ግብጽ ኢትዮጵያ ላይ መዛቷ ለዉስጣዊ ፖለቲካ ቁማር መሆኑን ሰማን

mm

ሞሃመድ ሞርሲ በቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት ለህዝባቸው የ”ብሄራዊ ዕርቅ” ጥሪ ባቀረቡበት ወቅት ያደረጉት ንግግር እና ጥረታቸው የግብጽ ህዝብ ከተቀየመባቸው ዋነኛ ችግር ትኩረት ለማስቀየር እና ለማደናቀፍ ነው ሲሉ የተቃዋሚ ሰልፍ አደራጁ ወቅሰዋቸዋል።

አደራጁ ፕሬዝዳንቱ ስልጣን የያዙበትን በዓል በተቃውሞ ሰልፍ የሚያደርጉት ዘመቻ ከስልጣናቸው ሊያወርዳቸው እንደሚችል ሰግተው ህዝብን ትክክለኛ ባልሆነ ምክንያት ለማስተባበል የሚያደርጉት ስትራቴጂ ነው ብለዋል።

አቶ ባድር ፕሬዝዳንቱ ስልጣን መልቀቅ አለባቸው ሲሉ ተሰምተዋል።

በሌላ ዜና አልጃዚራ ግብጽ ኢትዮጵያን አስጠነቀቀች ሲል ዘግቧል። አቶ ባድር የፖለቲካ ቁማር እንደሆነ የገለጹትን ይህን የሞሃመድ ሞርሲን ንግግር አልጃዚራ ሁኔታው የተባባሰ የማስመሰል ጥረት ማድረጉ ይህ የዜና አውታር ገለልተኛ መሆኑን አጠያያቂ ያደርገዋል ሲሉ የገለጹት ቀድሚ ጋዜጠኛ የነበሩ አስተያየት ሰጪ ናቸው።

ይህን ያሉትም ሚዲያው በማጋነን ለአንድ አካል ያደላ ዜና ጽፏል በሚል ነው። በተለይም ”ሁሉም አማራጭ ክፍት ነው” ያሉት የሞርሲ ንግግር ኢትዮጵያ ለልማት ብቻ እንጂ ግብጽን ለመጉዳት አለመፈለጓ እየታወቀ በመሆኑ ይህንን ክግብጽ የናይል ጥገኝነት እና የጥፋት ፍራቻ ጋር ማያያዝ እንዲሁም የኢትዮጵያን አመለካከት ወደ ጎን መተው ፍትሃዊነት የለውም ሲሉ አበክረው ተናግረዋል።

እሳቸው በቃላቸው ”አልጃዚራ እንደ አማራጭ የመረጃ ምንጭ ሊታይ የሚችል የዜና አውታር ነው። ነገር ግን በዘገባቸው ነገሮችን ለአረቡ ማህበረሰብ ጥቅም የመጠምዘዝ አዝማሚያ አለባቸው።” ካሉ በኋላ ”እንደ ጋዜጠኛም ሆነ በሚዲያ ነጻነት ለብዙ ዓመታት አክቲቪስት ሆኖ እንደሰራ ሰው መናገር የምችለው አልጃዚራ ገለልተኝነቱ ላይ ጥያቄ እንዳለብኝ ነው” ብለዋል። ምንጮች (አህራም እና አልጃዚራ)

wolaita

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: