የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሰሜን ጎንደር ሉግዲ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ።

4444444

የወያኔው አምባገነናንዊ ስርዓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የጫነውን የግፍና የመከራ እንዲሁም የችግርና የሰቆቃ ዘመን ለማሳጠር ስርዓቱን በግንባር እየተፋለመ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በግንቦት 24-2005 ዓ.ም ሉግዲ በተባለው አካባቢ ከወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ጋር ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት በተካሄደው ውጊያ 44 የጠላት ወታደሮችን በመግደልና 66 በማቁሰል እንዲሁም ብዛት ያላቸው ተተኳሽ መሳሪያዎችን ከነሙሉ ትጥቃቸው በመማረክ አኩሪ የአርበኝነት ጀብድ ፈፅሟል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሚንቀሳቀስባቸው የሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተለይም በሰሜን ጎንደር አርማጭሆ፣ ወልቃይት፣ ቋራና መተማ ግንባሮች በተለያዩ ጊዜያት በጠላት ላይ በሚሰነዝራቸው ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃ በወያኔ የታጠቁ ሀይሎች ላይ ወታደራዊ የበላይነትን በመቀዳጀት የግንባሩ ሰራዊት የተሰለፈበትን ሀገርንና ወገንን የመታደግ ዓላማ ከግብ ለማድረስ ከመቸውም ጊዜ በላይ ቆርጦ በመነሳት ኢትዮጵያዊ ኩራት መሆኑን እያስመሰከረ ይገኛል።

በወታደራዊ ሀይልና በመሳሪያ ብዛት የተመካው ጎጠኛው ስርዓት አሁንም ከሚሰነዘርበት የሀይል ጡጫ መቋቋም የተሳነው በደረሰበት ሽንፈትና በተከናነበው የሐፍረት ካባ ጀርባውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት እያሳዬ ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ መፈርጠጡም ታውቋል።

በመጭረሻም ግንባር የጀመረውን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማዳን ተልዕኮ ከመቼውም ጊዜ በላይ አጠናክሮ እንደሚገፋበት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያስታውቃል።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: