በረከት በቀለ (ፍልፍሉ) ጨምሮ 12 ኮሜዲያኖች ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው ።

ኮሜዲያኖቹ የፍርድቤት መጥሪያ የደረሳቸው ሲሆን የፊታችን ማክሰኞ ፍርድቤት ቀርበው ክሱ ጉዳያቸውን የሚታይበትን ሂደን ለመከታተል ነው።በዚህ በጉዳዩ ዙሪያ ያናገርነው እና በሰሜን አሜሪካ ለተወሰነ ጊዜያት ኑሮውን ያደረገው በረከት በቀለ ፍልፍሉ እንደገለጸው ከሆነ የክሱ ሂደትም ሆነ ሁኔታው እሱን እና ጓደኞቹን ያስገረመ ከመሆኑም በላይ ለጉዳዩ ምንም ጥልቀት እውቀት እንደሌለው እና የቀልድ ስራውን ሰርቶ ከሃገር ለስራ ግዳይ መውጣቱን ለማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል በስልክ ባደረገው መግለጫ ተናግሮአል። እኛ የማንኛውንም የእምነት ተቋም አንነቅፍም ነገር ግን መቀለድ ማለት ሆኖ መገኘት አይደለም እና ህረተሰብን ለማስደሰት እና ለማዝናናት ስንል የምንሰራቸው ቁምነገር እና ፌዞች ከክፉ ነገር ጋር ተያይዘው ሊቀርቡ የሚታዩ ሊሆን አይገባም ሲል ጠቅሶአል::filfilu_obama

አንዳንድ የአነጋገርናቸው ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ የሃይማኖቱ ተቋሙ ካነሳቸው የክስ ነጥቦች አንዱ ስኒ እና ጀበና ያሉት እቃዎች በሙሉ የአንድ ሃይማኖት መለያ ሳይሆን ማናቸውም የሃገሪቱ ህብረተሰቦች የሚጠቀሙበት ከመሆኑም በላይ አንቋሸውብኛል ማለቱ ተገቢ አለመሆኑን ጠቁመዋ። በሌላም በኩል ያነጋገርናቸው ግለሰቦች ኮሜዲያኖቹ እንዴት ሊከሰሱ ይገባል ሊከሰስ የሚገባው ከሆነ የዚህ ፊልም ስክሪፕት ደራሲ እና አዘጋጅ ብቻ መሆን አለበት እንጂ ደራሲያኖቹ ጨዋታውን ተጫወቱት እንጂ የጭብጡን ሂደት እነርሱ አልመሰረቱትም ሆኖም ግን የተከናወነው የፊልም ሂደት ከጠንቋዩ የአቶ ታምራት ገለታ ጋር የሚያያዝ እና ወቅቱን ጠብቆ የተከናወነ ስለሆነ ክሱ ውድቅ ሊደረግ ይገባዋል ሲሉ የህግ ባለሙያዎች ጠቁመዋል።

ይህንን ሲሉ አንድ ጋዜጠኛ በአዘጋጁ በኩል ክሱ ይቀርብበታል እንጂ በተናጠል ክስ እንደማይቀርብበት የሃገሪቱ ህግ ይጠቅሳል በተመሳሳይ መልኩ የኮሜዲያንም ሆነ ቴአትር በዚህ መልኩ ተያያዥነት ያለው ክስ መሆኑን ሊታወቅ እና ኮሜዲያኑ ነጻ ሊሆኑ ይገባል በማለት አክለዋል።በማንኛውም አለም ኮሜዲያኖች በሚያውት እና በሚሰሙት አዳዲስ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመቀለድ ህብረተሰብን ቁምነገር ለማስጨበጥ የሚጥሩ የስራው ባለሙያዎች መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም ።በዚህ ጉዳይ ላይ በኢትዮያ የሚገኘውን የኮሜዲያን ማህበር አባል እና አስተዳዳርን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ማለዳ ታይምስ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: