የተከሰሱ ሰዎች ሕገ መንግስታዊ መብት ሊከበር ይገባል!

943206_571066916270709_2041270244_n

ጋዜጣዊ መግለጫ
የተከሰሱ ሰዎች ሕገ መንግስታዊ መብት
ሊከበር ይገባል!

ጥር 28/2005 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ራድዮ ድርጅት በፌደራል ፖሊስ እና በብሄራዊ ደህንነት እና ፀጥታ ባለስልጣን የተዘጋጀ ዘገባዊ ፊልም ለህዝብ ማቅረቡ ይታወቃል። የዶኩመንታሪዉ ይዘት በአሁኑ ሰዓት ከመስከረም 15/2005 ዓ.ም ጀምሮ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሸባሪነት ወንጀል ተከሰዉ ፍርድ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙትን ተከሳሾች በተለያ የሽብር እና የአመፅ ተግባራት ያላቸዉ ተሳትፎ እና ዝግጅት ላይ የሚያጠነጥን ነዉ። ጥናታዊ ፊልሙ እነዚህ የተከሰስንበትን ወንጀል አልፈፀምንም ብለዉ በፍርድ ቤት በመከራከር ላይ የሚገኙትን ተጠርጣሪዎች ከናይጄርያዉ ቦኮ ሃራም፣ ከሶማልያዉ አልሸባብ እና ከአልቃይዳ ጋር በማመሳሰል የሽብር ወንጀል ለመፈፀም ሲያሴሩ እና ሲዘጋጁ እንደነበር ይገልፃል። ፊልሙ የብሄራዊ ደህንነት እና ፀጥታ ባለስልጣን እነዚህን ተጠርጣሪወች ለብዙ ዓመታት ለወንጀል ዝግጅት ሲያደርጉ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ቢገልፅም እነዚህ የወንጀል ዝግጅቶች ስለመደረጋቸዉ የቀረበዉ ማስረጃ ግን ተከሳሾቹ በራሳቸዉ ላይ ሲመሰክሩ የሚያሳይ ቃለ ምልልስ ብቻ ነዉ።

የፌደራል ፖሊስ እና የብሄራዊ ደህንነት እና ፀጥታ ባለስልጣን እንደ መንግስት ተቋምነታቸዉ በአሁኑ ሰዓት በፍትህ ሚኒስቴር የፊደራል ማዕከል ዐቃቤ ህግ በነዚህ ተጠርጣሪወች ላይ በከፈተዉ የሽብርተኝነት ወንጀል ክስ በምርመራ ያገኙትን ማስረጃ እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።

ይህም ማለት እነዚህ ተቋማት ያቀረቡት ማስረጃ በፍርድ ቤት ተቀባይነት አግኝቶ ፍርድ ቤትም የመጨረሻዉን ዉሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ተጠርጣሪወቹን በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 20 መሰረት በተከሰሱበት ወንጀል እንደጥፋተኛ ያለመቆጠር መብታቸዉን ሊያከብርላቸዉ ይገባል።

ነገር ግን ተቋማቱ ይህንን ባለማክበር ተከሳሾቹን በይፋ ወንጀል ስመፈፀማቸዉ አዉጀዋል። ይህም ተከሳሾቹ እስከ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ዉሳኔ ድረስ ንፁህ ሆኖ የመገመት መብታቸዉን የጣሰ ሲሆን በተጨማሪም ተከሳሾቹ በፍርድ ቤት የመከላከያ ማስረጃ የማቅረብ አቅማቸዉንም አስቸጋሪ ያደርገዋል።

ከሁሉም በላይ ይህ ዘገባዊ ፊልም ፍርድ ቤቶች በህዝብ ዘንድ ያላቸዉን ተቀባይነት የሚያዛባ ይሆናል። ይህን መሰሉ ከፍርድ ቤት ዉጭ የሚደረግ የወንጀለኛነት ዉሳኔ ፍርድ ቤቱ ለወደፊት የሚሰጠዉን ማንኛዉም ፍርድ አስቀድሞ የሚወስን ነዉ። በአንድ በኩል የፌደራል ፖሊስ እና የብሄራዊ ደህንነት እና ፀጥታ ባለስልጣን ያላቸዉን ማስረጃ በዐ.ህግ በኩል ለፍርድ ቤት አቅርበዉ የተከሳሾቹን የወንጀል አድራጊ መሆን ወይም አለመሆን እየተጠባበቁ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የተከሳሾቹን የሽብር ወንጀል ፈፃሚነት መንግስታዊ በሆነዉ የሚዲያ ተቋም አዉጀዋል፤እያወጁም ነዉ።

በመሆኑም የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ(ሰመጉ) ይህን ከላይ የተጠቀሰዉን ድርጊት አጥብቆ የሚያወግዝ ሲሆን ዘገባዊ ፊልሙን ያዘጋጁት እና እንዲሰራጭ ያደረገዉ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ራድዮ ድርጅት ከድርጊታቸዉ እንቆጠቡ እና የሚመለከተዉን የመንግስት አካልም ድርጊቱን በማዉገዝ አስፈላጊዉን ማስተካከያ እንዲያደርግ ይጠይቃል።

ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: