የአንድ ለ አምስት ጠርናፊዎች ጭምር አለመምረጣቸው ኢህአዴግን አስደንግጦታል

EPRDF-logo

ኢህአዴግ የሚያዚያ 13 ቀን 2005ዓ.ም. የተደረገውን የአዲስ አበባና የደቡብ ክልል ወረዳዎች ምክር ቤት ምርጫ 1 ለ 5 ጥርነፋ ኃላፊነት የተሰጣቸው ግለሰቦች ግዴታቸውን አልተወጡም በሚል በግምገማ እያስጨነቃቸው መሆኑ ተሰማ፡፡ ቀደም ሲል ሚያዚያ 6 ቀን የተደረገውን የአዲስ አበባ፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና የአካባቢ ምርጫ ከዚህ በፊት ኢህአዴግ የልማት ሰራዊት ሲል ከህዝብ ግብር በሚገኝ ገንዘብ ደመወዝ እየከፈለ ለኢህአዴግ ፖለቲካ ቅስቀሳ እንደሚሰሩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታ ቢያቀርቡም የ2005ዓ.ም. ምርጫ ላይ ግን ኢህአዴግ እራሱ ማስተባበል ያልቻለውን የምርጫ ሰራዊት በማለት 1 ለ 5 ጥርነፋ ስራ በይፋ አሰርቷቸዋል፡፡ ሆኖም ኢህአዴግ ከጠርናፊዎቹ የጠበቀውን ውጤት እንዳላገኘ ተጠቁሟል፡፡ በዚህም ምክንያት በተለይ በአዲስ አበባ ሳምንቱን ሙሉ እስከ ሚያዚያ 13 ቀን 2005ዓ.ም. ምርጫው እስኪጠናቀቅ የየወረዳ ኃላፊዎችና የጥርነፋ ኃላፊነት የተሰጣቸው የኢህአዴግ አባላት በየቤቱ እያንኳኩ ቃል የገቡላቸውን “ሄዳችሁ ምረጡ” የሚል ትዕዛዝ እየሰጡ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

ጠርናፊዎቹም “የገባችሁትን ቃል አላከበራችሁም” በሚል በተለይ በአዲስ አበባና ደቡብ ክልል ለሚያዚያ 13ቱ ምርጫ በየቤቱ እየዞሩ እንዲቀሰቅሱና የያዙትን ካርድ ይዘው ሄደው ድምፅ እንዲሰጡ በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት አልተገበራችሁም በሚል አሁንም ሄዳችሁ በአግባቡ አልቀሰቀሳችሁም፣ ቀደም ሲል ቃል ያስገባችሁትም ቢሆን የውሸት ነው ስለዚህ ተልኳችሁትን አልፈፀማችሁም ሲል ቁጣውን ያወረደባቸው መሆኑንና ወደፊትም እርምጃ ሊወስድባቸው ማሰቡንም የፍኖተ ነፃነት ምንጮቻችን አስታውቀዋል፡፡ ይህንንም ሁኔታ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ባልደረባ በተግባር የተመለከተ ሲሆን በተለይ የየወረዳው ሰራተኞች በየቤቱ እያንኳኩ በማስከፈት ወረቀትና እስክሪብቶ ይዘው የትኛው ምርጫ ጣቢያ ነው ካርድ የወሰዳችሁት? ከቤታችሁ ስንት ሰው ካርድ ወስዷል? ከመካከላችሁ ሄዶ ድምፅ ያልሰጠ አለ እያሉ ይናገሩ እንደነበር ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በአዲስ አበባ አንዳንድ ወረዳዎች ጠርናፊዎችም ጭምር ድምፅ ለመስጠት አለመሄዳቸው ይበልጥ እንዳበሳጫቸው ምንጮቻችን አስታውቀዋል፡፡ ከዚህና ከውጤቱ ጋር በተያያዘ ያነጋገርናቸው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ጸሐፊ አቶ ወንድሙ ጎላ በበኩላቸው ምርጫው በሰላም ከመጠናቀቁ በስተቀር የተለየ ነገር የለም፤ ውጤቱን በሚመለከት ውደ ፊት ተጣርቶ ይፋ ይደረጋል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

fnotenetsanet

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: