መንግሥት በዘጠኝ ወራት ውስጥ 3.9 ቢሊዮን ብር አትሟል

ethiopia-41

• ከ222 ቢሊዮን ብር የባንኮች ተቀማጭ 207 ቢሊዮን ብር ለብድር ውሏል

በዘንድሮው የበጀት ዓመት መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ ቀጥታ ብድር (ብር ማተም) እንደማይወስድ መንግሥት ገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ በዘጠኝ ወራት ውስጥ 3.95 ቢሊዮን ብር የቀጥታ ብድር መውሰዱን ብሔራዊ ባንክ ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚታየውን የዋጋ ግሽበት ለመዋጋት መንግሥት የብር ማተም (ከብሔራዊ ባንክ የቀጥታ ብድር መውሰድ) ተግባሩን ባለፈው ዓመት በማቆሙ፣ አንፃራዊ የዋጋ መረጋጋትን ፈጥሮ ነበር፡፡ ይህ ዕርምጃ ያስገኘውን ውጤት ለማስቀጠል የብር ማተም ተግባር በዘንድሮው የበጀት ዓመት እንደማይኖ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ከወራት በፊት መግለጹን ሪፖርተር አስነብቦ ነበር፡፡ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በተመሳሳይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከወራት በፊት አረጋግጠው ነበር፡፡

ይሁን እንጂ የአገሪቱን የገንዘብ ፖሊሲ የሚቆጣጠረው ብሔራዊ ባንክ ያለፉትን ዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለፓርላማው የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት፣ የመንግሥትን የበጀት ጉድለት ለመሸፈን ሲባል 3.95 ቢሊዮን ብር የቀጥታ ብድር መሰጠቱን አስታውቋል፡፡

መንግሥት የብር ማተም ዕቅድ እንደሌለውና የበጀት ጉድለቱንም በሌሎች አማራጮች እንደሚሸፍን ቢገልጽም፣ የብሔራዊ ባንክ ሪፖርት ግን እስከ በጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት መጨረሻ ድረስ ለበጀት ጉድለቱ 6.03 ቢሊዮን ብር የማተም ዕቅድ ተይዞ እንደነበር ይገልጻል፡፡ ይሁን እንጂ ከታቀደው የገንዘብ መጠን ውስጥ እስከ መጋቢት ወር መጨረሻ ድረስ 3.95 ቢሊዮን ብር ብቻ ታትሟል ሲል ይገልጻል፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሐጂ ኢብሣ ከወራት በፊት እንደገለጹት፣ የበጀት ጉድለቱ በብር ማተም የሚሸፈን እንዳልሆነና በመንግሥት የተያዘው አማራጭ ከሌሎች የኢኮኖሚው ምንጮች የበጀት ጉድለቱን መሸፈን እንደሆነ አስረድተው ነበር፡፡ ከሌሎች የኢኮኖሚ ምንጮች መካከል የግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ በዘጠኝ ወራት ውስጥም መንግሥት ይህንን አማራጭ በሚገባ እንደተጠቀመበት የብሔራዊ ባንክ ሪፖርት ያስረዳል፡፡

‹‹እንደሚታወቀው ባንኩ የግምጃ ቤት ሰነድን ለገንዘብ ፖሊሲ ማስፈጸሚያ ብቻ ሳይሆን፣ መንግሥትን በመወከል ለበጀት ጉድለት መሸፈኛ በጨረታ ያቀርባል፤›› በማለት ሪፖርቱ ያብራራል፡፡

በዚሁ መሠረት በዘጠኝ ወራት ውስጥ 59.7 ቢሊዮን ብር ከግምጃ ቤት ሰነዶች ጨረታ ለመሰብሰብ ታቅዶ 82.3 ቢሊዮን ብር በሰነዶቹ ሽያጭ መገኘቱን ያስረዳል፡፡

በሌላ በኩል ባንኩ ከተጣሉበት ኃላፊነቶች መካከል የፋይናንስ ተቋማትን መከታተልና የተረጋጋና አስተማማኝ የፋይናንስ ሥርዓትን መፍጠር ሲሆን፣ ይህም በተገቢው ሁኔታ በዕቅዱ መሠረት መከናወኑን ያስረዳል፡፡

በአገሪቱ ሁሉም ባንኮች ኅብረተሰቡ ያስቀመጠው ተቀማጭ ገንዘብ ዓምና በዘጠኝ ወራት ከነበረበት 174.89 ቢሊዮን ብር፣ በ26.9 በመቶ በማደግ 222.02 ቢሊዮን ብር መድረሱን ይገልጻል፡፡

ሁሉም ባንኮች የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ጨምሮ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ 40.99 ቢሊዮን ብር አዲስ ብድር የሰጡ መሆኑንና ይህ ግን ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት በ3.5 በመቶ ብቻ እንደሚበልጥ ከሪፖርቱ መረዳት ይቻላል፡፡

የአገሪቱ ባንኮች የሰጡት ጠቅላላ የብድር ክምችት በዘጠኝ ወራት ውስጥ 132.93 ቢሊዮን የደረሰ መሆኑን፣ በቦንድ መልክ ለተበዳሪዎች የሰጡት 74.4 ቢሊዮን ብር ሲታከልበት አጠቃላይ የብድር ክምችታቸው 207 ቢሊዮን ብር ይደርሳል፡፡ ይህ የብድር ክምችት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 28.9 በመቶ ማደጉን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡ ይህ የብድር ክምችት ባንኮቹ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የሰበሰቡት 28.58 ቢሊዮን ብር ተመላሽ ብድር ተቀናንሶ መሆኑን ከሪፖርቱ መገንዘብ ይቻላል፡፡

ባንኮቹ የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ሳይጨምር ያላቸው ጠቅላላ ካፒታል 18.4 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ሪፖርቱ ያትታል፡፡

የአገሪቱ ባንኮች የተቀማጭ ገንዘብና የብድር ምጣኔ በከፍተኛ ደረጃ ላይ መሆኑን ከሪፖርቱ መገንዘብ የሚቻል ሲሆን፣ ከጠቅላላ የብድር ክምችታቸው ውስጥም 2.4 በመቶው የማይመለሱ አጠራጣሪ ብድሮች ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡ የገንዘብና የብድር ምጣኔ ከ60 በመቶ በታች ከወረደ ባንኮች ጤናማ ንግድ ውስጥ አለመሆናቸውን ሲያሳይ፣ ከ80 በመቶ በላይ ከሆነ ድንገተኛ የደንበኞች የገንዘብ ጥያቄን ማስተናገድ እንዳይችሉ ያደርጋቸዋል፡፡

ይሁን እንጂ የባንኮቹ ጤናማነት የሚለካው ያላቸው ካፒታል ከሀብታቸው ተጋላጭነት አንፃር ሲሰላ ነው፡፡ ይህ ምጣኔ በዘጠኝ ወራት ውስጥ 13.52 በመቶ መሆኑን ሪፖርቱ ገልጾ፣ ይህም ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው የስምንት በመቶ ዝቅተኛ ምጣኔ ከፍ ያለ መሆኑን ያስረዳል፡፡

በሌላ በኩል የአገሪቱ የንግድ ሚዛን የ6.57 ቢሊዮን ዶላር ጉድለት የሚታይበት መሆኑን ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

የንግድ ሚዛን ጉድለቱን ለማስተካከል የወጪ ንግድን ማጠናከርና የውጭ ምንዛሪን ማሳደግ፣ እንዲሁም ለገቢ ዕቃዎች የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ በአገር ውስጥ ምርቶች በመተካት መቀነስ አማራጮች መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከወጪ ንግዶች የተገኘው 2.23 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን፣ መንግሥት ግን ለገቢ ዕቃዎች ያወጣው 8.8 ቢሊዮን ዶላር በመሆኑ የንግድ ሚዛኑ ጉድለቱ 6.57 ቢሊዮን ዶላር አድርሶታል፡፡

Ethiopian Reporter

Advertisements

2 thoughts on “መንግሥት በዘጠኝ ወራት ውስጥ 3.9 ቢሊዮን ብር አትሟል

  1. […] መንግሥት በዘጠኝ ወራት ውስጥ 3.9 ቢሊዮን ብር አትሟል. […]

    Like

  2. sppqnkvdv May 22, 2013 at 3:37 pm Reply

    vsrdjtfyw hoolp wmkcttc vyvy mjwgcqcxrmbuauc

    Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: