ጎንደር ታምሷል፤ አዲስ አበባ ህዝቡ ተነሳስቷል!

403580_322825531093385_2117987836_n

በመተማ ገንዳውሃ ከተማ ግንቦት 20 ቀን 2005 ዓ. ም የእርሻ መሬታቸው የተነጠቁ በርካታ ሰዎች በተገኙበት ስብሰባ ተካሄደ፡፡ በስብሰባው የ‹ክልሉ› ም/ አስተዳደር እንደሚገኝ ቢነገርም የተገኙት የሰ/ ጎንደር አስተዳደር ሀላፊ አቶ ግዛት አብዩ ናቸው፡፡
Blue party logo
ስብሰባው የእርሻ መሬታቸውን በተነጠቁት አርሶ አደሮች ጉዳይ ሲሆን ከፍተኛ ክርክር ተካሂዶ ስምምነት ያልተደረሰ ሲሆን አቶ ግዛት ‹‹ መሬቱን መልቀቅ አለባችሁ..›› ሲሉ ተሰብሳቢዎች ተቃውሞ አድርገዋል፡፡
አያይዘውም አቶ ግዛት ‹‹…እስከ አፍንጫው የታጠቀ መከላከያ ሰራዊት ነው ያለን ሜዳው ያውላችሁ….›› በማለት ዛቻ አሰምተዋል፡፡ አርሶ አደሮችም ‹‹ መሬቱን አንለቅም መከላከያ እገላለሁ ካለም ይግደለን፡፡›› በሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ከስብሰባው በኋላ የኢህአዴግ አባላትን ይዘው እስከ ምሽቱ 6፡00 በመሰብሰብ ችግር ይፈጥራሉ ባሏቸው ሰዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዶልተው ሂደዋል፡፡

በተመሳሳይ በጎንደር ከተማ የሚገኙ ባለኀብቶችና ነጋዴዎችን የቀበሌ ሹማምንት ‹‹የመለስ ራእይ›› የሚለው ‹‹መፃህፍን›› ከ2000.00- 5000.00 ብር ግዙ በማለት ከፍተኛ ጫና እየፈጠሩ መሆኑን ነጋዴዎች በምሬት ገለፁ፡፡ እያንዳንዱ ቀበሌ ‹‹መፅሀፉን›› ሽጦ ከ400.000.00- 500.000.00 ብር ገቢ እንዲያደርግ ታዟል፡፡

በሌላ መልኩ ቁጥቸው 500 የሚደርሱ ሚሊሻዎች ከደባርቅ ወረዳ በመሰብሰብ ለልዩ ስልጠና ከ21/ 09/ 2005 ዓ. ም ጀምሮ በድብ ባህር ልምምድ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ የስልጠናው ምክንያት በአካባቢው ባሉ የታጠቁ ኃይሎች ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ አበባ ላይ የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ የሰሞኑ የአገር ቤት አቢይ ዜና መሆኑ ተገልጿል። ከዚሁ ጋር የደረሰን መእክት እንዳስተላለፈው፤ የህዝባዊ ስብሰባው አጀንዳ ሀገራዊ በመሆኑ ቀደም ሲል ሁሉም ኅብረተሰብ ‹‹ተቃዋሚ የለም፣ ማን ያስተባብረን፣ ሚጠራን የለም፣…ወዘተ. ›› ጉንጭ አልፋ ወሬዎችን የሰበረ ነው፡፡ ይኸው ‹‹ና›› ተነስ ተቃውሞህን ግለጽ ተብለናል፡፡ በየጓዳው፣ በየካፌው፣ በየባንኮኒው፣ በየወረቀቱ፣ በየ…፣በየ…፣ መትመክመክ ዋጋ የለውም፡፡

ስለዚህ በዚህ ምቹ አጋጣሚ ሁላችንም ተነስተን ‹‹ሆ›› ብለን ተቃውሟችን እንግለፅ፡፡
በስብሰባው መገኘት የግድ የሰማያዊ ፓርቲ አባል መሆን አይደለም፣
ስብሰባው ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ይጋብዛል፣
ሁሉንም ተቃዋሚዎች ይጋብዛል፣
ሁሉንም እምነቶች ያካትታል፣
ከቤት ውጭ በመሆኑ በጣም አመችና ገላጭ ነው፣
መፈክር ይዞ ለመውጣት ያመቻል፣
ለረዥም ቀናት/ድል ለመጨበጥ/ ያመቻል፣
ከሁሉም በላይ ወሩ ግንቦት ነው፣
ጥንካሬ፣ ድፍረት፣ ቆራጥነት፣ ፅናት፣ ….ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡

የዘገባው መጨረሻ፤ ራሳችን ነፃ ወጥተን ሀገራችንን ነፃ እናውጣ!!!
…..ቱኒዝያ፣ ግብፅ፣ ሊብያ፣ የመኒያ፣……ኢትዮጵያ፣……” ብሏል ርእየ- ሁለንተና – አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ

EMF

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: