ነጋዴዎች በግብርና በተለያዩ ሰበብ አስባቦች እየተዋከቡ መሆኑን ገለጹ

esat
ነሃሴ ፳፫(ሃያሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ነጋዴዎች ለኢሳት እንደገለጹት መንግስት በሰበብ አስባቡ ከገበያ
እያስወጣቸው ነው።አንዳንድ ነጋዴዎች አድሎአዊ በሆነ ሁኔታ ከሚጣለው ግብር በተጨማሪ ፣ በአስተዳደራዊ በደሎች እየተማረሩ ነው።
በአዋሳ ነዋሪ የሆኑ አንድ ነጋዴ እንደተናገሩት፣ ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ በተጣለባቸው ግብር ድርጅታቸውን ሸጠው ስደት ለመምረጥ እየተገደዱ ነው
በሚዛን ተፈሪ ነዋሪ የሆኑ ሌላ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው በከተማዋ የሚገኙ በርካታ ነዋሪዎች ከግብር ባሻገር በከተማው የሚሰሩ ባለስልጣናት
በሚያሳዩት ዘረኝነት በርካታ ነጋዴዎች ድርጅታቸውን እየዘጉ አካባቢውን እየለቀቁ ናቸው።
በባህርዳር ነዋሪ የሆኑ ሌላ ነጋዴም እንዲሁ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በሚፈጥሩት አስተዳዳራዊ በደል ድርጅታቸውን ዘግተው ለመቀመጥ
መገደዳቸውን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ ዜና ደግሞ ለመንግሥት ሠራተኞች ከሐምሌ ወር 2006 ዓ.ም ጀምሮ የተደረገውን የደመወዝ ጭማሪ ተከትሎ በሸቀጦች ላይ ተገቢ ያልሆነ
ጭማሪ አድርገዋል ባላቸው 1 ሺህ 602 ነጋዴዎች ላይ የማሸግና ከባድ ማስጠንቀቂያ የመስጠት እርምጃ መውሰዱን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ የተገኘ መረጃ አመልክቷል፡፡
ከቢሮው የተገኘ መረጃ እንዳመለከተው በቂ አቅርቦት እያለ ሰው ሰራሽ የዋጋ ንረት እንዲከሰት አድርገዋል በሚል እርምጃ በ716 ላይ የማሸግ እርምጃ፣ በ886 ደርጅቶች ላይ ደግሞ ከባድ ማስጠንቀቂያ ተላልፎባቸዋል።
ነጋዴዎቹ እርምጃው የተወሰደባቸው ሸቀጦችን በመደበቅ፣መንግስት በድጎማ ያስገባቸውን ምርቶች በመደበቅ፣ አየር በአየር በመሸጥና ሰውሰራሽ
እጥረት ፈጥረዋል በሚል ክስ ነው፡፡
አንድ በሸቀጣ ሸቀጥ ንግድ ሥራ ላይ የተሠማሩ ነጋዴ ለዘጋቢያችን እንደተናገሩት «በቅርቡ ቀበሌዎች በድንገት መጥተውከዋጋ በላይ ትሸጣለህ፣ሸቀጥ
ደብቃለህ በሚል ምላሼን እንኳን ሳይሰሙ 6 ቤተሰብ የማስተዳድርበትን ሱቁ አሽገው ሄዱ፡፡ምን እንዳጠፋሁ፣ለማን አቤት እንደምል እንኳን
በማላውቅበት ሁኔታ ሱቄ ታሸገ፡፡በሁዋላም የወረዳ ኃላፊዎቹ ጋር ሄጄ ሳለቅስ ሁለተኛ በዚህ አድራጎት ብገኝ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰድብኝ ብለህ ፈርም
ብለውኝ ፈርሜ ሱቄ የተከፈተልኝ ሲሆን እንዲህ የሚያደርጉትን በመጠቆምም እንድትባበራቸው አስጠንቅቀውኛል» ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ነጋዴው አያይዘውም «እንደ ዘይትና ስኳር ያሉ ምርቶች መንግሥት ካደራጃቸው የሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት ያገኙ እንደነበር፤በአሁኑ ሰዓት
ግን ማህበራቱ አየር በአየር ንግድ በመልመዳቸው ምርቱን ማግኘት መቸገራቸውን ጠቅሰው መንግሥት ለዚህ ችግር መጠየቅ ያለበት ያደራጃቸውን
ማህበራት እንጂ እኛን አልነበረም» ብለዋል፡፡
ለመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ መደረጉ ከተነገረ በኃላ በከፍተኛ ደረጃ ያሻቀበው የዋጋንረት ለመቆጣጠር መንግስትጅምላና ቸርቻሪ
ነጋዴዎችንና አምራች ኢንዱስትሪዎችን በየእለቱ ስብሰባ በመጥራት፣ሱቃቸውን በማሸግና ነጋዴዎችን በማሰር ተደጋጋሚ እርምጃ እየወሰደ ያለ
ቢሆንም በገበያ ላይ የሸቀጦችን ዋጋ በተጨባጭ ሊያረጋጋ ባለመቻሉ የህብረተሰቡ ምሬት ከፍተኛ ደረጃ ደርሶአል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: