የደርባ ሚድሮክ የደጀን ሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ አቆመ

de

ሚድሮክ በኦሮሚያ ክልል ደርባ አካባቢ ግዙፍ የሲሚንቶ ፋብሪካ ከመገንባቱ በፊት፣ በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ደጀን አካባቢ ያቋቋመው የሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ አቁሟል፡፡

የደርባ ሚድሮክ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኃይሌ አሰግዴ ፋብሪካው ማምረት ያቆመው በቴክኒክ ችግር ነው ቢሉም፣ የአካባቢው የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት ኩባንያው ለፋብሪካ ምርት ጥሬ ዕቃ በሚያወጣበት ወቅት፣ የሚያፈነዳው ድማሚት ለአካባቢው ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ሥጋት በመሆኑ እንዲቆም ተደርጓል፡፡

ኩባንያው ለሲሚንቶ የሚሆነውን ጥሬ ዕቃ የሚያገኘው በአማራ ክልል  በደጀን ወረዳ ውስጥ በዓባይ ሸለቆ ውስጥ በሰጠው ቦታ ነው፡፡ ከዚህ ሥፍራ ለሲሚንቶ ምርት የሚሆነውን ማዕድን ለማውጣት የድማሚት ፍንዳታ የሚጠቀም በመሆኑ፣ ይህ ፍንዳታ በመቶዎች ዓመታት የሚቆጠር ዕድሜ ያለውን ጥንታዊውን መር ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ሊያናጋው ይችላል ተብሎ በመሰጋቱ እንዲቆም ተደርጓል ሲሉ የአካባቢው ምንጮች አብራርተዋል፡፡

በዚህ መሠረት ክልሉ ተለዋጭ ቦታ ለኩባንያው ቢያቀርብም ኩባንያው ባለፉት ሁለት ወራት ማምረት አቁሞ ሠራተኞቹን አሰናብቷል፡፡ የአካባቢው መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ ደርባ ሚድሮክ ደጀን ሲሚንቶ ፋብሪካን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዘግቶ ትኩረቱን ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በገነባው ደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካ ላይ የማድረግ አዝማሚያ አሳይቷል፡፡ “የደጀኑን ሲሚንቶ ፋብሪካ ሊነቅለው አስቧል፤” ሲሉ በፋብሪካው ውስጥ የሚሠሩ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ይህንን አስተያየት አቶ ኃይሌ አይቀበሉትም፡፡ በቅርቡ ሁሉም ነገር ወደ ቀድሞ ቦታው ይመለሳል ሲሉ አቶ ኃይሌ ፋብሪካው በቀናት ውስጥ ወደ ሥራ እንደሚመለስ ገልጸዋል፡፡

ደጀን ሲሚንቶ ፋብሪካ ሲቋቋም ከደጀን ከተማ ሁለት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ፋብሪካው ሥራ ከጀመረ በኋላ ከተማው  ወደ ፋብሪካው አካባቢ እየተስፋፋ በመሆኑ፣ በአሁኑ ጊዜ ፋብሪካው ከከተማው ጋር መግጠሙ ታውቋል፡፡

በዚህ ምክንያት ፋብሪካው የሚለቀው ጭስ ለከተማው ነዋሪዎች ጤና መታወክ  ምክንያት ሆኗል እየተባለ በሚነገርበት ጊዜ ነው ፋብሪካው ማምረት ያቆመው ይባላል፡፡

ደርባ ሚድሮክ በኦሮሚያ ክልል ደርባ አካባቢ ከገነባው የሲሚንቶ ፋብሪካ እኩል ወይም የበለጠ ሲሚንቶ የማምረቻ አቅም ያለው ፋብሪካ በደጀን ወረዳ ውስጥ ለመገንባት ቀደም ሲል ዕቅድ መያዙ ይታወቃል፡፡

Ethiopian Reporter 

Advertisements

2 thoughts on “የደርባ ሚድሮክ የደጀን ሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ አቆመ

  1. fjzumopnx May 22, 2013 at 3:36 pm Reply

    bggslgyxy lfluk txkvsnf qvty qbspxdgeiunlcax

    Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: