እነዶ/ር ሺፈራው ማኅበረ ቅዱሳንን የሚወነጅሉበት የአክራሪነት ክሥ ወደ ‹‹የጎዳና ላይ ነውጥ ማነሣሣት›› ተጠናከረ

sendek-newspaper-sene-04-2006-e-c000ይህ የዛሬ ረቡዕ፣ ሰኔ ፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ሰንደቅ ሳምንታዊ ጋዜጣ ዘገባ ነው፡፡ ዘገባው÷ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በሚያዝያ ወር ፳፻፮ ዓ.ም ‹‹አክራሪዎች/ጽንፈኞች በተሳሳተ መንገድ ሃይማኖታዊ ይኹንታን ለማግኘት በሕዝባችን ውስጥ የሚያነሷቸው የማደናገርያ መልእክቶችና ማብራሪያቸው›› በሚል ርእስ ባዘጋጀውና በቅርቡ በአዳማ ከተማ ለሚዲያ ባለሞያዎች በሰጠው ሥልጠና ላይ ተመሥርቶ የቀረበ ነው፡፡

ሰነዱ፣ ሚኒስቴሩ በመጋቢት ወር አጋማሽ ማኅበረ ቅዱሳንን አስመልክቶ በሚዲያዎች ከተላለፉት ዘገባዎችና ከቀረቡት ጽሑፎች በመነሣት በከፍተኛ ሓላፊዎች የተመራ ግምገማ ካደረገ በኋላ ‹‹በማኅበሩ የመሸገ አክራሪ ኃይል እንዳለ የተያዘውን አቋም በማጽናት ማኅበሩን ግን ለማፍረስ የተደረገ እንቅስቃሴ እንደሌለ ማብራራት›› በሚል የተሰጠው አቅጣጫ የተካተተበት እንደኾነ ተጠቁሟል፡፡ማኅበሩ ውስጥ በመሸጉ የፖሊቲካ ዓላማ ባላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ‹‹አሉባልታ ይነዛሉ፤ ሕዝቡን ያደናግራሉ›› የተባሉት የኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ከአጀንዳው አኳያ ቅድሚያውንና የበላይነቱን የያዙበት ኹኔታ ከግምገማው አነጋጋሪ ነጥቦች አንዱ እንደነበር ታውቋል፡፡

በሰነዱ፣ የበላይነት የተያዘባቸውን መረጃዎች በበቂ ለማስተባበል አልያም በወረዳና በክፍላተ ከተሞች ደረጃ የግንባሩ አደረጃጀቶች በተሳተፉበትና በቅርቡ በተካሔደው ማኅበረሰብ አቀፍ ውይይት ፍረጃውና ትንታኔው ለአመራሩና አባሉ እንኳ አሳማኝ ያልኾነ የአክራሪነት ክሥ በማኅበሩ ላይ የቀረበበት ኹኔታ በማንኛውም መገለጫው ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርግ አቀራረብ አለመታየቱ በሥልጠናው ተሳታፊዎች ተገልጧል፡፡

‹‹የጎዳና ላይ ነውጥ ለማነሣሣት ሁከትና ብጥብጥ የሚሰብኩና የሁከትና ብጥብጥ መንገድን የሚቀይሱ›› ግለሰቦችና ቡድኖች በማኅበሩ ጥላ ሥር መሸሸጋቸውንና በማኅበሩ መወገዝ እንዳለባቸው የሚገልጽ የተጠናከረ ክሥ የቀረበበት ሰነዱ፣ ‹‹የመንግሥት ፍላጎት ማኅበሩ ከእኒህ አካላት ራሱን እንዲያጸዳ ነው፤›› ብሏል፡፡ ‹‹ማኅበሩን ለማዳከምና ለማፍረስ መንግሥት እንደሚንቀሳቀስ ተደርጎ የሚቀርበው አሉባልታ ቀድሞ በማስጠንቀቅ ከተጠያቂነትና ከሕግ የበላይነት አሠራር ለማምለጥ ይጠቅመናል የሚል ስልት ከኾነ የተሳሳተ አመለካከት ይኾናል፤›› ሲልም አሳስቧል፡፡

በኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች በቀረቡ ዘገባዎችና ጽሑፎች ላይ ተመሥርቶ በሚ/ር ዴኤታው አቶ ሙሉጌታ ውለታው በተመራው የሚኒስቴሩ ግምገማ፣ የተላለፉት መረጃዎች ሐሰት እንደሌለባቸውና እነዶ/ር ሺፈራው በፀረ አክራሪነት ትግሉ አያያዝ ላይ ድክመት እንዳለባቸው ማሳየቱ ተጠቁሟል፡፡
የግንባሩ አመራሮችና አባላት ጭምር የተቃወሙት የእነዶ/ር ሺፈራው ማኅበሩን በማዳከም ቤተ ክርስቲያንን የማቀጨጭ የአክራሪነት ፍረጃና መፍቀረ ፕሮቴስታንታዊ ብሎግ መር ትንታኔ የግንባሩን ድርጅታዊ መዋቅር ለማይቀለበስ አደጋ ሊያጋልጠው እንደሚችል ግንዛቤ ተወስዷል፡፡
‹‹ከማኅበሩ ጋራ የተጀመረው ውይይት መቋረጡ ተገቢ አልነበረም፤ በውይይት ይዘን መሔድ ነበረብን፡፡›› /ግምገማው ያመለከተው ድክመት/
የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ተቃዋሚ አማሳኞች፣ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ አስገዳጅ ኹኔታ በመፍጠርና በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ለሚያካሒዱት ዘመቻ ‹‹በቅርብ ክትትል እገዛ እንደሚደረግላቸው›› በዶ/ር ሺፈራው እንደተገለጸላቸው ተናግረዋል – ‹‹አንዳንዶቹን ጳጳሳት አስቀድመን አስጠርተን አስወርድንባቸው፤ አባ እስጢፋኖስ ራሳቸው ተነሥተው ለቅቄአለኹ እንዲሉ አስደረግናቸው፤ ታዲያ ፓትርያርኩ እስከ ጥቅምት ሲኖዶስ ድረስ ሥራ አስኪያጅ [የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት] ኹነኝ ብለው አላስቀምጠኝ አሉ፤ ዶ/ር ሺፈራው በቅርብ ክትትል ጥበቃ የሚደረግልህ ወዳጃችን ነኽ አለኝ፤ ማኅበረ ቅዱሳንም ሐዘን ላይ ነው፤ ሕንፃው ንብረታችን ነው፤ ልቀቁልን ብለን እሪ ልንል ነው፤ መንግሥትም በትኑ ብሎ ለአመራሩ መመሪያ ይሰጠዋል፡፡››
/የአማሳኞቹ ቀንደኛ አስተባባሪ የኾነው ‹ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ
ከተናገረው/

‹‹ከዚኽ በፊት ተደፍቀው የነበሩ ሃይማኖቶች የተረጋገጠላቸውን መብት ከሕገ መንግሥታዊ መርሖ ባፈነገጠ መልኩ በመጠቀም ሌላ ገጽታ ያለው የተዛባ የሃይማኖቶች ግንኙነት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ጥቂት ግለሰቦች፣ በፌዴራል ሥርዓቱ የተረጋገጠውን የሃይማኖት እኩልነት ምቹ ኹኔታ በመጠቀም ራሳቸው የሚከተሉት እምነት የበላይነት እንዲኖረው በስፋት ሲረባረቡ ይገኛሉ፡፡››
ዶ/ር ኃይለ ሚካኤል አበራ ‹‹አዲሲቷ ኢትዮጵያና የሃይማኖት
ብዝኃነት አያያዝ›› በሚል ርእስ ካቀረቡት ጽሑፍ የተወሰደ ነው፡፡
ዶ/ር ሺፈራውና የመሰሏቸው የመንግሥት ሥልጣንን በመጠቀም
ፕሮቴስታንታቲዝምን ለሚያደላድሉበት የሸፍጥ ቁመና በገላጭነት ቀርቧል፡፡

‹‹መንግሥት በሃይማኖት ነክ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች የሚሠሩ ባለሥልጣናቱን ሚዛናዊነት በቅርበትና በየጊዜው መከታተልና መፈተሽ ይኖርበታል፤ አለበለዚያ አደጋው ለራሱ ነው፡፡›
/ከጥር ፳ – ፳፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. በደሳለኝ ሆቴል የኢትዮጵያ
የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠርቶት በነበረውና በዶ/ር ሺፈራው
በተመራው ውይይት በታየው የተሳትፎ ዕድል አሰጣጥ ግልጽ አድልዎ
ሳቢያ መድረኩን ጥለው የወጡ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት
ጽ/ቤት ከፍተኛ ሓላፊዎች ከሰጡት አስተያየት/

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: