወጥ በሚል ሽፋን
የማይጨው ከተማና የመኮኒ ከተማ ኣካባቢያዊ ፖሊሶች ታጣቂዎች ምልሻዎች እንዲሁም የኣካባቢው
ቀበሌ የህውሓት ካድሬዎች በማስተባበር 7000 ኣባወራ ነዋሪዎች የሚኖርበት ቀበሌ በመግባት ሰዎች ንብረታቸው ለራሳቸው ሳያስወጡ በእነዛ ኣፍራሽ ግብረ ሃይሎች ቤታቸው በማፍረስ ህፃን ኣዛውንት እርጉዞች ያለባቸው እቃ በፀሃይ እና በዝናብ እንዲበላሽ ተደርጋል፡፡

የሚገርመው ነገር ግን ከፋፍለህ ግዛ ከሚል ፈሊጣቸው የአንድን ቀበሌ ህዝብ የሌላኛውን ቀበሌ እንዲያፈርሰው በማድረግ በህዝቦቹ መካከል የማይጠፋ ቂም በመፍጠር የማይጠፋ አሻራ ጥለዋል

የገፊሕ ገረብ ኣላማጣ መኮኒ ሰዎች ፍትህ ለማግኘት ከወረዳ ክልል ድረስ መጥተው በሰልፍ በተወካዮቻቸው ቢያመለክቱም ያገኙት መልስ የፌደራል ፖሊስ ዱላ እና ስድብ ነው በተለይ የመሆኒ ሰዎች ሁለት ጊዜ ከ 100 በላይ የመጨረሻ ጊዜ ግን 200 ተወካዮች በትግራይ ክልል ቢሮ በር ለ4 ቀን በፌደራል ፖሊስ ተከበው ሰንብተው በመጨረሻ በሃይል ተበትነዋል ወደ መቀሌ የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን ና እንባ ጠባቂ ቢያመለክቱም ያገኙት መልስ ግን የነአባይ ወልዱ ዓይነት ነበር፡፡ምክንያቱም እነሱም ካድሬዎች ናቸውና

ለመሆኑ ማነው ህገወጥ መንግስት ቤት ሰሪዎች

በኔ እምነት ቤት ሰሪዎች ምንም ወንጀል የለባቸውም ህገ ወጠጥ ገዢ የሚባለው የመንግስት መዋቅር የሆነው የቀበሌ ሊቀ መንበር የቀበሌ ፍርድቤት የሽያጭ እና ገዢ ውል ኣስፈፃሚ የባለንብረትነት ሰነድ ሰጥቶ እያለ እንዴት ብሎ ህገ ወጥ ይሆናል? ህገ ወጥ የሚባሉ ኣቶ ኣባይ ወልዱ እና መዋቅራቸው ናቸው፡፡ በተጨማሪ ህገ ወጥ ነበር ካሉ የመሆኒ 2 ና3 ትውልድ የኖሩበት ነው እንደነ ገፊሕ ገረብ ኣላማጣ ሽሬ ግን ከ10 ኣመት በላይ የኖሩበት ነው፡፡ ቤቱ ሲመሰረት ሲሰራ እያዩ ምን ይሰሩ ነበር? መንግስት ስልጣን የሰጣቸውን ለዚህ ነው ተጠያቂውች ኣባይ ወልዱና መዋቅራቸው ናቸው ያልኩት ፕሬዝደንት ኣለቃ ፀጋይ በርሄ በስልጣን በነበሩበት ጊዜ ምንም እንካን በሌላ ኣላማቸው እና ፖሊሳቸው ኣሰራራቸው ከኣባይ ወልዱ የተለዩ ባይሆኑም የገፊሕ ገረብና የሌሎች ቦታዎች እንደ ትልቅ ኣጀንዳ ቀርቦላቸው ይፍረስ ብለው ከማዘዛቸው በፊት ከሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸው ሆነው ገፊሕ ገረብ ሄደው ሲመለከቱት የነባሩ መቀሌ ያህል ሰፊ ከተማ ሆኖ ሲያዩት ወይም ሲመለከቱት ኣግራሞትን ፈጥሮላቸው ይህ ማፍረስ ከባድ ነው ይህን የሚያህል ከተማ ሲታነፅ ዝም ብለን ቆይተን ኣሁን ከተማ ሙሉ ይፍረስ ማለት ኣይቻልም ስህተቱ ከራሴ ጀምሮ የተፈጠረ ነው፡፡ ይህ ከማፍረስ እዛው ሳለ ማስተካካል ይሻላል ብለው እንድተመለሱ ይነገራል፡፡ በቦኩሌም የኣለቃ ፀጋይ ውሳኔ የተሻሉ ጨቃኝ መሪ ነው የምላቸው ኣባይ ወልዱ ግን ይቺ ኣገር ከማን ጋር ሆኖ እንደሚኖሩበት ለብዙ ህዝብ የማይጠፋ ጠባሳ ፈጥራል፡፡በዘመነ ስልጣን ኣባይ ወልዱ የትግራይ ህዝብ መጠልያ የማግኘት ህገ መንግሳታዊ ዜጊኔታዊ መብቱ ተነጥቃል ፡፡ ለዚሁ እንደ ምሳሌ ለመጥቀስ ማንም ዜጋ በእጣ በሊዝ በማህበር መሬት እየተሰጠው ቤት ሰርቶ ዩኑር የሚል ፖሊሲ በመጣስ ከ 10.000 በላይ ኣባዎራዎች በማህበር ተደራጅተው ገንዘባቸው ከ4 ኣመት በላይ ባንክ ኣስቀምጠው መሬት ይሰጠናል በለው እየጠበቁ ድንገት መሬት ኣይሰጥም በሊዝ ወይ ኮንደሚኒየም ግዙ ገንዘባችሁ ኣውጡ ተብለው ኣቤት ቢሉ ሰሚ ጆሮ ኣላገኙም በመቀሌ ብቻ 7800 ኣባወራ በማህበር የተደራጁ እንዲበተኑ ተደርገዋል በኣሁኑ ጊዜ የቤት ኪራይ ዋጋው ሰማይ ተሰቅላል በኣንድ ክፍል ቤት ከ 10 ሰዎች በላይ ተጣቦ የሚኖር ህዝብ ብዙ ነው፡፡በዘመነ ኣባይ ወልዱ ኣገዛዝ የትግራይ ነጋዴ ባለሃብት ፍትሃዊ የግብር ኣከፋፈል ባለመኖሩ ንግዱ እየዘጋ ለስደት ተዳርጋል ግብር መክፈል ዜግኔታዊ ግዴታ ነው ነገር ግን በትግራይ ክልል የንግድ ህ/ሰብ ገቢና ወጪ ያላገናዘበ ግብር መተመን ያለኣቀሙ ገንዘብ እንዲከፍል በማድረግ ህዝቡ ከኣቅሙ በላይ ስለሆነበት ያለው ንብረት ሽጦ ከፍሎ ንግድ ፍቃዱ ዝጉልኝ ወደ ስደት ነኝ ቢልም መዝግያ ሰነድ ተከልክሎ ብዙ እንቅፋት ደርሶበታል፡፡ ኣባይ ወልዱ ኣንድ ባለሃብት ወይም ነጋዴ ከክልል ወይም ከሃገር ከሸሸ ጉዳቱ ቢረዳቸው ምን ነበር?

በሌላ በኩል በትግራይ ያነሰች ክልል አነስተኛ ህዝብ ያላት 1.8ቢሊዮን ብር ግብር ሰብስባ ከሁሉም ክልሎች የላቀ ግብር ሰብስባል በማለት 1ኛ በመሆን የሁሉም ክልሎች ፋናንስ ሃላፊዎች መቀሌ መጥተው ተሞክሮው ቀስመው ተምረው ሄዱ ተባለ፡፡2ኛ በህውሓት 11ኛ ጉባኤ እንደ ትልቅ ድል ተቆጥሮ እኛ ከሁሉም ክልሎች በመብለጥ 1.8 ቢሊዮን ብር ግብር ሰብስበናል በማለት ኣባይ ወልዱ በሃወልቲ ሰማእታት መድረክ ተኮፈሶወ ተናግረዋል ምን ያህል የባለሃብት ና ነጋዴ ጭንቅላት እንደገደሉ ይረዳቸው ይሆን በእኔ እምነት ኣባይ ወልዱ በጤናቸው ናቸው? ሃቁ ግን የትግራይ ነጋዴ ጭራሹን ኣገር ለቆ የጠፉ ኣሉ፡፡ ክልል የቀየሩም ኣሉ ሃብታም የሆኑ ደግሞ ውጪ ድረስ የሄዱ ኣሉ፡፡ በተለይ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ነጋዴዎች ፍፁም ደህይተው የጠፉ ኣሉ፡፡ በትግራይ ያሉ ግልጋሎት ሰጪ ድርጅቶች ጋራጆች ወርክሾፕ ለቀው ለመጥፋት ወይም ስራቸው ለቀው ወደ ሌላ ስራ ለመሰማራት ጋዛቸው እየጠቀለሉ ናቸው፡፡

የመንግስት ሰራተኛ በንሮ ውድነት ችግር ላይ እያለ የህውሓት ኣባል ካልሆንክ የኣባልነት መዋጮ ካልከፈልክ ኣትታመንም እየተባለ ከስራው እንዳይፈናቀል በስጋት ተውጦ ይገኛል የተቃውሞ ቃል ካወጣ የት ይኖራል፡፡ በየቤቱ በየቢሮው ተደብቆ በሃሜት ስሜቱን ያተነፍሳል በት/ቤቶች በኣንድ ለ5 በህወሓት ህዋስ ኣደረጃጀት በተጨማሪ በት/ቤት ያሉ ተማሪዎች እና ኣስተማሪዎች A B C D በሚል መስፈርት በማስቀመጥ እጅግ ታማኝ የሆኑ ተማሪዎችና ኣስተማሪዎች ቅድመ ግንባር ወይም በወታደራዊ ኣጠራር ቀዳሚ መምሪያ የሚል ስም ተሰጥቶዋቸው ህውሓት ኣድርጉ ባላቸው ሊያደርጉ በሚችሉበት ተደራጅተው ይገኛሉ በቅድመ ግንባር ያልተሰለፉ ኣስተማሪዎች እና ተማሪዎች ታማኝነታቸው ጥያቄ ውስጥ ገብታል ይህ ተግባር ህግ መንግስትም በመጣስ በሁሉም ትምህርት እያደገ ያለ ነው፡፡ለሁሉም እንደ ሞዴል የኣፄ የውሃንስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ይጠቀሳል፡፡

የኣባይ ወልዱ ኣነስተኛ እና ጠቃቅን ተቃማት ተዳክመው በእዳ ተይዘው ጭራሽ እየከሰሩ ከክልሉ ሲሰደዱ በጣም ጥቂቶች ደግሞ ለሞት እያቃሰቱ ይጋኛሉ የኣባይ ወልዱ ፈላጭ ቆራጭ መንግስት ግን ትግራይ በልማት የሰጠመች በማለት በቴሌቭዠን መስኮት

ይኮፈሳሉ፡፡ የሚገርመው የመንግስትና የፓርቲ ሬድዮ ጣብያ ኤፍኤሞች ቴሌቨዠን ጋዜጦች በሬ ወለደድ ኣይነት እየደስኮሩ የሌለ ልማት የሌለ መብት ኣለ ይሉናል፡፡ ህዝብ ዳኛ መሆኑን እያወቁ

በዘመነ ኣገዛዝ ኣባይ ወሉ የውሸት ልማት በሽ ሆናል በዚህ የያዝነው ኣመት 50% ታራሽ መሬት/ 650 ሄክታር መሬት /በመስኖ በልማት 49 ሚሊዮን ኩንታል ኣትክልትና ፍራፍሬ እናመርታለን ብለው ነበር ኣሁን የውስጥ ኣዋቂዎች እንደሚሉት 10% ኣላለማም በየትኛው ውሃ ሊለማ ና ሰውና እንስሳ ዘቤት የሚጠጡት ውሃ ኣጥተው እየተቸገሩ፡፡

በምስራቃዊ ዞን ኣፅቢ ወንበርታ ወረዳ 36ሺ ሄክታርታራሽ መሬት በመስኖ ኣልምተናል ብለዋል እንደ ሞዴለ በማሰቀመጥ ለመሆኑ በኣፅቢ ወንበርታ 36ሺ ሄክታር ታራሽ መሬት ኣለ ወይ እስቲ ኣፅቢ ወንበርታ የምታውቁ ዜጎች መስክሩ፡፡

በትግራይ ክልል በተደረገው የደን ተከላና እንክብካቤ 2.5 ሚሊዮን ሄክታር በኣሮንጋዴ ተሸፍነዋል ብለው ኣባይ ወልዱ ህወሀት ጉባኤ ሪፖርት አሰምተዋል ግን በጥናት የተመሰረተ ዳታ ልጠቁም . በደርግ ስርኣት ጊዜ በኢ/ያ ደረጃ የነበረ የደን ሽፋን ከ 3-5% ነበር ይላል ጥናቱ በዘመነ ኣገዛዝ ኢህኣደግ የደኑ ሽፋን ወደ 8/10% ኣሻቅባል ይባለል፡፡ ይህ ኣሃዝ ወደ ትግራይ ሲመነዘር ፍፁም የማይሆን ነገር ነው አባይ ወልዱ በጉባኤ ሲናገሩ 2.5 ሚሊዮን ሄክታር 47.16% በደን ተሸፍዋል ብለዋል ሃቁን እንመልከት፡፡

የትግራይ ክልል ታራሽና የማይታረስ መሬት ከተሞችና በገጠር ቤቶች ያረፉበት ለግጦሽ የሚሆን መሬት ከ5.1 እስከ 5.3ሚሊዮን ሄክታር ኣይበልጥም ከነዚህም 1.3ሚሊዮን ሄክታር ታራሽ መሬት ለግጦሽ የተመደበ መሬት 300ሺ ሄክታር የከተማና የገጠር ቤት መስርያ ያረፈበት መሬት 400ሺ ሄክታር ደግሞ ለግጦሽ ኣርሶ ኣደሩ የሚጠቀምበት ነው፡፡ኣባይ ወልዱ ኣለማሁት የሚሉት2. 5ሚሊዮነ ሄክታር ነው፡፡ ኣሁን ደን የሌለው የተራቆተ መሬት 1ሚሊዮን ሄክታር ብቻ ነው የሚሉት ያሉ ያበደን ተሸፍዋል የሚሉን የትግራይ መሬት የቆዳ ስፈት 47.16% ነው ይህ ከሆነ ኣባይ ወልዱ ለሽልማት መቅረብ ኣለባቸው ግን ደግሞ ያለ ውሸት ነው ይህ ደግሞ የትግራይ ፕላን ቢሮና የመሬት ኣስተዳደር የአርሻ ቢሮ የሚያረጋግጡት የሚሆን ሀቅ ነው ስለዚ ኣቶ ኣባይ ውሸተ ደጋግመው ስትናገሩ ሃቅ ይሆናል የሚል የኣንባገነንኖች ፋሽሽቶች ኣነጋገር ለዚህች ኣገር ኣይጠቀማትም በኣሁኑ ጊዜ የኢትዮፕያ ህዝብ ከመንግስት መሪዎች ኣልፎ በንቃትና መረጃ እውቀቱ መጥተዋል፡፡

4.3 ሚሊዮን ህዝብ ፍትህ ነፃነት መልካም ኣስተዳደር የህግ የበላይነት ኣጥቶ ያማርራል ኣባይ ወልዱ ግን ሁሉም ነገር ተንበሽብሻል እያሉን ነው በትግራይ ታሳሪ ወጣት ብዙ ነው እንደ ሽሬ ያሉ የነበረው እጅግ ሰፊ እስር ቤት ኣሁን ብዙ ሚሊዮን ብር በመመደብ እስር ቤት እያሰፋፉ ናቸው፡፡

በትግራይ ምሳራቃዊ ዞንና በደቡብ ራያ ዓዘቦ በማእከላዊ ዞን ወረዳ በኢሮፕ ወረዳዎች በሞቶሺ የሚቆጠሩ ህዝብ በረሃብ በድርቅ ውሃ ጥም ህዝቡ እየተጎዳ እንስሳ እየሞቱ የኣባይ ወልዱ መንግስት ግን ስንዴ ድርቅና ረሃብ በመደበቅ ለዱቄት ፋብሪካ ይቸበቸባል ደግሞ ኣድልዎ ባለበት .ለመለሰ ጉባኤ ለእድገትና ለእመርታ ለማጀብ ተብሎ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ማባከን ምን ያህል ጨካኞች መሆናቸው ያሳያል፡፡ ደርግ በ1977ዓ.ም ለኢስፓ ጉባኤ ምስረታ 10 ሚሊዮን ብር የተገዛ ዊስኪ ከእንግሊዝ ገዝቶ ኣግብታል ተብሎ እንዳልተነገረ በዘንድሬ በኢሃደግ ኣባል ድርጅቶችና የኢሃደግ ጉባኤ በመቶ ሚሊየን የሚቆጠሩ ገንዘብ ማባከን ለኣጀባ ተብሎ የህዝብ ተሽከርካሪዎች በግዳጅ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ ማድረግ ትልቅ ግፍ ነው፡፡ የመንግስት ቡዙሃን መገናኛ ለኣንድ ፓርቲ 24 ሰኣት ዲሱኮራቸው ሲያሰሙ ህዝብ ኣሰለቸ፡፡

ገበሬዉ በማይፈልገው ኣስደዳጅ ፓኬጅ በማስገባት ለእዳና ለኪሳራ መዳረግ የግብርና ባለሞያ ያላመኑበት የማይተገበር የእርሻ ስራ ማቀዱ ለሁሉም ሙያተኞች ተቃውሞ ፈጥራል፡፡ በገጠሮች የእርሻ ምርት ቀነስ እያለ ነው ኣርሶ ኣደር ኣልፎለታል አያሉ መዋሸት ሃቁ ግን የትግራይ ወጣት የተማረም ያልተማረም ኣስተማሪዎች ወደ ስደት ፈልሳል ምስራቃዊት ትግራይ እንደ ኣብነት ወደ ሱዳን እንድሚደርስ ወጣት ኣስተማሪዎች ወደ ስደት ፈሳል ምሳራቃዊት ትግራይ አንደ ኣብነት ወስደን እድሜ ደረስ ወጣት ኣስተማሪዎች ብንወስድ ባገር የሉም ትምህርት ቤቶች ኣስተማሪ ታጥቶ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ፈተና የወደቁ እያስተማሩ ይገኛሉ ለዚሁ እንደ ማስረጃ ለወረዳና ቀበሌ ምርጫ ሊመረጥ ተብሎ የተቀመጠ ከታ ስላልሞላ ኮታ ለሞምላት ተበሎ የ 13.14 እድሜ ህፃናቶች ለመራጭነት ተመዝግበዋል ለዚሁ ለማረጋገጥ የሚፈልግ ዜጋ ካለ የሃውዜን ወረዳ ሄዶ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ሃውዜን እንድ ሞዴል ኣስቀመጡኩት እንጂ በመላው የትግራይ ዞኖች ወረዳ ቀበሌም ተሰርታል፡፡

የትግራይ ህዝብ ኣርሶ ኣደር ሙሁር ተማሪ ነጋዴው ተማሪ ሰግቶ ተርበድብዶ ኣሜን ብሎ እንዲገዛ እየተደረገ ነው፡፡ የተቀቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ኣበላት ከ መንግስት ስራ መፈናቀል ማስር ድርጅቶች ከሚሰጡት ኣገልጉሎትና ጥቅማ ጥቅም መገለል በስለላ ድህንነት ክትትል ማስገባት ጭንቀት መፍጠር የኣባይ ወልዱ ዋነኛው ስራ ነው፡፡ በኣሁኑ ጊዜ በትግራይ ክልል ድህንነት ሰላድች ለኣንድ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ይህ ደግሞ ህዝብን በሰላል መዋቅር መከበብና ስጋት መፍጠር ለድርግም ለሁሴን መባረከም ኣልጠቀምባቸውም ህዝብ ሃያል ነውና ኣሸነፋቸው፡፡

ታድያ የሌሎች ክልሎች የፋይናንስ የእርሻ የፀጥታ የፍትህ ኣባላት የከተማ ልማት ሰራተኞች ተሞክሮ ሊወስዱ ተብለው ለትራንስፖርት ውሎ ኣባል ተከፍሎ የኣባይ ወሉ ተሞክሮ መውሰድ ማለት በህዝባቸው ለስደት ከማድረግ ምንም ውጤት የለውም፡፡ ስለዚህ ከትግራይ ሰው እንዴት እንደሚታፈን ተሞክሮ መውሰድ ለህዝብም ቀሳሚዎች ኣየጠይቅም፡፡

በመጨረሻም ላሳስበው የምወደው ሁሉም ነገር የሚገነዘብ የኢትዮፕያ ህዝብ በተለይ ደግሞ በህዝብ ገንዘብና ሃብት ተምሮ ለተለያዩ ደረጃ የደረሰ ሙሁር ክፍል በመንግስትና በመንግስት መዋቅሮች ባለስልጣኖች ብዙ ቀዳዳ ህገ መንግስት ቢሆንም ከባድ መስዋእት ከፍሎ ያፀደቀው ስልጣናቸውን ተገን ኣድርግው ህገ መንግስት መስረት በማደርግ በሰላማዊ ዲሞክራሲያዊ መንገድ መርቶ ነገሮች እዝንዲከሰቱ ለማድረግ መስራት ኣባላት፡፡

ሌላ የሃገራችን ህዝቦች በየክልሉ ይደረስ ያለው ኣፈና የ 80 ሚሊዮን ህዝብ ኣፈና ስለሆነ ኦሮሞ ህዝብ በኣማራ ወይ በትግራይ በህዝብ ላይ ኢፍትሃዊ ተግባር ሲፈፀምበት በጫንቃው ይድርስ እንዳለ ቀጠሮ መቃወምና ጥያቄ ማስነሳት ኣለበት፡፡ የኣማራ የትግራይ የኦሮም የሶማል የኣፋር ህዝብም በደቡብ ህዝቦች በጋንቤላ በቤንሻንጉል ለሚደርስ በደለ እንደዛ መቃወም ኣለበት ካለበለዝያ ኣማራው ወደሱማል በትግራይ ወይ በኦሮም ጉዳት ሲደርስ በሩቅ ሆኖ በመመልከት ምን ኣገባው በመደገፍ ለወገኖች እንደ መካድ ይቆጠራል፡፡

ይህ ያልኩበት ምክንያት በኣሁኑ ጊዜ ይቅርና ክልል ለክልል ብሄር ሊከራከርለት ሳይቀር በክልል ውስጥን ዞን ለዞን ወይ ወረዳ ለወረዳ ሲተሳሰብና ሲረዳ ኣይታም፡፡ ለዚሁ እንደ ማስረጃ ቀደም ሲል በቤንሻንጉልና በደቡብ የኣማራ ክልል ዜጎች ሲፈናቀሉ በሌላ ክልል ያለው ወገናቸው ጥያቄ ሲያነሳ ኣለታየም፡፡ ኣቅርቦ ጊዜ በመቀሌ ኣላማጣ ሙሁኔ የደረሰው የህዝብ ሃብት ውድመት በዚዝች የደረሰ የሰብኣዊ መብት ጥሰት ከኣጎራባች ዞኖች ወረዳዎች ቀበሌዎች መንግስት ለፈፀመው ድርጊት ሲቃወም ኣልታየም በትግራይ የተፈፀመው ኢፍትሃዊ የግብር ኣከፋፈልና የባለሃብቶች ንግድ ህብረተሰብ መፈናቀል በሌሎች ክልሎች ያሉ ንግድ ህብረተሰብ ተቃውሞ ሲያሰሙ ኣልታየም ነገ ጥዋት ግን በትግራይ ንግድ ህ/ሰብ የተፈፀመው ድርጊት ነገ ወደነሱ እንደግብኣት ወደነሱ ይጛዝ እንዳለ እያወቁ ስለዚህ በኢትዮፕያ ያለው ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ችግሮች ሊፈቱ ከሆኑ ህዝብ ችግሩ ለመፍታት በመተማመን በመተሳሰብ ኣንድነት ኣጠናክሮ መፍትሄ ማግኘት በእጅ ነው ያለው፡፡ በተለይ ደግሞ ሙሁር ህብረተሰብ ሙሁራዊ ግዳጁ ከፈፀመ ሁሉም ነገር ሊፈታ ይችላል፡፡

ቸር ሰንብቱ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: