ልጄ በድብቅ እስርቤት ግፍ እየተፈፀመበት ይገኛል

 መከራው ከእኔ ኣልፎ ልጄም ስቃይ ወራሽ ሆነ

ከኣስገደ ገስላሴ ወ/ሚካኤል

አሕፈሮም አስገደ ገ/ስ

የ26 አመቱ ወጣት ልጄ ኣሕፈሮም ኣስገደ ገ/ስላሴ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምሩቅ ሲሆን ስራው ደግሞ ኮምፕዩተር “ኔትወርክ” እና “ሃርድዌር ሜንተናንስ” ያጠቃልላል።

ይህ ልጅ ከ 4ወር በፊት በኣንድ ካፌ ቡና እየጠጣ እያለ ሁለት ሲቢል ሰዎች እንፈልግሃለን ኣሉት። እሱም ሰላማዊ ሰዎች መስለዉት ተነስቶ ሲሄድ በማይስማ መንገድ ቀጥ ብለሀ ወደ ወሰድንህ ሂድ ብለው ወደ ትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ወስደው ለኣንድ ቀን ኣስረው ደብቀዉት ዋሉ።

ማታ በጨለማ በመቀሌ ምስራቃዊ ኣቅጣጫ ከ ባሎኒ ኣለፍ በሎ የሚገኘው ጎድጓዳ ኣካባቢ ከእንዳየሱስ ቤተክርስትያን በስተ ምዕራብ ከኣሪድ ዩንቨርስቲ ግርጌ የሚገኝ ድብቅ እስርቤት ወይም በመቀሌ ህዝብ ኣነጋገር ቤርሙዳ እይተባለ የሚጠራ በትግራይ ባለስልጣኖች ደሞ 06 (ባዶ ሽዱሽተ) የሚባል ስም ያለው ለ ኣራት ቀን ያህል ገርፈው ጀርባውን በምን እንደመቱት የማይታወቅ ቆስሎና በስብሶ መጣ።

በዛን ወቅት ምን ሆንክ ብለን ብንጠይቀው ወድቄ ነው ኣለ። እኛም ግርፋት ወይም ቶርች እነደሆነ ተረድተናል። የኋላ ኋላ ግን ቀስ ኣድረገን ጠይቀነው ግን የደረሰብኝ እንዳልነግራችሁ መርማሪዎቹና ሃላፊዎቹ ገርፈዉኛል በለህ ከተናገርክ ሂወትህን እናጠፋታለን እንዳሉትና ለወላጆቹ ኣለመናገሩ ሰግቶ መሆኑ ገልፆልናል። እኛም በግልፅ ኣቤት ለማለት ግዜ ኣልፏል ብለን ችላ ብለን ቆየን፤ መሆን ግን ኣልነበረበትም ልጄም በሰላም ስራው እየሰራ ነበር፡፡

የኣሁኑ ይባስ ልጄ በ 16/8/2005 ዓ.ም ዕለተ ሮብ በኣምስት ሰኣት ላይ ከስራ ወጥቶ ቡና እየጠጣ እያለ ፖሊሶች መጥተው ኣስረው በቀዳማይ ወያኔ ወረዳ ፖሊስ ጣብያ ኣስገቡት፤ መታሰሩ ሰምተን ስንጠይቅ መጀመርያ የለም ኣሉን። ቆየት በለው ግን ኣለ ግን ልታገኙት ኣትችሉም ኣሉን። የምወስድለት ምግብም ፖሊሶች ተቀብለው ይወስዱታል፤ ይብላው ኣይብላው ኣናውቅም።

በህገመንግስት ድንጋጌ መሰረት ኣንድ ተጠርጣሪ በፖሊስ ሲያዝ የፍርድ ቤት ትእዛዝ መኖር ኣለበት። 2ኛ ከፖሊስ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በ48 ሰኣት ውስጥ ወደ ፍርድ ቤት መቅረብ ነበረበት ይህ ግን እስካሁን በ120 ሰኣታት ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ለምን ልጃችን አታገናኙንም? ከጠበቃም ይገናኝ እያልን ስንጠይቅ ኣናሳይም በማለት ከልክለውን ሰንብተዋል። ኣሁን ግን ልጃችን ከዛ ህጋዊ ህዝብ የሚያውቀው ፖሊስ ጣብያ ኣውጥተው ደብቀዉታል። ወደ ህጋዊ ያልሆነ ድብቅ እስርቤት ወስደው የስቃይ ምርመራ ይፈፅምበታል የሚል ጭምጭምታ ሰምተን ወደ ታሰረበት ወረዳ ፖሊስ ጣብያ ሄደን ስንጠይቅ ታችኞቹ ፖሊሶች የለም ከዚ ልቀቁ ኣሉን። እኛም ተስፋ ሳንቆርጥ የወረዳ ፖሊስ ጣብያ ዋና ኣዛዠ ኮኖሬል ኣንድነት ልጄን የት ወሰዳችሁት ብየ ስጠይቀው ወደ 06 ሄዶል ይላል። የት ነው 06 ስለው ለክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጠይቅ፤ ብሎኛል ሃይለ ቃል በተሞላው።

ለመሆኑ በመቀሌ ከሚገኙት 7 ወረዳ ፖሊስ ጣብያ ውጭ 06 የሚባል እስርቤት ህጋዊ የመንግስት እስር ቤት ኣለ እንዴ ብየ ጠየቅኩት ኮነሬል ኣንድነት ግን እጅግ በመናደድ ስማ እስገደ ለራስህ ባያዝድ ሆነህ /ተበክለህ/ በዚህ ላለው ሰው ኣትበክልብን! ተጠንቀቅ ኣለኝ፡፡ ለዚህ ኣባባል ብዙ ማስረጃዎች ባሉበት በኮነሬል ኣንድነት የደረሰብኝ ማስፈራራትና ዛቻ ነው ጉዳዩ እንደዚህ እያለ ልጄ ምክንያቱ ባልታወቀ ከከተማ ወጣ ያለ ድብቅ እስርቤት ተወስዶ ሁኔታው ባለማወቃችን በጭንቀት ላይ እንገኛለን።

የተከበራችሁ ሃገር ወዳጅ ዜጎች እኔ ህውሓትን በመቃወሜ፤ በተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ተደራጅቼ በመታገሌ የህውሓት የትግል ታሪክ ጋህዲ አንድ፣ ጋህዲ ሁለት እና ጋህዲ ሶስት እንዲሁም ሌሎች ፅሁፎች በመፃፌ በስም ማጥፋት ሰበብ ተከስሼ ለሁለት ኣመት እየታሰርኩ እየተፈታሁ እስካሁን እየተንገላታሁ እንደምገኝ ሁሉም የሚያውቀው ነው፡፡

በጣም የሚያሳዝነኝ ግን የህውሓት ኢሃደግ ስርኣት መሪዎች የሚወስዱት እርምጃ ከወላጆቹ ኣልፎ ለልጅ የሚያልፍ ቂም በቀል መስራታቸው ነው። የዚህ ልጅ መታሰር ከኣሁን በፊት ኣስረው የገረፉበት ምክንያት የኣስገደ ፀረ-መንግስት የሆኑ ፅህፎች የምትሰራ ኣንተነህ በሚል እንደገረፉት ልጄ ራሱ የሚያረጋግጠው ነው፡፡

በመጨረሻ ልለው የምፈልገው ይህ ተግባር የሃገራችን በሚሊዮኖች ዜጎች መስዋእት የተረጋገጠ ህገመንግስት መናድና የህግ የበላይነት ኣለመኖሩ በተጨባጭ ያረጋገጠ እኔ ስለ ልጄ ኣሁን በደረሰብኝ ችግር ብቻ ኣይደለም እየተናገርኩት ያለሁት በኣጠቃላይ ልክ እንደ ልጄ በሌሎች ዜጎች እየደረሰ ያለው ሰቆቃም ይቁም እላለሁ፡፡

ኣስገደ ገ/ስላሴ – መቐለ

Advertisements

2 thoughts on “ልጄ በድብቅ እስርቤት ግፍ እየተፈፀመበት ይገኛል

  1. Aytalnew Newzendro May 2, 2013 at 12:16 pm Reply

    I doubt that the Italian fascists committed more crime than woyane ethnic fascists. This is a wake up call for all Tigrians and hodam collaborators from various ethnic Groups that the home grown fascists are dangereous and criminal who do not hesitate to kill anybody if they think that will prolong their reign of Terror. Ato Asgede it is really sad but if this is the Price we should pay for freedom there is no other was than to fight and get rid of These home grown fascists. http://www.ecadforum.com/2012/12/19/from-ethnic-liberator-to-national-atrocities-the-tale-of-tplf
    http://www.ecadforum.com/articles/torture-and-arbitrary-detention-in-ethiopia

    Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: