ሰሞኑን የተደረገው የደመወዝ ጭማሪ ትኩሳት

IMG_2612ናትናኤል በርሔ ( ኖርዌይ ቲንግቮል)

ለአንድ አገር አስተዳደር መንግስት ለዜጎቹ መሰረታዊ ፍላጎቶች ከሆኑ ነገሮች አንዱ የሆነው ሰው ስራውን ሰርቶ በቂ የላፋቱን ዋጋ ማግኘት መብት ነው በተለይ በአሁኑ ሰዖት መንግስት እከተለዋለሁ ከሚለው መርህ የተገላቢጦሽ እየሆነ ዜጎች በገዛ አገራቸው በተፈጥሮዋዊ ወይም በሰው ሰራሽ አደጋ የኢኮኖሚ ግሽበት ከድጡ ወደ ማጡ እየተሸጋገሩ ይገኛል።የቀድም ጠቅላይ ሚኒስተር የሽግግር መንግስቱ ሲመሩበት በነበር ጊዜ በዋሽንግተን ዲሲ october 1995 በተጠየቁት ጥያቄ ” የዛሬ 10 ዖመት ወይም 20 ዖመት በሗል ኢትዮጵያ በዚህ ሁኔታ ባየው ደስ ይለኛል ብለው የሚያስቡት” ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ እሳቸው ሲመልሱ የዛሬ 10 ዖመት ይሆናል ብየ ተስፋ የማደርገው እና የምመኘው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በቀን 3 ጊዜ ምግብ ያገኛል የሚል ነው።ከዛም ቀጥሎ ምናልባት በጣም የተሳካልን እንደሆን በአመት 2 ቅያሪ ወይም 3 ቅያሪ ልብስ ያገኛል እንዲሁም ከዛ በጣም የተሳካልን እንደሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ህዝብ ግፋ ቢል ከመንገድ 2 ሰዖት ርቀት በላይ ይኖራል።በተጨማሪም የኢትዮጵያ ህዝብ ምግብ አማርጦ ይበላል።ነገር ግን ከ19 ዖመት በፊት የተናገሩት ቃል የተስፋ ቃል ከመሆን ያለፈ እና የዘለል አልሆነም።የኑሮ ውድነቱ ይልቁንስ የታችኛው ክፍል ህብረተሰብ ፈተና ውስጥ እና አደጋ ውስጥ ከቶታል።በተለይ የደመወዝ ጭማሪ ጋር በተያያዘ ጭማሪው ይመለከተናል የተባለው የመንግስት ሰራተኞች አብዛኞቹ ይጨመርላቸዋል የተባለው ጭማሪ የኑሮውን ሁኔታ ከመቅረፍ ይልቅስ ኑሮው የባሰ የሚያደገረሽ እና ገንዘብ የመግዛት አቅም ያሳጣዋል።መንግስት ከወራት በፊት የደምዝ ጭማሪ አደርጋለሁ በማለቱ ምክንያት በአንዳንድ ምርቱን አምራች ፋብሪካዎች የምርት አቅርቦታቸው ላይ ጭማሪ አሳይተዋል።

በዚህም በተያያዘ ዜጎች፣ገበሬዎች፣ተማሪዎች፣ክሊኒኮች፣ሆስፒታሎች፣ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች የጥራት መጋደል እና በበቂ ሁኔታ ያለመቅረብ ችግሮች ያመጣል።ነጋዴ እና ቸርቻሪ ነን ባዮች ሕዝቡን ጨርቁን አስጥሎ ለመስደድ ቆርጠው የተነሱ ይመስል ከመንግስት ጋር እሽቅድምድም ይዘዋል፡፡ መንግስት ዋጋ ተምንኩ ሲል፣ እነሱ ከላይ ከላይ ዋጋ ይጨምራሉ፡፡ ሸማቹ ግን የእነሱን ጭማሪ ያክል እድገት በየወሩ እንደማያስመዘግብ የታወቀ ነውና ግራ መጋባትን ሲጋፈጥ ይስተዋላል ይህ መተረማመስ ወራትን ተሻግሮ እንደ ከዚህ በፊቱ ድስት ጥዶ የዘይቱን ማለቅ ያየ ሮጥ ብሎ ከሱቅ ማግኘት አልቻለም፡፡ ብዙዎችም ቡና በጨው ሳይወዱ ለመጠጣት ተገደዱ፡፡ ልብሳቸውን በአመድና በእንዶድ ማጠብ እስኪከጅሉ ድረስ የሳሙና ዋጋ የማይቀመስ ሆነ፡፡ አሁን ደግሞ መንግስት የቸርቻሪነትና የአከፋፋይነት መብቱን መንግስት ነክ ለሆኑ ተቋማት አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ እውነት ይሄ ግና እስከምን ድረስ ያስኬዳል ?
ለመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ከመደረጉ በፊት ደሞዝ ሲጨምር አብረው ዋጋ የሚጨምሩትን ነጋዴዎች ለመቆጣጠር ተብሎ የዋጋ ተመን መደረጉ በብዙ ሚዲያዎች ተወራ፡ ፡ ደስ ብሎን ሳናበቃ የደሞዝ ጭማሪው ምን ያክል እንደሆነ ሳናውቅ የዋጋ ጭማሪን መንግስት ራሱ አንድ ብሎ ጀመረው፡፡ ማባሪያና ማቆሚያ ያጣው የየወሩ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ያልነካካው ማን አለ?

በመጀመሪያው ወር የትራንስፖርት ወጭው አንድ መቶ ብር የነበረ ግለሰብ፣ በሁለተኛው ወር ወደ አንድ መቶ አስራ አምስት ብር፤ በሶስተኛው ወር ወደ አንድ መቶ ሃያ አምስት ብር፤ በአራተኛው ወር ወደ አንድ መቶ ስልሳ ብር እያደገ ይገኛል፡ ፡ ለመሆኑ የትኛው ኢትዮጵያዊ ሰራተኛ ነው በየወሩ ይህንን ያክል ጭማሪ መሸከም የሚችለው; በደሞዙ ወይም በገቢው ይህን ያክል ጭማሪ መቋቋም የሚያስችል እድገት እያገኘ ያለው የትኛው ሰው ነው? ሁሉም የትራንስፖርት አማራጮች እጅግ እጅግ አስጨናቂ በሆኑበት በዚህ ዘመን በእግር መሄድን ምርጫ ማድረግ የብዙዎች
ግዴታ እየሆነ ነው፡፡

መንግስት ነዳጅ ወር እየጠበቀ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን ተያይዞታል፡፡ የዚህን ምክንያት በተመለከተ በየጊዜው ምክንያቶች ይደረደራሉ፡፡ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ስለጨመረ የአረብ ሀገራት በአብዮታቸው ምክንያት ያቀርቡት የነበረው የነዳጅ መጠን ስለቀነሰ ወዘተ ይባላል፡፡ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ስለጨመረ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ቆዳ ከመወጠር ሌላ አማራጭ የለውም ? ለመንግስት ሰዎች ስብሰባ የቅንጦት ውሃና ኩኪስ መግዣ በየጊዜው እንደ ርችት ለሚረጩት የጽህፈት መሳሪያዎች ወይም ለሌላ አልባሌ መዝናኛ የሚወጡ ወጭዎችን ቆጥቦ ነዳጅ ላይ ድጎማ ማደረግ አይቻልም እንዴ ?

የደሞዝ ጭማሪው የተደረገው ለመንግስት ሰራተኞች እንጅ ለሁሉም የሀገሪቱ ሰራተኞች አይደለም፡፡ እንደውም ይህንን ልብ ብለን ከተመለከትነው ከምሬት ብዛት ሊያስቀን የሚደርስ እውነታ እናያለን፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃ ኖሯቸው በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ ሁለት መምህራንን ብናነጻጽር፣ ይህንን እውነታ ማየት እንችላለን፡፡ ለነገሩ የግል መስሪያ ቤቶች ጉዳይ አሁንም ስግብግብ ነጋዴዎችን የሚመለከት ቢሆንም፣ ተቀጥረው የሚሰሩት ግን እንደዜጋም፣ እንደነጋዴም፣ እንደሰራተኛም ሊታሰብላቸው ይገባል፡፡

መንግስትም ቢሆን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቅ ከነበረው የደሞዝ ጭማሪ በታች እንደ ጨመረ ብዙዎች ይስማማሉ፡ ፡ በሰላሳና አርባ ፐርሰንት ብቻ የሚወሰን ጭማሪ ያደርጋል ብሎ ላለመገመት ታላቁ መነሻ መንግስት ቀድሞ ይሰጣቸው የነበሩ የሚያጓጉ መግለጫዎች ነበሩ፡፡የሆነው ሆኖ፣ ሀገራችን ይህን በመሰለ የወል እውነታ ውስጥ እንዳለች እየታወቀ፣ የኑሮ ውድነት ከእለት እለት ሲባባስ፣ አሁንም መፍሄ እየተባሉ የሚወሰዱ እርምጃዎች ችግር ሲያባብሱ እንጅ ሲያሻሽሉ እያየን አይደለም፡፡

ሰሞኑ የተጨመረው የደምዝ ጭማሪ ውጤታማ እና አመርቂ አለመሆኑን በሰራ ላይ እናየዋለን ለምሳሌ ያክል ስኳር አቅርቦትን መንግስት አገር ውስጥ የሚያደርሳቸውን ምርት ለህብረተሰቡ በበቂ ከማዳረስ ያለፍ ገበያውን በማን አለብኝነት ተቆጣጥሮ ድሃውን ህዝብ የዕለት ጉርሱን በመንጠቅ ለረሃብ እና እርዛት ዳርጎታል።ታሪክ
እንደሚያወሳው ከሆነ በንጉሱ ዘመን የመጨረሻ ስርዓት መውደቅ ለፊውዳሉ የቀረቡና የንጉሱን ቤተሰቦች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ስልጣን ላይ መቀመጥ መሞከር ትልቁ ምክንያት በትራንስፖርት ላይ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በአገሪቱ ላይ በመደረጉ ነበር።የኢህአዴግ መንግስት ስልጣን በተረከበ ዘመን ኢኮኖሚውን በምኒተሪ እና በፊሲካሊ ፖሊሲ በነፃ የንግድ ስም ህዝቡን እያታለሉ በማደናገር የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም የሚደረግ ስልታዊ መንገድ ነው።

በአገራችን የምትገኝበት ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ምስቅልቅል፣የፖለቲካው ነፀብራቅ ነው።የዚህ ምስቅልቅል በመሆኑም ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው አንዱ ማሳያ ከፍተኛ የሆነ የዜጎች ስደት ነው።ባለፉት ዓመታት በኢኮኖሚው እና ፖለቲካው ዙሪያው ባጠኑት ጥናት ተቋማት የኢትዮጵያ ዜጎቿ ለኑሮ የማይመርጧት ሀገር እንደሆነች ተዘግቧል። 46% የሚቆጠሩ ዜጎች ከሀገራቸው ውጭ በስደት የመከራን ሕይወት ለመግፋት ተገደዋል።ዜጎች ባገራቸው ሰርቶ የመኖር ዕድሉን ማግኘት ካልቻሉበት ሀገር፣ስደት መምረጣቸው ፣የትምህርት፣የስራ ፣የቁጠባ ዕድል ለሁሉም እንዲደርስ ማድረግ ግድ የሚል በተለይ ወደ ዓረብ አገራት የሚሄዱ እህቶቻችን የሚደርስባቸው ግፍና ውርደት ፣ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ነው።ሁሉም አንገት የሚያስደፋ ሆኖዋል።በነዚህ ሀገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሰሩበትን የደመወዝ ይከለከላሉ፣ ዜጎች በቂ ጥሪት እንዲያፈሩ ከማገዝ ጎን ለጎን ይደበደባሉ፤ ይደፈራሉ፤ በግፍ ይታሰራሉ፤ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ይገደላሉ፡፡ ይህ ዓይነት የዜጎች መብት በድርጅት፣በማህበረሰብን ጥቅም መብት ማስከበር አልቻለም።በኢትዮጵያ የተከሰተው የኑሮ ውድነት ዘላቂ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ ሕዝቡ በመንግስት ላይ ግፊት ማድረግ አለበት።በምርጫ ሰምን የሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ ማስተካከያ ህዝብን መደለል አይቻልም።ቸር እንሰንብት፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: